Get Mystery Box with random crypto!

' አስክሬኑ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል ተልኳል ' - ፖሊስ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በዛሬው | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

" አስክሬኑ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል ተልኳል " - ፖሊስ

ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

እንደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ከሆነ ፤ ድምፃዊው ዛሬ ጠዋት ላይ ሕመም ተሰምቶት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚኩራ ክ/ከተማ ወደ ሚገኝ አንድ የሕክምና ማዕከል ለሕክምና መሄዱና ሕክምና ማድረጉን ከቆይታ በኋላም ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል።

ማዲንጎ ምንም ዓይነት አካላዊ ጉዳት እንዳልነበረበት ጓደኞቹ በተገኙበት ቢረጋገጥም አስክሬኑ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል መላኩን ፖሊስን ዋቢ አድርጎ ኢብኮ ዘግቧል።

የድምፃዊው ወዳጆች በበኩላቸው ፤ ማዲንጎ ህመም ተሰምቶት እራሱ መኪናውን እያሽከረከረ ወደ ህክምና ስፍራ መሄዱን ከዛ በኃላ ህይወቱ እንዳለፈ ጠቁመዋል።
======{{{{================
ቀሪ የዛሬ ረፋድ መረጃዎች ከስር ባለው ሊንክ ዩቱብ ላይ ተጭኗል