Get Mystery Box with random crypto!

_ወንጌልንና ተረት ተረትን እንለይ__ በተለይም ማንኛውም ሰው ጉባዔ ያልዋለበትን እና ያላደላደለውን | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

_ወንጌልንና ተረት ተረትን እንለይ__
በተለይም ማንኛውም ሰው ጉባዔ ያልዋለበትን እና ያላደላደለውን መጽሐፍ ቅዱስ በራሱ መሰለኝ መተርጎም አይገባም። ጥቅስን ለራስ ዓላማ ማዋል ሰይጣናዊ ጠባይ ነው። ጌታን እንዲህ ተብሎ ተጽፏል ብሎ ሰይጣን ለራሱ ዓላማ መጽሐፍ ቅዱስን ጠቅሶ ነበር። ነገር ግን ጌታ እንዲህም ተብሎ ተጽፏል ብሎ ነገሩን ከንቱ አድርጎበታል። ያልተማሩትን ቃል መጥቀስ ያላሳደጉትን ውሻ ጆሮ እንደመቆንጠጥ ነው። ያ እንዲናከስ። ይህም ያሰናክላል። አጥዐወ ጣዖት አመለከ ከሚለው የግእዝ ግሥ "ጣዖት" የሚል ምዕላድ ይወጣል። ጣዖት ምሥጢራዊ ትርጓሜው ሳይፈጥር የሚመለክ የሚፈራ ማለት ነው። ሰማይንና ምድርን የፈጠረ አንድ አምላክ ነው ያለው። ሳይፈጥሩ በውሸትና በተንኮል የሚመለኩ ፍጥረታት ጣዖታት ይባላሉ። እግዚአብሔር ግን ፈጥሮ የሚገዛ ስለሆነ ከእኔ ውጭ ሌላ አምላክ አታምልክ ብሎ ተናግሯል። ዘጸ. ፳፣፪ "ወይቤ አነ ውእቱ እግዚእ እግዚአብሔር ዘአውፃእኩከ እምድረ ግብፅ እምቤተ ቅንየት። ጽኑ አገዛዝ ከምትገዛበት ከግብፅ አገር ያወጣውህ ፈጥሬ የምገዛህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። ኢታምልክ አማልክተ ወኢምንተኒ ዘእንበሌየ። አሁንም ያለ እኔ ምንም ምን ሌላ ባዕድ አምላክ አታምልክ። ካለ በኋላ ቁጥር ፭ ላይ ኢትስግድ ሎሙ ወኢታምልኮሙ ይላል። አትስገድላቸው ተብሏል። ይህ ስግደት የአምልኮ ስግደት ነው። አምልኮ ተገዢነትን፣ ፈሪሕን፣ አክብሮን፣ እና ሰጊድን አጠቃሎ የያዘ ቃል ነው። ራእየ ዮሐንስ ፳፪፣፲፭ ላይ እንደተገለጸው አምስቱ ውሾች ከተባሉት አንዱ "ጣዖት አምላኪ" ነው። ጣዖት አምላኪ የሚባለው እንጨት ጠርቦ፣ ድንጋይ አለዝቦ አምላኬ ነህ ፈጣሪዬ ነህ የሚልና ራሱ ለሠራው ጣዖት መሥዋዕትን የሚያቀርብ አሳዛኝ ሰው ነው። ማንኛውም ሃይማኖተኛ ከሁሉም በፊት ሊጠብቀው የሚገባ ሕግ "ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ" ያለውን ቃል ነው። እግዚአብሔርን ትቶ በሌላ ያመለከ ሰው ጣዖት አምላኪ ይባላል። ዋናው የፍቅረ እግዚአብሔር መገለጫ እግዚአብሔርን ማምለክ ነው። እግዚአብሔርን የማምለክ መገለጫው ደግሞ ተጠምቆ ቆርቦ የእርሱ የጸጋ ልጅ ሆኖ፣ ምሥጢራትን መፈጸምና መልካም ሥራን መሥራት ነው።

አንድ እግዚአብሔር አንድ አምላክ አንድ ሃይማኖት እያለ ይህ ሁሉ እምነት ከምን መጣ? ማቴ. ፲፫፣፳፭ "ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ" ተብሎ እንደተገለጸው ክፉ አስተሳሰብንና ትምህርትን ሰይጣን በሰዎች ልቡና እያሳደረ ብዙ ቤተ እምነቶች እንዲመሠረቱ ሆኗል። በተጨማሪም በጉሥዐተ ልብ (በልብ ወለድ) ሰው የራሱን መሰለኝ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ እያደረገ ቤተእምነት እስከመመሥረት ደርሷል። በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አርዮሳውያን ያደረሱት በደል የጉሥዐተ ልብ ውጤት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ትቤ ጥበብ ፈጠረኒ አብ መቅድመ ኩሉ ተግባሩ ያለውን ጥቅስ ያለ አግባብ ጠቅሶ ጥበብ ወልድ ነው። ስለዚህ ወልድን አብ ፈጠረው ብሎ የራሱን መሰለኝ የሃይማኖት አስተምህሮ አስመስሎ አቀረበ። ነገር ግን ዝቅ ብሎ ቢያየው እምቅድመ አድባር ወአውግር ወለደኒ ሲል ያገኘው ነበር። ፈጠረ ወለደ ተብሎ ይተረጎማል። ወለደም ፈጠረ ተብሎ የሚተረጎምበት ወቅት አለ። ኦሪት ዘልደት ባለ ጊዜ ኦሪት ዘፍጥረት ማለት መሆኑን ልብ ይሏል። የራስን መሰለኝ የሃይማኖት አስተምህሮ አድርጎ ማቅረብ ይህ ሁሉ ቤተ እምነት እንዲፈበረክ ምክንያት ሆኗል። ጣዖት ማምለክን ሴሩህ ጀምሮታል። ይህ ሴሩህ ብኑ የሚባል ልጅ ነበረው። በሕፃንነቱ ተቀሠፈበት። ይወደው ነበርና እንቅበረው ቢሉ ከመውደዱ የተነሣ አላስቀብርም አለ። ሲወጣ ሲገባ ልጄ ብኑ፣ ልጄ ብኑ እያለ ኀዘን ጸናበት። የሀገሩ ሰዎች ወጥቶ በሄደበት ያንን ልጅ ቀብረው እንጨት ጠርበው ጆሮ፣ አፍንጫ፣ ዓይን፣ እጅ፣ እግር ቀርጸው ቀለም ቀብተው ቀሚስ አጥልቀው በኋላው አቁመው ልጅህ ተነሣልህ አሉት። ልጄ ብኑ ነህን አለው። በዚያ በእንጨት ያደረ ሰይጣንም "እ" አለ። አምላክ ካልሆነ ተነሥቶ ተነጋገረውን? ብለው የሚያመልኩበት ሆኗል። ንጉሠ እስራኤል ዳዊት ስለጣዖታት በመዝ. ፻፲፫፣፲፫-፲፭ ላይ "አፍ አላቸው አይናገሩም። ዓይን አላቸው አያዩም። ጆሮ አላቸው አይሰሙም፣ አፍንጫ አላቸው አያሸቱም፣ እጅ አላቸው አይዳስሱም፣ እግር አላቸው አይሄዱም___" ብሎ ተናግሯል። ጣዖት የሚባሉት እንዲህ ናቸው። ሰው ያመልካቸዋል እንጂ ማንንም አልፈጠሩም። በማንም ላይም ጉዳትን አያመጡም። ደካሞች ናቸው። ሰው ዝም ብሎ ነው የሚፈራቸው።

የሰው ልጅ ጥሮ ግሮ ይበላ ዘንድ ከፈጣሪው ትእዛዝ ተሰጥቶታል። ስለዚህም ሰው በተለያዩ የሥራ መስኮች ተሰልፎ ይሠራል። ያርሳል፣ ይቆፍራል፣ ይጽፋል፣ ይደጉሳል፣ ይሮጣል፣ ቤት ይሠራል፣ ወዘተ። ይህንን ሥራውን ደግሞ በየዘመናቱ በተሠሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ያሳልጣል። ለምሳሌ በበሬ ያርስ የነበረው በትራክተር እያለ ድካሙን ይቀንሳል። ነገር ግን አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በተሠሩ ቁጥር ተፈጥሮን እና ለሰው ልጅ ጥበብን የሰጠ እግዚአብሔርን ከማመስገን ይልቅ ሰይጣናዊ አሠራር አድርጎ የማቅረብ ክፉ ልማድ አለ። ለምሳሌ በአጼ ምኒልክ ዘመን ስልክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ሲመጣ እና ንጉሠ ነገሥቱ ሲነጋገሩበት የሰሙ አንዳንድ ቄሶች ንጉሡ ከሰይጣን ጋር ተነጋገረ ብለው እንደነበር ይነገራል። ሕዝቡም ስላልተማረ የእነ ቄሴ ንግግር ለተወሰነ ጊዜ ተስማምቶት ነበር። በኋላ ዓይናማ ሊቃውንት ከንጉሡ ጋር ሲሆኑ ውሸት እየቀለለች መጣች። ብዙ አትፍረዱባቸው። ብዙ ያልተማረ ሰው ትምህርቱ ካለቀበት አላዋቂ መባልን ስለሚፈራ እርሱ የማያውቀውን ነገር ሁሉ ከሰይጣን ጋር ያያይዘዋል። በእርግጥ ትሕትና ያለው ከሆነ ዝቅ ብሎ ይማራል። ምሁራኑ ሊቃውንቱ ግን የማያውቁት ጉዳይ ከገጠማቸው አላውቀውም ይላሉ እንጂ በግምት አይናገሩም።

ስፖርት ከሳይንስ ክፍሎች አንዱ ነው። በውስጡም ብዙ ዘርፎች አሉት። ሩጫ፣ ውርወራ፣ ዝላይ፣ እግር ኳስ፣ መረብ ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ ፈረስ ጉግስ፣ ዋና እና የመሳሰሉት የስፖርት ዓይነቶች ናቸው። እነዚህ ነገሮች እንኳንስ ጣዖት አምልኮ ሊሆኑ በራሳቸው ኃጢአት ሊሆኑ እንኳ ፈጽሞ አይችሉም። ጣዖት አምልኮ የሃይማኖት ነው። ኃጢአት ደግሞ በሃይማኖት ውስጥ ያለ ሰው ሆኖ ምግባረ ጽድቅን አለመሥራት ነው። በሀገራችን ሀገራችንን በበጎ ያስጠሩ እነ አትሌት አበበ ቢቂላ፣ እነ መሠረት ደፋር፣ እነ አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ እነ ቀነኒሳ በቀለ፣ እነ ጥሩነሽ ዲባባ እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ። ሩጫ አንድ የሙያ ዘርፍ ነው። ስለዚህ በሩጫው ዓለም ያላችሁ ውድ ክርስቲያኖች ካላችሁ በርትታችሁ ሥሩና እንደቀደሙ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ አሳውቋት። እግር ኳስ አንድ የሙያ መስክ ነው። በእግር ኳስ ያላችሁ ወንድሞች ጠንክራችሁ ሥሩና ሀገራችሁን በሙያችሁ አስጠሯት። ይህ ሥራችሁ ጽድቅ ነው አንልም። ኩነኔም እንዳልሆነ ግን አስረግጨ እናገራለሁ። ቤተክርስቲያን ዘፋኝነትን ነው አጥብቃ የምትቃወመው። ስለዚህ ዘፋኞች ደግሞ ንስሓ ገብታችሁ ሌላ ሙያ ቀይሩ። ስፖርተኛ ስፖርት ሠርቶ አሥራቱን ለቤተክርስቲያን ይስጥ። አራሽም አርሶ አሥራቱን ለቤተክርስቲያን ይስጥ። የዘፋኝንና የዘማውያንን አሥራት ግን ቤተክርስቲያን አትቀበልም። መጀመሪያ ንስሓ መግባት አለባቸውና። ስለዚህ እግር ኳስም ልክ እንደ እርሻ እና ንግድ ሁሉ አንድ የሥራ