Get Mystery Box with random crypto!

ነው፡፡ /ሕዝ 33÷11/ ➪ ወዳጆቼ ስለ ግለ ወሲብ በመንፈሳዊ እይታ ይህንን ብልም ግለ ወሲብ አ | " አውደ ገሀድ "

ነው፡፡ /ሕዝ 33÷11/

➪ ወዳጆቼ ስለ ግለ ወሲብ በመንፈሳዊ እይታ ይህንን ብልም ግለ ወሲብ አሁን ሳይንሱ በጥናት የጎንዮሽ ጉዳቶቹን ደርሶበታል፡፡ እውነታውን አረጋግጫለሁ፣ ጉዳቱን አውቄያለሁ ያለውን ብንመለከት ግለ ወሲብ አሉታዊ ተጽዕኖዎች አሉት፡፡ አንድ ሰው ግለ ወሲብ ሲፈጽም፣ ሲያዘወትር የዘር ፍሬው ይቀንሳል፡፡ ይህ ማለት ዘር የመተካት/የመውለድ እድሉን በከፍተኛ ሁኔታ በራሱ ይቀንሳል፡፡

➪ በተለያዩ መንገዶች እራስን ለማርካት በሚሞከርበት ጊዜ ብልት ላይ ጉዳት ይደርሳል፡፡ በተለይም ብልት ላይ ያሉ ስሜት ቀስቃሽ ነርቮችን ተፈጥሯዊ ባልሆነ ፍትጊያ ልንገድላቸው እና ልናጣቸው እንችላለን፡፡ ይህ ደግሞ ወደ ፊት ስንጎለምስ ሩካቤ የመፈጸም አቅማችንን ያሳጣናል ወይም ስንፈተ ሩካቤ ለምንለው ችግር ይዳርገናል፡፡

➪ በኅብረተሰቡ ዘንድ መገለልና መድልዎ ያመጣብናል፡፡ ከፍተኛ ለሆነ አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ ያጋልጠናል፡፡ ለወገብ ሕመም ይዳርጋል፡፡ ከትዳር አጋር ጋር ወይም ከተቃራኒ ጾታ ጋር ሩካቤ ሥጋ በተለመደው መንገድ ለመፈጸም እንድንቸገር ያደርገናል፡፡ ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ያጋልጠናል፡፡

➪ ሽንት መቆጣጠር አለመቻልን በጊዜ ሂደት ያመጣብናል፡፡ ለኩላሊት በሽታ ይዳርገናል በጊዜ ሂደትም ሁለቱም ኩላሊታችን ከጥቅም ውጪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ /ፌል ያደርጋሉ/፡፡ የዓይናችን እይታ ሊቀንስ እና በጊዜ ሂደት ለዓይነ ስውርነት ልንጋለጥ እንችላለን፡፡ ለከፍተኛ የመርሳት በሽታ እንጋለጣለን፡፡ ንቃተ ሕሊናችን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፡፡

➪ ለመገጣጠሚያ ሕመም እንጋለጣለን፡፡ ግለ ወሲብ የሚያዘወትር ሰው በ 20 ዓመቱ እንደ 70 ዓመት፤ በ30 ዓመቱ እንደ 80 ዓመት አዛውንት እጅ እግሩ፤ ወገቡ መገጣጠሚያው ይንቋቋል፡፡ በተለይ ቁጭ ብሎ ሲነሳ ውኃ እንዳጣ የደረቀ ቁርበት ይንቋቋል፣ ይንቆሻቆሻል፡፡ ለመገጣጠሚያ ድርቀት ይጋለጣል፡፡

➪ ዘይት የጨረሰ መኪና ሞተሩ ይነክሳል ከጥቅም ውጪ ይሆናል፡፡ በወጣትነታቸው ዕድሜ በግለ ወሲብ ምክንያት አጥንታቸው መገጣጠሚያቸው የነከሰ ወጣት የትየ ለሌ ናቸው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ላላወቅናቸው ለጤና ቀውሶች ተላልፈን እንሰጣለን፡፡

➪ ተወዳጆች ሆይ ከዚህ ጸያፍ እና አጋንንታዊ ተግባር ለመላቀቅ ድርጊቱን የሚጸየፍ ሕሊና፣ ለንስሐ የጀገነ ልቦና ያስፈልገናል፡፡ እንዲሁን ንስሐ፣ ጾም፣ ጸሎት በተለይም ብርቱ ስግደት ያስፈልገናል፡፡ በተለይ ጸበል መጠመቅ ትልቁ መፍትሔ ነው፡፡ በተረፈ መምህራንንና አባቶች ካህናትን በማማከር፣ እግዚአብሔርን በመማጸን ከዚህ ሰይጣናዊ ተግባር ለመላቀቅ መሞከር ሳይሆን መተግበር አለብን፡፡

➪ እባካችሁ በልጅነታችን የገባው ዓይነ ጥላና የዝሙት መንፈስ በግለ ወሲብ እንዳይጫወትብን፣ ነገአችንን እንዳያበላሽብን፣ ከወደደን በሞቱ ሕይወቱን ከሰጠን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንዳያቆራርጠን አጋንንቱን ልንነቃበት ይገባል፣ እስከ ዛሬ የተጫወተብን ይበቃል፡፡
.
.
.
.
.
.
#share  ይደረግ።
.
.
ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻችሁን ለመጋበዝ
  @Awede_gehad
  @Awede_gehad