Get Mystery Box with random crypto!

ወለጋ በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ አገምሳ ከተማ ትናንት ከማለዳ ጀምሮ ታ | B B C News አማርኛ™

ወለጋ

በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ አገምሳ ከተማ ትናንት ከማለዳ ጀምሮ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ 55 ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ!!

የአከባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ለአንድ ዓመት ያህል የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የአከባቢውን ፀጥታ ሲያስከብሩ ነበር። ይሁንና ባለፈው ዕሁድ ነሐሴ 22 ቀን፣ 2014 የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከከተማዋ መነሳታቸውን ተከትሎ የተለያዩ ስያሜ ያላቸው ታጣቂዎች በከተማዋ መፈራረቃቸውን ነው የዐይን እማኞች የገለጹት።

የአይን እማኞቹ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት «መንግስት ‘ሸኔ’ ያላቸው “የኦሮሞ ነጻነት ጦር” ሰኞ ጠዋቱን ገብተው ከተማዋን ተቆጣጠሩዋት» ብለዋል።ታጣቂዎቹ ከተማዋ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መንቀሳቀስ ከጀመሩ በኋላ ወደ 59 መሳሪያ ከማህበረሰቡ አስፈትተው በዚያው ሰኞ ቀን ከተማዋን ለቀው ወጥተዋል፡፡

“ትናንት ማክሰኞ ጠዋት ደግሞ ፋኖ ነን ያሉ የታጠቁ አካላት ወደ ከተማዋ ገብተው ከኦነግ ጋር አብራችኋል በሚል በመደዳው ከተማዋ ላይ ተኩስ በመክፈታቸው ከ15 ሺህ የማያንሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል” ነው ያሉት፡፡

ከትናንት ማታ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የ55 ሲቪል ዜጎች አስከሬን መቅበራቸውንና የ32 ሰዎች አስከሬን በየጫካውና በየገደሉ እየፈለግን ነው” ሲሉም የችግሩን ስፋት አስረድተዋል፡

(ምንጭ፣ የጀርመን ድምፅ/Dw)
@bbc_amharic1