Get Mystery Box with random crypto!

➪ ዓይነ ጥላና የዝሙት መንፈስ ይህንን ጠባይ ከልጅነታቸው ጊዜ ጀምሮ በማውረስ እስከ አሁን ሕይወታ | " አውደ ገሀድ "

➪ ዓይነ ጥላና የዝሙት መንፈስ ይህንን ጠባይ ከልጅነታቸው ጊዜ ጀምሮ በማውረስ እስከ አሁን ሕይወታቸውን በማቃወስ የሚጫወትባቸው አሉ፡፡ የዚህ አንዱና ዋነኛው ችግር የተፈጥሮን ሩካቤ ሥጋን ሳያውቁ ግለ ወሲብን በማጣጣም፣ ነገ በትዳር መሀል ባለው ሕገ ሩካቤ ጣዕም ይቸገራሉ፡፡ አጋንንቱም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የተፈጥሮ ሩካቤ ጣዕምን ያጠፋባቸዋል፡፡

➪ ሁለተኛ የወጣቶች ግለ ወሲብ ነው፡፡ ይህም ወጣቶች በወሲብ ፊልም፣ በመጠጥ ፣ በሱስ እና በሌሎችም ነገሮች በመገፋፋት አጋንንት ተጨምሮበት የሚፈጽሙት ግለ ወሲብ ነው፡፡ ይህ አብዛኛውን ጊዜ ዓይነ ጥላ ሴቷን ከወንድ፣ ወንዱን ከሴት አላስቀርብ እያለ የሚገረግርባቸው ወጣቶች የሚፈጽሙት ነው፡፡

➪ ራሳቸውን ከተቃራኒ ጾታ በማራቅ ደስታን ለማግኘት ዓይነ ጥላቸው በግለ ወሲብ እንዲጠቁ እና ራሳቸውን እንዲደብቁ ያደርጋቸዋል፡፡ እንዲሁም የፍትወት እሳት ድንገት ሲያቃጥላቸው ለማብረድ፣ እርካታን ለማግኘት የሚያውቁትን ሰው በሕሊና በማሰብ፣ በምስል በመከሰት ይፈጽማል፡፡

➪ በነገራችን ላይ አንድ ሰው ግለ ወሲብ ሲፈጽም ከሁለት አካል ጋር ነው የሚፈጽመው፡፡ አንደኛው ከራሱ ጋር ሲሆን ከራስ ጋር በራስ አካል ግል ወሲብ መፈጸም ግብረ ሰዶማዊነት ነው፡፡ ሁለተኛው የምናውቃቸውንና የማናውቃቸውን በምናብ የሚታዩ ነገር ግን የማይጨበጡ ሰዎችን እያሰብን መፈጸም ማለት ከሰይጣን ጋር ግል ወሲብን ፈጸምን ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ግለ ወሲብ አደገኛ ኃጢአት እና ርኩሰት የሆነው፡፡

➪ ሦስተኛ የባለ ትዳሮችና የእጮኛሞች ግለ ወሲብ ነው፡፡ ባል እና ሚስት፣ እጮኛሞች በሥራ ምክንያት ሲራራቁ፣ ሲጣሉ፣ ሲኳረፉ፣ ሲለያዩ የሚፈጽሙት ነው፡፡ ይህ ደግሞ አጋንንቱ የጸብ ወይም የጥል ጊዜያቸውን ለማስረዘም እና ሩካቤያቸውን ለማሰልቸት ይጠቀምበታል፡፡

➪ አንዳንዴም ባለ ትዳሮች ከትዳራቸው ውጪ ያለን ሰው በሕሊና ፣ በምናብ በማሰብ ይፈጽሙታል፡፡ ይህ ድርጊት ደግሞ ከእውነተኛው ዝሙት ልዩነት የለውም፡፡ አንዳንዴም ባለ ትዳሮች እዛው በተኙበት አልጋ ላይ ከሁለት አንዳቸው በራሳቸው መንገድ ግለ ወሲብን ይፈጽማሉ፡፡

➪ አራተኛ ሰዎች ሰይጣንን ያስለመዱት ግን ሰይጣን መልሶ የሚጫወትባቸው ግለ ወሲብ ነው፡፡ ይህም ሰይጣንና የእኛ አባቶች የማያውቁት በዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂ የሚፈጸም ግለ ወሲብ ነው፡፡ አንደኛው በስካይ ፒ፣ በዋትስ አፕ፣ በቴሌ ግራም ወዘተ/ በቪዲዮ እየተያዩ/ የሚፈጸም ግለ ወሲብ ነው፡፡ ከእውነተኛው ሩካቤ ብዙም የማይለይ ነው፡፡ እውነት የሚያስመስለው ሁለቱም እየተያዩ ስለሚፈጽሙ ደስታውና እርካታው የገሀዱን ሩካቤ ይመስላል፡፡

➪ ሁለተኛው ሰይጣን የማያውቀው ግን እኛ ያስለመድነው ፎን ሴክስ እና ቻት ሴክስ የሚባል ነው፡፡ ስለ እውነት እናውራ ከተባለ ፎን ሴክስ ፣ ቻት ሴክስ እና በቪዲዮ እየተያዩ የሚፈጸም ግለ ወሲብ እኛ ሰይጣንን ያስለመድነው እንጂ እሱ እኛን ያስለመደን አይደለም፡፡

➪ በተለይ ፎን እና ቻት ሴክስ ከምናውቃቸውና ከማናውቃቸው ሰዎች ጋር የሚፈጸም ስለሆነ እራስን በእግዚአብሔር ፊት ማርከስ እና ማስናቅ ካልሆነ በስተቀር በራሳችን የምናመጣው ጣጣ ነው፡፡
ተወዳጆች ሆይ ዓይነ ጥላና የዝሙት መንፈስ ውስጣችን ካለ ይህ ክፉ ድርጊት እንደ ኮሶ በመጣባት ለጸያፍ ሕይወት ይዳርገናል፡፡

➪ የዚህ ድርጊት መጨረሻው ደናግሎች ድንግልናቸውን፣ ቅድስናቸውን፣ ንጽሕናቸውን ያሳጣል ያጎድፍባቸዋል፡፡ ወጣቶችንና ባለ ትዳሮችን ደግሞ ከተፈጥሮ ሩካቤ በማስፈንገጥ የሞራል ውድቀት ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ ወንዶችም በተለይ ሴቶች ‹‹በግለ ወሲብ ድንግልናዬ ይጠፋልን? ግለ ወሲብ ፈጽሜ በተክሊል ማግባት እችላለሁን?›› የሚሉት የፍርሃት እና የጭንቀት ጥያቄ ኃጢአታችን የወለደው ነው፡፡

➪ አንድ ሴት በእጇ ግለ ወሲብን ፈጽማ ድንግልናዋን አጥታ ድንግል ነኝ ማለት ትችላለችን? ድንግልና ለመጥፋት የግድ በወንድ ብልት መሆን አለበት? ወንዶችስ ድንግልናችሁን ለማጣት የግድ ከሴት ጋር ግንኑነት ማድረግ አለባችሁ? ወይስ ድንግልና የሚጠፋው በሰው የመራቢያ አካል ብቻ ነው?

➪ ወዳጆቼ በግለ ወሲብ ምከንያት በተለይም በወንዶች ላይ ዘርን ያለቦታው ማፍሰስን ያስከትላል፡፡ ይህ ደግሞ ትልቅ ኃጢአት ነው፡፡ ለዛውም ኃጢአተ አውናን ነው፡፡ ብዙዎች እርግዝናን ከመከላከል ጋር በማያያዝ የሚፈጽሙት ተግባር ነው፡፡ ነገር ግን ተግባረ አውናን በመሆኑ ያስቀጣል፡፡ የከበረውን የወንድ ዘር ያለ ቦታው ማፍሰስ ተገቢ ስላልሆነ፡፡

➪ ዘርን በግለ ወሲብ ማፍሰስ በወገባችን ያለን ልጅ በሜዳ ላይ እንደመጣል ነው፡፡ ሆን ተብሎ ዘርን ማፍሰስ ትልቅ ኃጢአት ነው፡፡ በግለ ወሲብ ጊዜ ዘርን ማፍሰስ የእርካታ ምልክት ቢሆንም በእኛ ደስታ ውስጥ ማለትም በሚፈሰው ዘር ውስጥ ያሉት ልጆች ናቸው፡፡

➪ የሚያሳዝነው ወልደን ካሳደግናቸው ልጆች ይልቅ ዘርን ከማሕጸን ውጪና በግለ ወሲብ በማፍሰሳችን የማናውቃቸውና የበተንናቸው ልጆች ይበልጣሉ፡፡ አንድ ወዳጄ ግለ ወሲብ ሰልችቶት ‹‹እስከ ዛሬ በግለ ወሲብ ያለቦታው ያፈሰስኩት ዘሬ የአንድ ወረዳ ሕዝብ ያክላል›› ያለኝ ይገርመኛል፡፡

➪ ወዳጆቼ የሰው ልጅ ዘር በእግዚአብሔር ዘንድ ክብር ነው፡፡ እግዚአብሔር ልጆችን በማሕጸን ለመፍጠር የሚጠቀምበት አንዱ የሰው ልጅ ዘር ነው፡፡ ይህ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ጥበብ የሚገለጥበትን የሰው ዘር ያለ ቦታው ማፍሰስ ተገቢ አይደለም፡፡ አባቶቻችን ይህን ድርጊት ‹‹ኃጢአተ አውናን›› በማለት ይገልጹታል፡፡

➪ የይሁዳ ልጅ ዔር ትዕማር የምትባል ልጅ አግብቶ ይኖር ነበር፡፡ የይሁዳ ልጅ ዔር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ ክፉ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ዔርን ቀሠፈው ሞተም፡፡ ይሁዳም የዔርን ወንድም ልጁ አውናንን ‹‹ወደ ወንድምህ ሚስት ግባ፣ አግባትም፣ ለወንድምህም ዘር አቁምለት›› አለው፡፡

➪ አውናንም እንደ ወንድሙ ዔር ክፉ ነበርና ለወንድሙ ዘር እንዳይተካለት ከትዕማር ጋር ሩካቤ ሥጋ ሲፈጽም ዘሩን ከማሕጸንዋ ውጪ በምድር ላይ ያፈሰው ነበር፡፡ በማሕጸን ፅንስን የሚጠቀልለው እግዚአብሔር የአውናንን ተንኮልና ግፍ ተመለከተ፡፡ በአስጸያፊ ድርጊቱ እግዚአብሔር አውናንን ቀሠፈው እንደ ወንድሙ ዔር ሞተ፡፡ /ዘፍ 38÷6-10/

➪ እግዚአብሔር በሐዲስ ኪዳን ንስሐን ባይሰጠን፣ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ባይታረቀን ኖሮ ዘርን ከማሕጸን ውጪና በግለ ወሲብ እያፈሰስን፣ ዘራችንን ያለ ቦታው ስናውለው፣ ስንጥለው እንደ አውናን በተቀሠፍን ነበር፡፡ ምህረቱ እና ቸርነቱ ይዞን ይኸው ከነ በደላችን አለን፡፡

➪ በዓለማችን ላይ በሕይወት ካሉት የሰው ልጆች ይልቅ የመፈጠር ዕድል እያላቸው ግን ባልባሌ ቦታ በሚፈስ ዘር ልጆች የመሆናቸው ዕድል የተጨናገፉ ይበልጣሉ፡፡ ስለዚህ ስንት ጳጳሳት፣ አገር መሪዎች፣ ለወገንና ለአገር የሚጠቅሙ ሰዎች የሚሆኑትን ዘርን ያለ ቦታው በማፍሰስ ምክንያት እያጠፋን ስለሆነ ከዚህ ድርጊት ልንታቀብ ይገባል፡፡

➪ ለዚህም ነው እኛን፣ ያልተቀሠፈውና እግዚአብሔር የታገሰው ትውልድ ያልኩት፡፡ ምክንያቱም አውናን ተፈጥሯዊ ሩካቤን እየፈጸመ በተንኮሉ እና በክፋቱ ዘሩን ከማሕጸን ውጪ ያፈስ ስለነበር ነው እግዚአብሔር የቀሠፈውና የሞተው፡፡ እኛ ግን ተፈጥሯችን ባልሆነና ለባሕርያችን የማይስማማውን ግለ ወሲብን በእጃችን እየፈጸምን አለመቀሠፋችን እግዚአብሔር የንስሐ ዕድል እየሰጠንና ለንስሐ እያጨን መሆኑን ያስረዳል፡፡ ‹‹ኃጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኃጢአተኛው ይሞት ዘንድ አልፈቅድም›› ያለው ለዚህ