Get Mystery Box with random crypto!

B B C አማርኛ ዜናዎች®

የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amharic_news — B B C አማርኛ ዜናዎች® B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amharic_news — B B C አማርኛ ዜናዎች®
የሰርጥ አድራሻ: @bbc_amharic_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.23K
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም ውድ የ ቻናላችን ቤተሰቦች የ እናንተን ሀሳብና አስተያየት ለመቀበል አዲሱ ቦቻችየ
ንን ይጠቀሙ ሀሳብ አስተያየቶን ያድርሱን
👉 @BBC_amharic_news_bot

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 15:12:38
ወቅታዊ ጉዳዮች ፦

- የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ አፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች የሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎች እስር፣ የነዳጅ ዘረፋና ተሸከርካሪ በኃይል የመውሰድ ጨምሮ ተቀባይነት የሌለው ጣልቃ ገብነት እየደረሰባቸው ነው ብለዋል። ዕርዳታ ለተቸገሩት ይደርስ ዘንድ ሁሉም ወገኖች የሰብአዊ ተግባራትን እንዲያከብሩ ጥሪ እናቀርባለን ብለዋል። ፓወር በዚህ መልዕክታቸው የድርጊቶቹ ፈፃሚዎችን በግልፅ አልተናግሩም። ፓወር ከዚህ ቀደም ህወሓት 150 ሺህ ጋሎን ነዳጅ ከመቐለ WFP መጋዘን መዝረፉንና ሰራተኞችን ማንገላታቱን በመግለፅ ነዳጁን እንዲመልስ ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህ መልዕክታቸው በአማራ እና አፋር ክልሎች ውስጥ ስለተፈፀሙ ድርጊቶችና ፈፃሚዎች በግልፅ ሳያብራሩ አልፈዋል።

- አሜሪካ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንቶኒ ብሊንከን በኩል የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ወታደራዊ ኦፕሬሽኖችን በአስቸኳይ እንዲያቆሙና ግጭቱን በዘላቂነት ለማስቆም የሚደረገውን ጥረት በእጥፍ እንዲያጠናክሩ ጠይቃለች። ጦርነቱ እንደገና መቀስቀሱ ​ና በዚህ ሳቢያ አደጋ ላይ የሚወድቀው ህይወት ያሳስበናል ብላለች።

- ዩናይትድ ኪንግደም መንግስት የትግራይ ኃይሎች በአስቸኳይ ከአማራ ክልል ግጭት አቁመው ወደ ትግራይ እንዲመለሱ የኤርትራ ኃይሎችም ከትግራይ እንዲወጡ ጠይቋል። ንግግር ቢጀመር ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት እንደሚቻል ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ መሰረታዊ አገልግሎት እንዲጀምር እንዲያደርግ ህወሓት ከWFP የወሰደውን ነዳጅ ለሰብዓዊ ስራ እንዲውል እንዲያደርግ ጠይቋል። ይህን ግጭት ለማስቆም ብቸኛው መንገድ ግጭት በማቆም ወደፖለቲካ ድርድር ማምራት ነው ብሏል ለዚህም የUK መንግስት የአፍሪካ ህብረትን የማሸማገል ጥረት እንደሚደግፍ አረጋግጧል።
355 views12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:11:09
ወቅታዊ ጉዳዮች ፦

1. ዛሬ ህወሓት የኤርትራና የኢትዮጵያ መንግስት በጋራ ሆነው በ4 አቅጣጫ ጥቃት ከፍተዋል ሲል ከሷል። ጥቃቱ ከፍቅያ ገብረ እስከ አደመይቲ፣ ከሰላሞ - ሽራሮ፣ ከጎቦ ፅንዓት ወደ እርዲ ማቲዎስና አዲ አሰር እና አዲ ጎሹ በከባድ መሳሪያ ጥቃት እየተፈጸመባቸው ነው ብሏል። እስካሁን ከኢትዮጵያ መንግስት ሆነ ከኤርትራ በኩል ለዚህ ክስ ቀጥተኛ ምላሽ አልተሰጠም።

2. የኢፌዴሪ መንግስት መግለጫ፦

• ሕወሐት ወረራውን እያስፋፋ መጮኹን ቀጥሏል ብሏል። ህወሓት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ገፍቶ በየአቅጣጫው በለኮሰውና ዛሬም እያስፋፋ ባለው እሳት ንጹሐን እየተገደሉ፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ፣ ንብረትም እየወደመ ነው ብሏል። ሕወሓት ከሀገር አጥፊነት ተግባሩ የማስቆም ግዴታ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ላይ መውደቁን ገልጿል።

• በሕወሓት ቡድን እየደረሱ የሚገኙ ጥፋቶችን ለማስቆም ለሰላማዊ  አማራጭ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ሁሉ እየመከኑ ባቡለበት ሁኔታ ሕወሓትን መጫን ሲገባቸው "ሁለቱም ወገኖች" በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነታው ያፈነገጡ ስለሆነ ተቀባይነት የላቸውም ብሏል።

• ሕወሓት ተደጋጋሚ የሰላም አማራጮችን በመግፋት የከፈተው ጥቃት ሃገርን እንዳይበትን፣ የመከላከያ ኃይል በሁሉም አቅጣጫ የተከፈተበትን ወረራ ከሰላም ወዳዱ ደጀን ሕዝብ ጋር በመሆን በጽኑ ጀግንነት በመከላከል ላይ ይገኛል ብሏል።

3. የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መንግስት የሀገሪቱን ሉአላዊነት ለማስከበር በሕወሓት ላይ የትኛውንም አይነት እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ዛሬ ለአምባሳደሮች፣ የሚሲዮን መሪዎችና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች በሰጡት ማብራሪያ ገልጽዋል። ከሚወሰደው እርምጃ ጎን ለጎን አሁንም #የሰላም በሮች ክፍት መሆናቸውን አሳውቀዋል።
311 views12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:10:35
#Harari #SafaricomEthiopia

በሐረሪ ክልል ፤ የ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " መለያ በተለጠፈባቸው ሁሉም መደብሮች እና ሱቆች ሲም ካርድ እና የአየር ሰዓት መግዛት ይቻላል ተብሏል።

በተጨማሪ በአራተኛ እና በሥላሴ አካባቢ ባሉት ሁለት የሽያጭ ማዕከሎቹ የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

ደንበኞች ለማንኛውም የደንበኞች ድጋፍ አገልግሎት በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጥሪ ማዕከል በተለያዩ ቋንቋዎች ፦
- በአማርኛ፣
- በአፋን ኦሮሞ ፣
- በሱማሊኛ፣
- በትግርኛ እና እንግሊዝኛ አገልግሎት የማግኘት አማራጭ ያላቸው ሲሆን የደንበኞች አገልግሎት ሠራተኞችን በ 700 ላይ በመደወል ማናገር ይቻላል።

#SafaricomEthiopia #ሐረሪ #Harari
287 views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:09:46
#SafaricomEthiopia #Harari

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ-ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በሐረሪ ክልል መጀመሩን አሳውቋል።

ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት መሆኑን ተገልጿል።

በሐረሪ ክልል የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች የሚካሔድ ሲሆን ደንበኞች በዐ7 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት ይችላሉ ተብሏል።

ደንበኞች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርዶችን የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጀመሪያ የዳታ፣ የድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶች ጥቅል እንደሚያገኙ ተገልጿል።

የደንበኝነት ማስጀመሪያ ጥቅሉ በሚያልቅበት ጊዜ ደንበኞች የአየር ሰዓት ከሽያጭ ማዕከላት ወይም መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች በመግዛት መሙላት እና አገልግሎቱን መጠቀም መቀጠል ይችላሉ።

በሐረሪ ክልል አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ እንደሚችሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሳውቆናል።

#SafaricomEthiopia #ሐረር_ክልል #Harari
318 views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 08:33:22
የቤት ኪራይ ለቀጣይ ስድስት ወራት መጨመር አይቻልም ተባለ፡፡

የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለቀጣይ ስድስት ወራት ተራዘመ፡፡

የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታዉቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በመኖርያ ቤት ተከራዮች ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራይን ማስለቀቅን የሚከለክል ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

ይህም ደንብ በተለያየ ጊዜ እየተራዘመ ላለፈው አንድ አመት ተግባራዊ ተደርጎ ቆይቷል፡፡

ስለሆነም የከተማ አስተዳደሩ አሁን ያለውን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ እና የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ከግምት ባስገባ ወቅቱን በአብሮነትና በመተሳሰብ ለማለፍ ይረዳ ዘንድ ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም ወስኗል፡፡

በመሆኑም ይህንን ክለከላ በመተላለፍ ተከራዮችን የሚያስወጡ እና የኪራይ ዋጋን የሚጨምሩ አካላት ላይ ማህበረሰቡ በ 9977 አጭር ቁጥር  ጥቆማውን ለከተማ አስተዳደሩ ማድረስ እንደሚችል አስታዉቋል፡፡
432 views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 13:58:54
ቦረና

በኦሮሚያ ፣ ቦረና በድርቅ ሳቢያ በርካታ ወገኖቻችን ዛሬም ችግር ላይ ናቸው። እነዚህ ወገኖች በድርቁ ምክንያት ያላቸውን ከብቶች ስላጡ እጅግ በጣም ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነው የሚኖሩት።

በድርቅ ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ያሉ ወገኖች ሰሞኑን ቃላቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ ሰጥተው የነበረ ሲሆን ያሉበት ሁኔታ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው።

(በድብሉቅ ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች)

የ7 ልጆች እናት ወ/ሮ ጂሎ ጉራቻ ፦

" የዘንድሮው ድርቅ የነበሩንን ከብቶች እና ሁሉንም ንብረቶችን ነው ያወደመብን። ባዶ እጃችንን ስንሆን ወደዚህ መጣን ፤ እዚህ ከመጣን በኃላ በምግብ እና ውሃ እጥረት እየተቸገርን ነው። በተለይም ህፃናት ነፍሰጡር ሴቶች፣ አዛውንቶች በምግብ እጥረት እየተጎዱ ናቸው። እኛ እዚህ ከሰፈርን ከ6 ወር በላይ ሆኖናል። በመጠለያው በጣም ብዙ ቤተሰቦች ነው ያሉት። በቆይታችን አንዴ ብቻ ነው ለተወሰኑ ቤተሰቦች የምግብ ድጋፍ የተሰጠው እንጂ ምንም አላገኘንም። ስለዚህ በጣም ችግር ላይ ውስጥ ነው ያለነው። "

የ6 ልጆች አባት ዳለቻ ዲዳ ፦

" ምንጠጣው ውሃ በጣም የቆሸሸ ነው። እንስሳት ሲሞቱ ከሚጣሉበት ነው ልጆቻችን የሚቀዱልን። በዛ ላይ የመፀዳጃ ቦታም የለንም። እንዲሁ በበሩ ደጃፍ ነው ይህ ሁሉ በዚህ የሰፈረው ህዝብ የሚፀዳዳው ስለዚህ የበሽታ ወረርሽኝ ፍራቻ አለብን። ሌላው የመጠለያ ቦታና ላስቲክ ሰጥተውናል። ይህ ላስቲክ #ብርድ የሚከላከል አይደለም። እናም በጣም ችግር ውስጥ ነን። "

የልጆች እናቷ ትዬ አደንጌ ፦

" #ብርዱ_በጣም_አስቸጋሪ_ነው። ለምግብ ፍለጋ ነው ከእሳት አጠገብ የምንነሳው። በዛ ላይ የምንለብሰው ልብስ የለንም። በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። "

ያንብቡ : https://telegra.ph/Borana-08-23 #ገልሞ_ዳዊት
684 views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 21:22:12
# እንድታውቁት


በነገው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት የሚወስዱ መንገዶች በስራ ምክንያት ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ፡፡


ነገ ነሃሴ 15 ቀን 2014 ዓ/ም ከተለያዩ አቅጣጫዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምባሳደር አካባቢ አዲስ ወዳስገነባው ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ የሚወስዱ መንገዶች በስራ ምክንያት ከለሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት
•  ከሴንጆሴፍ መብራት ወደ ሃራምቤ ሆቴል
•  ከኢሚግሬሽን ወደ  ፍልውሃ
•  ከፍል ውሃ ወደ ኢትዮጵያ ሆቴል
•  ከጤና ሚኒስቴር ወደ ፍልውሃ
•  ከለገሃር ወደ ፍልውሃ
  የሚወስዱት መንገዶች ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ በመገንዘብ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚያመላክቷቸው አቅጣጫ መሰረት ሌሎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡
859 views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 14:26:44
#DigitalLottery

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስጀመረው " አድማስ " የተሰኘው ድጂታል ሎተሪ የመጀመሪያው ዙር እጣ ትላንት ማውጣቱን አሳውቋል

የዲጂታል ሎተሪ ዕጣው ቀጣይነት እንዳለው የገለፀው አስተዳደሩ የሁለተኛ ዙር  ዕጣው  መስከረም 11 ቀን 2015 የሚወጣ መሆኑን ገልጿል።

የአድማስ ዲጅታል ሎተሪ በአንደኛ ዕጣው 1.5 ሚሊዮን ብር፣ በሁለተኛ 800 ሺህ ብር፣ በሶስተኛ 350 ሺህ ብር ጨምሮ ሌሎችም የገንዘብ ዕጣዎችን ያካተተ ነው።

ከብሄራዊ የሎተሪ አስተዳደር እንዳገኘነው መረጃ ዕጣው በ605 ላይ ማንኛውም ፊደል በመላክ ወይም በቴሌብር ወደ *127# በመደወል በ3 ብር ነው የሚቆረጠው።

(ከላይ በትላትናው ዕለት የወጣው የመጀመሪያ ዙር ዕጣ #ሙሉ የባለዕድለኞች ቁጥር ተያይዟል)                            
704 views11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 07:49:18
#ExitExam

የትምህርት ጥራት #ፈተና_በመስጠት ብቻ ይረጋገጣል ?

ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀመር ይታወቃል።

ለመሆኑ ፈተና በመፈተን ብቻ የትምህርት ጥራት ማምጣት ይቻላል ? ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ምላሽ አለው።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) የተናገሩት ፦

" የትምህርት ጥራት ፈተና ብቻ በመስጠት የሚሳካ ፤ የሚረጋገጥ ነገር አይደለም።

በአጠቃላይ ግን በትምህርት እና ስልጠና ዘርፉ በተለይም በትምህርቱ ዋና ችግር አለ ተብሎ የተለየው ዋና የትምህርት ሴክተሩ ስብራት ነው ተብሎ የተለየው ትምህርታችን ጥራትም ተገቢነትም ጎሎታል።

ስለዚህ አስመርቀን የምናስወጣው በሙሉ ባይባልም የጥራት ፣ የብቃት ችግር አለበት ይሄንን መፍታት ያስፈልጋል።

ለዚህ የሚሆን በሁሉም ደረጃ ከግብዓትም ጋር ከሂደቱም ጋር የሚያያዝ እንደዚሁም ውጤቱን ከማረጋገጥ ጋር የሚያያዝ ስራዎች መሰራት አለባቸው ተብሎ በመንግስት ቁልፍ የሪፎርሞች ተጀምረዋል አንደኛው ከመውጫ ፈተና ጋር የሚያያዝ ነው።

ይሄ የመውጫ ፈተና በዋናነት የሚመለከተው የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃንን ነው ሁለተኛ ዲግሪ እና ሌሎችን አይመለከትም የሚጀምረው በ2015 ሰፋ ብሎ ነው እንጂ ከዚህ በፊትም የተጀማመሩ ስራዎች አሉ የተጀመሩ ፕሮግራሞች አሉ።

ዋናው ቁም ነገሩ በግብአት ደረጃ ጥራቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል የምሩቁን ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን የመማር ማስተማር ሂደቱ ጥራትን በሚያረጋግጥ መልኩ መምራት እና መስጠት ያስፈልጋል።

በጥሩ ግብዓት ከተደገፈ እና ጥሩ ሂደት ካለው በውጤቱ ማረጋገጥ ይገባል ከሚል መነሻ የተጀመረ የሪፎርም ስራ ነው "
700 views04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 12:41:53
#MoE

" የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 /2015 ዓ/ም ጀምሮ በ2 ዙር እንዲሰጥ ታቅዷል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ2ዐ14 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ #በሁለት_ዙር እንዲሰጥ መታቀዱን በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተፈርሞ ለ42 ዩኒቨርሲቲዎች በተላከውን እና bbc_amharic ትክክለኛነቱን ባረጋገጠው ደብዳቤ መመልከት ችለናል።

በዚሁ መሠረት ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ዩኒቨርስቲዎች ፦

1. ምንም አይነት የመደበኛ ተማሪ በግቢ እንዳይኖር እንዲያደርጉ፤

2. በቀጣይ በሚገለጸው ተማሪ ቁጥር ልክ ምግብ እንዲቀርብ ዝግጅት እንዲያደርጉ፤

3. ለፈተናዎች ማቆያ ቦታ እንዲዘጋጅ እና

4. የፈተናውን አሰጣጥና ደህንነት የሚቆጣጠር በፕሬዚዳንት የሚመራ ዋና ግብረ-ኃይልና በየካምፓሶቹ በዲን /ካምፓስ ኃላፊ የሚመራ ንዑስ ግብረ-ኃይል እንዲያደራጁ መልዕክት ተላልፎላቸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የ2ዐ15 የአካዳሚክ ካላንደር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወቅት (ከመስከረም 28 - ጥቅምት 17) ታሳቢ በማድረግ እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አሳስበዋል።
1.0K views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ