Get Mystery Box with random crypto!

አሳሳቢ ጉዳይ ስለሆነ በድጋሜ የቀረበ ርዕሰ ጉዳይ .............................. | " አውደ ገሀድ "

አሳሳቢ ጉዳይ ስለሆነ በድጋሜ የቀረበ ርዕሰ ጉዳይ
.................................................

#_ግለ_ወሲብ_በወንዶች_እና_በሴቶች_ላይ!

#_ግለ_ወሲብ_መንፈሳዊ_እና_ሥጋዊ_ጉዳቶቹ!

#_በግለ_ወሲብ_ድንግልናችን_ይጠፋልን?

ግለ ወሲብ መፈጸም ከራስ ጋር ግብረ ሰዶም መፈጸምና ከሰይጣን ጋር ግንኙነት ማድረግ ነው!

/ኃጢአተ አውናን/

/ያልተቀሠፈው እግዚአብሔር የታገሰው ትውልድ/

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ሼር በማድረግ በዚህ ችግር ለሚሰቃዩት አድርሱ!

➪ ተወዳጆች ሆይ በሰው ልጆች ሕይወት ጥንታዊ ኃጢአት ከሆነው አንዱ ግለ ወሲብ ነው፡፡ ግለ ወሲብ በሰው ልጆች ዘንድ መቼ እንደተጀመረ ጥንታዊ የታሪክ ዳራውን ስናይ ቀደምት ጀማሪዎቹ ሮማዎች ናቸው፡፡ ዘመኑም ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 4000 ዓመተ ዓለም ገደማ ነው፡፡

➪ ግለ ወሲብ በሮማ ኢምፓየር በዓለም ላይ እጅጉን እንደተስፋፋ የታሪክ መዛግብት ይነግረናል፡፡ ከሮማ በመቀጠል ግብጾች ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 3000 ዓመተ ዓለም እንደ ጀመሩ ተመዝግቧል፡፡ ጥንታውያን ሮማዎችም ሆኑ ግብጾች ግለ ወሲብን ከማህበራዊ እድገታቸው ጋር በማያያዝ ለፍትወት ማብረጃ እና ለወሊድ መቆጣጠሪያ ይጠቀሙበት ነበር፡፡

➪ ይህንን ያወቀው ቅዱስ ጳውሎስ በሮም ለሚኖሩ ክርስትያኖች እንዲማሩበት እንዲጠነቀቁበት ‹‹ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የማይገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባ ለወጡ፤ወንዶቹ ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ›› በማለት ጽፎላቸዋል፡፡ /ሮሜ 1÷26-27/

➪ ልብ ካልን ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን መልእክት የጻፈው ከጥንት ጀምሮ በሮም ግለ ወሲብና ግብረ ሰዶም ስለ ተስፋፋ ክርስቲያኖች ከዚህ ጸያፍ ድርጊት እንዲታቀቡ ለማሳሰብ እንደ ሆነ ግልጽ ነው፡፡ አጋንንት ግለ ወሲብን ገና የሰው ልጆች ተፈጥረው በአግባቡ መብዛት ባልጀመሩበት ዘመን ነው ወደ ሕይወታችን ያሰረጸው፡፡ በዚህ መልኩ ሰይጣን ያመጣውን፣ለሰዎች ያስለመደውን ግለ ወሲብ በዘመናችን በማስፋፋት ዛሬ ላይ አድርሶታል ፣ ብዙዎችንን አሰቃይቶበታል እያሰቃየንም ነው፡፡

➪ ተወዳጆች ሆይ ግለ ወሲብ ማለት ተፈጥሯችን ባልሆነ መልኩና መንገድ እርካታን ለማግኘት የምንጠቀምበት የሰይጣን ወጥመድ ነው፡፡ ድርጊቱም የራስን አካል በራስ አካል /እጅ፣ቁስ ወዘተ/ ማርካት ነው፡፡ ግለ ወሲብ በወንዶችም በሴቶችም ላይ ይጸናል፡፡ ግለ ወሲብ በሁለት መንገድ ወደኛ ይመጣል፡፡ አንደኛው በርኩሳን መናፍስት እንደ ዓይነ ጥላና እንደ ዝሙት መንፈስ ባሉ ይመጣል፡፡

➪ ሁለተኛው በምናያቸው ፊልሞች ፣ በምናነባቸው መጻሕፍትና መጽሔት፣ ዘልማድ በምናደርጋቸው ትእይንቶች ይመጣሉ፡፡ ግለ ወሲብ ከልጅነት እስከ ወጣትነት ባለ እድሜ ውስጥ የሚጠናወት አስከፊ ተግባር ነው ፤ ልዩ ልክፍትም ነው፡፡ ምክንያቱም ግለ ወሲብን ወንዶቹም ሴቶቹም ከለመዱት በቀላሉ ለመላቀቅ ይቸገራሉ፡፡ ለብዙዎች ግለ ወሲብን ከመተው ሺሻን መተው ይቀላቸዋል፡፡

➪ መንፈሳዊ ነን የሚሉትም በዚህ ችግር ክፉኛ ይጠቃሉ፡፡ ይህ ድርጊት እግዚአብሔር ቆርጦ ካልጣለልን በስተቀር አንዳንዱቹ በምክር፣ በንስሐ፣ በጸበል መተው ይቸገራሉ፡፡ ድርጊቱም እንደ ኮሶ ሲጣባ፣ ግራ የሚያጋባ ሕይወት ውስጥ ይከተናል፡፡

➪ ሌላ ችግሩ ግለ ወሲብን በእጁ መፈጸም የጀመረ ሰው ምናልባት ትቶት ወደ ትዳር ዓለም ውስጥ ሲገባ ትልቅ ችግር ይገጥመዋል፡፡ እራስን በራስ ማወሰብ ለምዶ የተፈጥሮ የሆነው ሕጋዊ ሩካቤ እምብዛም ላያስደስተው ይችላል፡፡

➪ ብዙ ወንዶችና ሴቶች በእጅ የሚፈጸም ግለ ወሲብን ከትዳር በፊት ይፈጽሙታል፡፡ ይህም በተግባር የሚፈጸመውን ሩካቤ ሥጋን በመፍራት በራሳቸው ሕይወት የግላቸውን ይፈጽማሉ፡፡ የግለ ወሲብ አንዱ ችግር ዘርን ያለ አግባብ ያለቦታው በማፍሰስ፣ በኃጢአት ላይ ኃጢአትን መጨመርና እራስን ማርከስ ነው፡፡

➪ ወዳጄ ስንት ለሀገርና ለወገን ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅሙ ዘሮች ያለ ቦታቸው ወድቀዋል፡፡ ሴቶች ድንግልናቸውን ከመጠበቅና ደፍረውም ተፈጥሮአዊ ሩካቤን ለመፈጸም ከመፍራት አንጻር ግለ ወሲብን በአልጋቸው፣ በሥራ ቦታቸው፣ በመዝናኛ ቦታ፣ በሲኒማ ቤቶች ወዘተ ይፈጽማሉ፡፡ ግን በእነዚህ ሁሉ ድርጊቶች የዝሙት መንፈስ ትልቅ ሚና ይኖረዋል፡፡

➪ ዝሙትን አልፈጽምም ብለን የሥጋ ንጽሕናችንን ብንጠብቅም በግለ ወሲብ በመፈተን ንጽሕናችንን እናጎድላለን፡፡ ‹‹ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ›› የተባለው ይሄም ነው፡፡ /ሮሜ 1÷26/ ሰይጣን ምናልባትም ኃጢአት እስከ ማይመስል ድረስ እየመከረ፣ በግለ ወሲብ እያሰከረ ትውልዱን ይጫወትበታል፡፡ ይህንን ድርጊት የሚፈጽሙትን ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ›› በማለት በእጅጉ ይገሥጸናል፡፡ ዮሐ 8÷44

➪ ዓይነ ጥላና የዝሙት መንፈስ እኛን በግለ ወሲብ በመጥመዱ በማስለመዱ ሁለት ጥቅም ያገኛል፡፡ በተለይ ሰውን ከተፈጥሮ ውጭ ዓይን አፋር የሚያደርግ ዓይነ ጥላ ግለ ወሲብን ያስለምዳል፡፡ አንደኛው ተፈጥሮአችን ባልሆነና በማይስማማን መልኩ እርካታን እያገኘን ግለ ወሲብን በማቆራኘት ከተፈጥሮ ሩካቤ ማስወጣት ሲሆን ሁለተኛው በግለ ወሲብ ምክንያት የኃጢአታችንን ሒሳብ ከፍ በማድረግ ከፈጣሪ ማጣላት እና ማቆራረጥ ነው፡፡ ሰይጣን በግለ ወሲብ እነዚህን ሰይጣናዊ ጥቅም ስለሚያገኝ ነው ግለ ወሲብን ለመተው ከባድ የሚሆንብን፡፡

➪ ሁለተኛው በፊልም በምናያቸው፣ በምናነባቸው መጻሕፍት፣ መጽሔቶችና ዘልማድ በምናደርጋቸው ትዕይንቶች የሚመጣው ግለ ወሲብ የብዙ ሰው ልማድ ሆኗል፡፡ አባቶችም ከልምድ ኃጢአት እራስህን ጠብቁ የሚሉት የልምድ ኃጢአት ከእኛ ጋር በመዋሐድ በጊዜ ሂደት ኃጢአት ላይመስለን ስለሚችል ነው፡፡ ይህ ክፉ ሰይጣናዊ ልማድ በአሁን ሰዓት ያልታወቀበት ግን ብዙ ወጣቶች የሚሰቃዩበት ወረርሽኝ ሆኗል፡፡

➪ ወዳጆቼ ከኃጢአት ሁሉ ክፉ ኃጢአት አንድ ድርጊት ልማድ ሲሆን ነው፡፡ ልማድ ከሆነ ንስሐ፣ ምክር፣ ትምህርት በቀላሉ ላያላቅቁን ይችላሉ፡፡ ልማድ ከሆነ ደግሞ ድፍረት ይሆንና የድፍረት ኃጢአት ሆኖ ስንተገብረው ምንም ላይመስለን ይችላል፡፡ እንደ ዳዊት ‹‹የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባርያህን ጠብቅ፤ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፣ ከታላቅም ኃጢአት እነጻለሁ›› ብለን ልንጸልይ ይገባል፡፡ /መዝ 19÷13/

➪ ግለ ወሲብን ከአፈጻጸሙ አንጻር በአራት ከፍለን እናያቸዋልን፡፡ አንደኛ የደናግል ግለ ወሲብ ነው፡፡ ከላይ እንዳየነው በውስጣችን ያለው ዓይነ ጥላና የዝሙት መንፈስ ሩካቤ ብንፈጽም ‹‹ድንግልናዬን አጣለሁ ግን ደግሞ በፍትወት እሰቃያለሁ›› የሚሉትን ሰዎችን የሚያጠቃ ነው፡፡ ይህን ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ለድንግልናቸው እንጂ ለቅድስናቸው ካለመጠንቀቅ ይፈጽሙታል፡፡

➪ አንዳንዴ ሴቶቹ ግለ ወሲብን ለብቻቸው፣ አልጋቸው ውስጥ በመሆን በእጃቸው ኃፍረታቸውንና የስሜት አካላቸውን በመነካካት ይፈጽሙታል፡፡ ወንዶቹ ደግሞ የከበረ እጃቸውን በመጠቀም ግለ ወሲብን ይፈጽማሉ፡፡ በዚህ ድርጊት ቅድስና፣ ንጽሕና እና ድንግልና ይጠፋል፡፡