Get Mystery Box with random crypto!

__ዲድስቅልያ ክፍል ፬____ √_አንቀጽ ፲፪_√ ፫-፬:- ከክፉ ሥራ ራቁ | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

__ዲድስቅልያ ክፍል ፬____
_አንቀጽ ፲፪_√
፫-፬:- ከክፉ ሥራ ራቁ። ይኽውም መዝፈን፣ ጣዖት ማምለክ፣ ጥንቁልና ነው።
፮:- ምእመናን ከክፉዎች ማኅበር ሊለዩ አገባብ ነው።
፲፩:- ተግባረ እድን አናቋርጥ። ቸልም አንበል።
፳:- ጥበበኛ ሰው ለራሱ አላዋቂ መስሎ ይታያል።
፳፪:- ሥራ የማይሠራ ሁሉ ምግብን አይመገብ።
_አንቀጽ ፲፫_√
፲፫:- ሕፃናት ሴቶች በቤተክርስቲያን ውስጥ አይሾሙ። የፈቲውን ፆር መታገሥ አይቻላቸውምና። በወጣትነት ኃይል ዳግመኛ ወንድን ያገባሉና።
፳:- ለቆነጃጅቶች ሴቶችም የቀድሞ ባሎቻቸው ከሞቱባቸው መታገድ ባይቻላቸው ሁለተኛ ባል ያገቡ ዘንድ እንዲገባ እናዛለን።
፴:- ለሰው ሁሉ በጎ ነገርን ታደርጉ ዘንድ ይገባል።
፵፪:- ባልቴቶች ትዕግሥተኞች ነገርን የማያበዙ ክፋትና ቁጣ የሌለባቸው ይሆኑ ዘንድ አገባብ ነው።
፵፯:- ሥርዓትን ይማሩ ዘንድ የሚሹ ወደ መምህራን ሄደው ይማሩ። የምክር ቃልንም ይስሙ።
_አንቀጽ ፲፬_√
፩:- ሴቶች ያጠምቁ ዘንድ አይገባም።
፬:- ሴቶችን ያስተምሩ ይገሥጹ ዘንድ አታሰናብቷቸው። የክህነት ሥራንም አይሥሩ።
፲:- (ሴቶች) ፈጽመው ብልሆችም ቢሆኑ፣ ሃይማኖትም ቢኖራቸው፣ መጻሕፍትንም ቢያውቁ፣ ያጠምቁና ወንጌልን ያስተምሩ ዘንድ አናሰናብታቸውም።
_አንቀጽ ፲፭_√
፩:- ሕዝባዊ የክህነት ሥራን እንዳይሠራ፣ ዕጣንንም እንዳያሳርግ፣ እንዳያጠምቅ፣ በአንብሮተ እድም እንዳይባረክ፣ በረከተ ኅብስቱንም እንዳይሰጥ እናዝዛችኋለን።
፮:- ኤጲስ ቆጶሳትና ቀሳውስት ብቻ ያጥምቁ።
፰:- ቀሳውስት ዲያቆናትንና ዲያቆናዊትን፣ አናጉንስጢስንም፣ መዘምራንንም፣ በር ዘጊዎችንም እንዳይሾሙ እነሄ እናዝዛለን።
_አንቀጽ ፲፮_√
፲፩:- መበለት ለሰጧትና ለመጸወቷት ሰዎች ትጸልይ።
፲፬:- ሀብት ከሰው ዘንድ የሚሰጥ አይምሰላችሁ። የጸጋ ሀብት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
፲፱:- የዐመፅ ርግማን ባልበደለ ሰው ላይ አይደርስም። ወደ ረጋሚው ይመለሳል እንጂ።
፳፮:- ኤጲስ ቆጶስም ቢሆን ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ቢሆን ከሹማምንት ወገንም የሆነ ቢሆን ስለበረከት ፈንታ እርግማንን እንዳይወርስ እርግማን ከአፉ አይውጣ።
፴:- ዲያቆናዊት ነውር የሌለባት ሴቶችን ለማገልገል የተመረጠች ንጽሕት ትሁን።
፴፯:- ከበለሳን የተገኘ ቅብዐ ሜሮን የሃይማኖት ኃይል ነው።
፵፯:- (ዲያቆናት) ለተቸገሩት ሰዎች ማገልገልን እንቢ አይበሉ።
፶፯:- እነሆ ኤጲስ ቆጶስ በሦስት ኤጲስ ቆጶሳት ያም ባይሆን በሁለት ኤጲስ ቆጶሳት ይሾም ዘንድ እናዝዛለን።
፶፱:- ቀሳውስት፣ ዲያቆናትና ሌሎች የቤተክርስቲያን ሹማምንት ግን በአንድ ኤጲስ ቆጶስ ይሾሙ።
_አንቀጽ ፲፯_√
፩:- እናት አባት የሞቱባቸውን ልጆች ያሳድጓቸው ዘንድ ይገባል።
_አንቀጽ ፲፰_√
፫:- (ኤጲስ ቆጶሳት ሆይ) ለሚያገለግሉ ደመወዛቸውን ስጡ። የተራቡትን አብሏቸው። ድሆችን አሳድሯቸው። የታረዙትን አልብሷቸው። የታመሙትን ጠይቋቸው። የታሠሩትንም እርዷቸው።
፲:- እያለው ምጽዋትን የሚቀበል እርሱን እግዚአብሔር ይቆጣጠረዋል። የድሃውን ምግብ ነጥቋልና።
_አንቀጽ ፲፱_√
፮:- ባልቴቶችንና ድሀ አደጉን ለሚቀበሉ እግዚአብሔር በመንግሥተ ሰማያት ደስ ያሰኛቸዋል።
_አንቀጽ ፳_√
፩:- ከመሸተኛ መባን እንዳትቀበሉ ተጠንቀቁ።
፫:- ፈጣሪ እግዚአብሔር ከዝሙት ዋጋ መባ አትቀበሉ ብሏልና።
፮:- ክፉ የሚሠራና ዐመፅን የሚናገር ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የተናቀ ነው።
፲፪:- ከብዙ የኃጢአተኞች ሀብት ጥቂት የጻድቃን ሀብት ይበልጣል።
፳፮:- እግዚአብሔርን ከሚጠሉ ሰዎች መባን ተቀብላችሁ መሳቂያና መዘበቻ ከምትሆኑ ታግሣችሁ በመራብ በመጠማት ትኖሩ ዘንድ አገባብ ነው።
፳፯:- ከወንጀለኞች መባን አትቀበሉ።
_አንቀጽ ፳፩_√
፩:- አባቶች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቻችሁን አስተምሯቸው። የእጅ ሥራንም ይማሩ ዘንድ እዘዟቸው።
፭:- ልጁን የማይገሥጽ አባት አላዋቂ ነው።
፰:- (ልጆች) ወደ መሸታ ቤት ይገቡ ዘንድ አታሰናብቷቸው።
_አንቀጽ ፳፪_√
፪:- አገልጋይ ክርስቲያን ቢሆን ጌታው ከሓዲ ቢሆን በሥራው ሁሉ ይገዛለት ዘንድ አገባብ ነው። ነገር ግን ከእርሱ ጋራ በሃይማኖት አይተባበር።
√አንቀጽ ፳፫
፩:- ደናግል ሰውነታቸውን ሳይፈትኑ ይሣሉ ዘንድ አይገባም።
√አንቀጽ ፳፬
፪-፫:- በመከራ ላሉ ሰማዕታት ከገንዘባችሁ ምግባቸውን ላኩላቸው። ዳግመኛም ለሚጠብቋቸው ጭፍሮች ምግባቸውን ስጡ። በእነርሱ ላይ መከራ እንዳያጸኑባቸው።
፭:- ሰማዕት የጌታ ወንድም ይባላል።
፰:- ገንዘብ የሌላችሁ ደግሞ መከራ እየተቀበሉ ስላሉ ሰማዕታት ጹሙ።
፸፬:- ንኡሰ ክርስቲያን ቢታመም መከራንም ቢታገሥ ስለ ክርስቶስ ስም ቢሞት መከራው ስለ ጥምቀት ይሆነዋል።
++++
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፭ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው