Get Mystery Box with random crypto!

ህግ እና መንግስት ባለበት ሀገር ላይ አንድ መርማሪ ፖሊስ ከህግ አግባብ ውጪ ያለ መጥሪያ ያለ | Belay Bekele Weya

ህግ እና መንግስት ባለበት ሀገር ላይ አንድ መርማሪ ፖሊስ ከህግ አግባብ ውጪ ያለ መጥሪያ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በግል ስልኩ እየደወለ ወደጣቢያ "ና" እያለ ቀን በቀን እየዛተና እያስፈራራኝ ነው !!! ይሄ ህጋዊ ህገ ወጥነት ፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ በየ ቦታው በየቀኑ በተለያየ ቦታ እየገጠመኝ እንኳ ከመፃፍና ሀሳቤን በነፃነት ከመግለፅ ተቆጥቤ "ሁሉም በጊዜው ያልፋል!" ብዬ ለማለፍ ብጥር እንኳ ስልጣን ህዝብን ማገልገያ እንጂ ማስፈራሪያ እንዳልሆነ ያልተገነዘቡ አንዳንድ ግለሰቦች ከህግ አግባብ ውጪ መዛቱንና ማስፈራራቱን ተያይዘውታል!!! እንግዲህ በዚህ በደል እና ጭቆና ውስጥ ሆኜ ... "መንግስት የለም ወይ? ህግ የለም ወይ? ኧረ በህግ አምላክ!" የሚል ርዕስ ያለው ግጥም ፅፌ ብለጥፍ .."ይህን ለምን ፃፍክ?" ብለው ይከሱኛል።ያለኝ አንድ ሀገር ነው!!! የት ሔጄ ልኑር?