Get Mystery Box with random crypto!

#DigitalLottery የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ | B B C አማርኛ ዜናዎች®

#DigitalLottery

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስጀመረው " አድማስ " የተሰኘው ድጂታል ሎተሪ የመጀመሪያው ዙር እጣ ትላንት ማውጣቱን አሳውቋል

የዲጂታል ሎተሪ ዕጣው ቀጣይነት እንዳለው የገለፀው አስተዳደሩ የሁለተኛ ዙር  ዕጣው  መስከረም 11 ቀን 2015 የሚወጣ መሆኑን ገልጿል።

የአድማስ ዲጅታል ሎተሪ በአንደኛ ዕጣው 1.5 ሚሊዮን ብር፣ በሁለተኛ 800 ሺህ ብር፣ በሶስተኛ 350 ሺህ ብር ጨምሮ ሌሎችም የገንዘብ ዕጣዎችን ያካተተ ነው።

ከብሄራዊ የሎተሪ አስተዳደር እንዳገኘነው መረጃ ዕጣው በ605 ላይ ማንኛውም ፊደል በመላክ ወይም በቴሌብር ወደ *127# በመደወል በ3 ብር ነው የሚቆረጠው።

(ከላይ በትላትናው ዕለት የወጣው የመጀመሪያ ዙር ዕጣ #ሙሉ የባለዕድለኞች ቁጥር ተያይዟል)