Get Mystery Box with random crypto!

#Breaking የአውሮፓ ህብረት ከሩሲያ ጋር የነበረውን “የቪዛ ማመቻቸት ስምምነት” ሙሉ በሙሉ ለ | B B C News አማርኛ™

#Breaking
የአውሮፓ ህብረት ከሩሲያ ጋር የነበረውን “የቪዛ ማመቻቸት ስምምነት” ሙሉ በሙሉ ለማቆም ወሰነ!!

ውሳኔው የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ በህብረቱና እና በሩሲያ መካከል የነበረው “የቪዛ ማመቻቸት ስምምነት” ለማቆም ሚያስችላቸውን እርምጃ ለመውሰድ ላለፉት ሁለት ቀናት በቼክ ሪፐብሊክ ከመከሩ በኋላ የተደረሰ ስምምነት ነው ተብሏል፡፡

ሚኒስተሮቹ በውይይታቸው ከሩሲያ ወደ አጎራባች ግዛቶች የሚደረጉ የድንበር ማቋረጦች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ትኩረት ሰጥተው የተመለከቱት አንኳር ነጥብ እንደነበር የአውሮፓ ህብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል አስታውቋል፡፡ሚኒስትሮቹ የድንበር ማቋረቱ ሁኔታ በአውሮፓ ከፍተኛ የሆነ ደህንነት ስጋት መደቀኑን በተመለከተ መወያየታቸውም ተገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት የአውሮፓ ህብረት ከሩሲያ ጋር የነበረውን “የቪዛ ማመቻቸት ስምምነት” ሙሉ በሙሉ ለማቆም መወሰኑ ጆሴፕ ቦሬል ከደቂቃዎች በፊት በትዊተር ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ ይፋ አድርገዋል፡፡

@bbc_amharic1