Get Mystery Box with random crypto!

አቦ ጉራጌ (በላይ በቀለ ወያ) . . ስንቱ ሲቀልድ ፣ በብሔሩ ስም 'ተቀለደብኝ' ፥ ብሎ አያለቅስ | Belay Bekele Weya

አቦ ጉራጌ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ስንቱ ሲቀልድ ፣ በብሔሩ ስም
"ተቀለደብኝ" ፥ ብሎ አያለቅስም !
።።።
ስንቶች ሲያሾፉ ፣ ጠርተው ብሔሩን
"ተናኩኝ ብሎ " ፥ ሳይጠላ ሀገሩን
ካሾፉበት ጋር ፣ አብሮ ይስቃል
ሥራን አክብሮ ፣ ወሬን ይንቃል።
።።።
ስንቶች ሲወድቁ ፣ ስንቶች ሲነሱ
ስንቶች ሲሻሩ ፣ ስንቶች ሲነግሱ
ስንቶች እርስ በርስ ፣ሲጨራረሱ
ስንቶች በታሪክ ፣ ሲወቃቀሱ
"እንዲህ ሆኛለው "
ብሎ ማይለው ፣ ሰብኮ ጥላቻ
ሀገር ያክላል ፣ ክልሉ ብቻ !!!
አቦ ጉራጌ
።።።
ጓድ Misbah Kedir Umer እንኳ ደስ አለህ።