Get Mystery Box with random crypto!

ህወሓት ወልዲያን ተቆጣጥሯል የሚባለዉ ሀሰተኛ ነዉ የወልዲያ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ የ | B B C News አማርኛ™

ህወሓት ወልዲያን ተቆጣጥሯል የሚባለዉ ሀሰተኛ ነዉ

የወልዲያ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ

የህወሓት ሃይል ወልዲያ ከተማን ተቆጣጥሯል እየተባለ በተለያዩ ሚዲያዎች የሚነዛው ወሬ ሀሰት ነው ሲል የወልዲያ ከተማ መስተዳድር አስታውቋል።

የወልዳያ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ የሆኑት ዶ/ር ዳዊት መለሰ ከተማዋ በጠላት ቁጥጥር ስር አለመውደቋን እና ሰላም መሆኗን ለሁሉም ማህበረሰብ መግለፅ እወዳለሁ ሲሉ በመግለጫቸው ተናግረዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ጥምሩ ሃይሉ ከቆቦ ከተማ ለቆ መውጣቱን መነሻ በማድረግ ወደ ከተማችን ብዙ ማህበረሰብ በመፍለሱና ሲዋጋ የነበረው የመከላከያ ሰራዊት ወደ ወልዲያ ከተማ መምጣቱ ተከትሎ ማህበረሰባችን በትላንትናው ዕለት ትንሽ የተረበሸ ቢሆንም ከትላንትና ጀምሮ ሁላችንም በጋራ በመረባረብ ማህበረሰባችን እንዲረጋጋና ሰላሙ ወደነበረበት እንዲመለስ እየሰራን ነው ብለዋል።

ከተማዋ ሰላም መሆኗንና በአሁኑ ስአት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ የአማራ ልዩ ሃይል ፍኖና ሚሊሻ በጥምረት በግንባር እየተዋደቁ በመሆኑ ከከተማዋ ማህበረሰብ በተጨማሪም መላው የሰሜን ወሎ ህዝብ የክልሉና አጠቃላይ የኢትዮጽያ ህዝብ ለጥምር ጦሩ ደጀን እንዲሆን ጥሪ ማቅረባቸውን ብስራት ከከተማ መስተዳድሩ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

@bbc_amharic1