Get Mystery Box with random crypto!

B B C አማርኛ ዜናዎች®

የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amharic_news — B B C አማርኛ ዜናዎች® B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amharic_news — B B C አማርኛ ዜናዎች®
የሰርጥ አድራሻ: @bbc_amharic_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.23K
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም ውድ የ ቻናላችን ቤተሰቦች የ እናንተን ሀሳብና አስተያየት ለመቀበል አዲሱ ቦቻችየ
ንን ይጠቀሙ ሀሳብ አስተያየቶን ያድርሱን
👉 @BBC_amharic_news_bot

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-11 10:43:55
ኢትዮጵያ እና የፋይናንስ ሴክተሯ !

በ2014 በጀት ዓመት ማለቂያ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሴክተር እውነታዎች ፦

• የባንኮች ብዛት 30

• የባንክ ቅርንጫፎች ብዛት 8,944

• ጠቅላላ የባንኮች ካፒታል (በብር) 199.1 ቢሊዮን ብር

• ጠቅላላ የባንኮች ሀብት (በብር) 2.4 ትሪሊዮን ብር

• ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ (በብር) 1.7 ትሪሊዮን ብር

• የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ብዛት 16.3 ሚሊዮን

• የዴቢት ካርድ ተጠቃሚዎች ብዛት 30.7 ሚሊዮን

• የሞባይል ገንዘብ ተጠቃሚዎች ብዛት 43.3 ሚሊዮን

• የኤቲኤሞች (ATM) ብዛት 6,902

• የፖስ ብዛት 11,760

• የኢንሹራንስ ተቋማት ብዛት 18

• የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ብዛት 40

መረጃ ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1.2K views07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 09:27:11
ነፃ የትምህርት ዕድል !

የሳንድፎርድ ኢንተርናሽናል ት/ቤት በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር በሚገኙ የመንግሥት ት/ቤቶች በመማር ላይ ከሚገኙ #በትምህርታቸውና #በፀባያቸው የተመሰከረላቸውን ተማሪዎች አወዳድሮ የነፃ ትምህርት ዕድል ለመሥጠት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አሳውቆናል።

ተወዳዳሪ ተማሪዎች ለነፃ ትምህርቱ ውድድር ለመመዝገብ ሲመጡ የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልተው የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት መግለጫ ኮፒ ይዘው መምጣት ይጠበቅባቸዋል።

1. በአ/አ ከሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተማሪ መሆን

2. ተማሪው የተወለደው እ.ኤ.አ ነሐሴ 31/2008 ድረስ 14 ዓመት የሚሞላዉ ነገር ግን 15 ዓመት በታች የሆነ ይህንንም የሚያረጋግጥ የልደት የምሥክር ወረቀት ይዘው መቅረብ የሚችሉ

3. በ2014 የትምህርት ዘመን መጨረሻ የ8 ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አማካይ ወጤት ከ95% በላይ የሆነ

4. የ7ና 8 የክፍል ትምህት ለየብቻው አማካይ ውጤቱ ከ90% በላይ የሆነ

5. ስለመልካም ሥነምግባሩ ወይም ፀባዩ ከሚማርበት ት/ቤት የጽሁፍ ማስረጃ በሳንድፎርድ ተቀባይነት ሲያገኝ ማምጣት የሚችል

6. ት/ቤቱ የሚሰጠውን የመግቢያና ቃለመጠይቅ ፈተናዎችን የተሻለ ዉጤት ማስመዝገብ

7. የወላጅ/የአሳዳጊ ሙሉ ፈቃድ ያገኘ

8. አሸናፊ የሚሆነው ተማሪ በአሥረኛ (10) ክፍል በት/ቤቱ ተመዝግቦ ለመማር ፈቃደኛ የሆነ ናቸዉ።

9. የምዝገባ ሰዓት ጠዋት 2፡30 - 6:00 ከሰዓት ከ7:30 - 9:30

መስፈርቱን ያሟሉ ተማሪዎች ነሐሴ 19/2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ለፅሁፍ ፈተና ይቀርባሉ።

ቦታ፦ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል አካባቢ በሳንድፎርድ ት/ቤት እስከ ነሐሴ 18 ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ በአካል በመቅረብ መመዝገብ ይቻላል።
811 views06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 22:23:08
#የትምህርት_እድል

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ8ኛ ወደ 9ኛ ክፍል ያለፉ ተማሪዎች አወዳድሮ ለማስተማር እንደሚፈልግ ገልጿል።

የምዝገባ መስፈርቶቹ ከታች የተዘረዘሩት ሲሆኑ መስፈርቶቹን የምታሟሉ ተማሪዎች ተመዝግባችሁ መወዳደር ትችላላችሁ።

ሀ/ የውድድር መስፈርቶች

1ኛ. ክልላዊ የ8ኛ ክፍል አማካይ ውጤት (average) (ጥሬ ማርክ) ለወንድ 78 እና ከዛ በላይ ለሴት 75 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገበ / ያስመዘገበች

2ኛ. ለተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ከፍተኛ ፍላጎት ያለው/ያላት 10ኛ ክፍል ካጠናቀቀ በኋላ በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ መቀጠል የሚፈልግ/የምትፈልግ

ለ. ዝርዝር መረጃ

• የምዝገባ ቀን ከ09/12/14 - 13/12/14
• የምዘገባ ቦታ-በሳይንስ ሼርድ ካምፓስ፡ በቀድሞው ቀዳማዊ ምኒልክ የመጀመሪያ ት/ቤት፡፡ ከአራዳ ክ/ከተማ ፊት ለፊት
• የምዝገባ ሰዓት ከረፋዱ 3፡00 - ቀኑ 10:00

ሐ/ ተወዳዳሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ

• ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ውጤት የሚገልጽ ዋናውንና 1 ፎቶ ኮፒ
• የመመዝገቢያ ብር 400
• አንድ ክላሰር ይዛችሁ ተገኙ

መ. ተጨማሪ መረጃ

• የጽሑፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን 18/12/14 ከቀኑ 7፡30 - 10፡30
• ፈተና የሚሰጥበት ቦታ በካምፓሱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው ተብሏል።

ት/ቤቱ ጎበዝ ተማሪዎች በማፍራት በሀገሪቱ ውስጥ አሉ ከሚባሉና በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናዎችም እጅግ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ያፈራ ት/ቤት ነው።

ለአብነት በ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና 78 ተማሪዎችን አስፈትኖ 42 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

በኢትዮጵያ ትልቁ ውጤት የመጣውም 659 ከዚሁ ሲሆን በት/ቤቱ ዝቅተኛ ውጤት የነበረው 529 ነበር።
899 views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ