Get Mystery Box with random crypto!

አሁን እኔ ብሞት ፣ ከኔ ምን ይቀራል? ስኖር 'ክፉ' ያለኝ 'ደግ ሰው ነበረ ' ፣ እያለ ያወራል። | Belay Bekele Weya

አሁን እኔ ብሞት ፣ ከኔ ምን ይቀራል?
ስኖር "ክፉ" ያለኝ
"ደግ ሰው ነበረ " ፣ እያለ ያወራል።
።።።
"እሱ ሰው አይደለም" ፣ ሰይጣን ነው መሠሪ"
ሲለኝ የከረመ ፣
"መልካም ሰው ነበረ ፣ መልአክ መሥሎ ኗሪ
ብሎ ቀብሬ ላይ ፣ እንባውን ይዘራል
መቼም በዚህ ሀገር
ሲኖር የተናቀ ፣ ሲሞት ይከበራል ።
* * * *
የሚጠላኝ ሁላ
ተወዳጅነቴን ፣ ቀብሬ ላይ ያወሳል
መቼም በዚህ ሀገር
ሲኖር የሚነቀፍ ፣ ሲሞት ይወደሳል
ሲኖር የተረሳ ፣ ሲሞት ይታወሳል!!!
።።።

@BelayBekeleWeya