Get Mystery Box with random crypto!

አሮራ (ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል) ምዕራፍ _11 እለቱ እሁድ ነው። አሮራ  ናይት ክ | አትሮኖስ

አሮራ
(ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል)
ምዕራፍ _11
እለቱ እሁድ ነው። አሮራ  ናይት ክለብ በስራ ላይ ነው ያለችው።  ይሄ መድረክ ለእሷ የፀሎት ስፋራዋ ነው።ጭንቀቷን የምትረሳበት ከሀሳቧ እፎይ ምትልበት  ፍፁም የእረፍት ስፍራዋ ነው።ሙዚቃ ባይኖርና እሷም ሙዚቀኛ ባትሆን ይሄን ከባድና የተወሳሰበ ህይወቷን እንዴት አድርጋ መቋቋም እንደምትችል ስታስብ ይገርማታል።ሰዓቱ ከምሽቱ  አራት ሰዓት አካባቢ ነው።ለሁለተኛ ዙር ወደመድረክ  የወጣችው።አንድ በቅርብ የለቀቀችውን ነጠላ ሙዚቃ ከዘፈነች በኃላ በሁለተኛ ላይ የታዋቂና ተወዳጆን የአስቴር አወቀን" ጠይም ዘለግ ያለ..."እያለች መዝፈን ስትጀምር ከታዳሚው መካከል  ተነስቶ እሷ ወደምትዘፍንበት መድረክ አካባቢ ቀረበና  ያለምንም ይሉኝታ ወለሉ  ላይ ተንበርክኮ ሙዚቃውን በተመስጧ ማዳመጥ ጀመረ...የታዳሚው ቀልብ የእሷን ዘፈን በማዳመጥና የሠውዬውን ሁኔታ በመከታተል መሀል መበታተኑ ያስታውቃል...አይደለም ታዳሚው እራሷ አሮራ  መንፈሷ እየተሸራረፈባት ነው።ሠውዬውን አውቃዋለች።መንግስቱ ነው።በእሷ ጦስ አባቷ ለሶስት አመት ያሳሰረው እና ሰሞኑን መፈታቱን የሠማችው አፍቃሪዋ።

መንግስቱ በተንበረከከበት ሆኖ አይኖቹን ጨፍኖ በጆሮው የሚያፈቅራትን ልጅ    ጥዑም ሙዚቃ እያዳመጠ በምናብ ለመጀመሪያ ጊዜ የዛሬ አራት አመት  እዚሁ ቤት እሷን ያየበትንና በእሷ የተነደፈበትን ትዕይንት በምናብ በምስለት መቃኘት  ቀጠለ።

በወቅቱ መንግስቱ  ከወጣትና ሀብታም ጓደኞቹ ጋር ለመዝናናት ሲመጣ  እሷ ደግሞ መድረክ ላይ ሆና ስትዘፍን ነው የተመለከታት ።መጀመሪያ ድምፆ ነው በጆሮው ሰርስሮ የገባው። ያን ያህል የሙዚቃ አፍቃሪ አይደለም።ግን ድንዝዝ ነው ያለው ።ወደመድረኩ  ፊቱን አዞረና  ተመለከታት። ሸንቀጥ እና ዘለግ ያለች ወጣት ሴት ነች ..ደብዛዛውና ቀለም የበዛበት የቤቱ መብራት ፊቷ ላይ ቦግ ብልጭ ስለሚልባአት  በጥራት አልታየችውም። ዘፈኗን ጨርሳ ከመድረክ ወረደችና ወደጀርባ በሚወስደው በራፍ ገባችና ተሠወረች ...እሷ በወጣችበት በር ሌላ ወንድ ዘፋኝ መጥቶ ተካት።
"ማን ነች ልጅቷ?"ሲል ጓደኞቹን ጠየቀ...ማንም አያውቃትም"አንደኛው ጓደኛው ቤተኛ ስለነበረ የናይት ክለብን ስራ-አስኪያጅ አስጠራው።ሠውዬው እነሱ ጋር እንደደረሰ
መንግስቱም"አሁን ዘፍና የወረደችው ዘፋኛኝ  ማን ነች?"ሲል ጠየቀው።
"አሮሯ ትባላለች  ...ምነው ዘፈኗ አልተመቻችሁም እንዴ?"
"አይ በጣም ጥኡም ድምፅ አላት...ልተዋወቃትና አድናቆቴን ቀጥታ ልገልፅላት እፈልጋለሁ"አለው።
በንግግሩ  ጓደኞቹ  ግራ ተገብ..እንዲህ አይነት የመንሰፍሰፍ አመል አልነበረውም ...ስራ-አስካጅ አንገራገረ"ያው ልትዘፍን ስትመጣ ነው ማግኘት የሚቻለው"
ጓደኛው ጣልቃ ገባ"አረ ተው ...ውለታ ዋልልን እንጂ" በማለት ሲጫነው"
"በል እስኪ ና ከተቻለ እንሞክር" አለና  መንግስቱን እየመራ ወሰደው።ወደውስጥ ገብተው ከናይት ክለብ  ጋር የተያያዝ ከጀርባ ያለ ክፍል ሲደርሱ ቆሙና"ያ በራፉ ላይ ያለው ጠባቂዋ ነው..እኔ ቀርበውና በወሬ አዘናጋዋለሁ.. ከዛ አንተ ቀስ ብለህ ግባና አግኛት...ግን ችግር ከተፈጠረ አደራ ስሜን እንዳታነሳ..ቀጥታ ነው የምባረረው."ሲል ስጋቱን ነገረው።በዛ ተስማሙና ስራአስኪያጅ ጋርድን በወሬ ሲያዘናጋለት እሱ የጠቆመውን ክፍል ገፋ አድርጎ ገባና መልሶ ዘጋው።
...ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ ብላለች..ፊት ለፊቷ አነስተኛ ጠረጴዛ አለ...ጠረጴዛው ላይ በዛ ያሉ ኮስሞቲኮች ተኮልኩለዋል።ፊት ለፊት ደግሞ ትልቅ መስታወት አለ...እዛ መስታወት ላይ  አይኖቾን ሰክታ  በሀሳብ ጠፋታለች።  ከጉንጮቾ ላይ እንባ እየረገፈ ነው።
ኩሏ ለቆ ከእንባዋ ጋር ተደባልቆ ፊቷን የህፃናት የስዕል ደብተር አስመስሏታል።እንደዛም ሆኖ ግን ከድምፆ የሚስተካከል አስደንጋጭ ውበት ነበራት።
ቀስ ብሎ ወደውስጥ ዘለቀ ...አላስተዋለችውም ...ዝም ብሎ ከጎኗ ካለ ወንበር ላይ በፀጥታ ተቀመጠ...ለአሰር ደቂቃ ከነበረችበት ሀዘን ያጠቆረው ምስጠት ውስጥ ልትወጣ አልቻለችም..
ከዛ ግን ድንገት"በጣም ይሸተኛል..መጥፎ የሚሰነፍጥ ሽታ አንጀቴ ውስጥ ገብቶ ይረብሸኛል...አስታውኪ አስታውኪ ሁሉ ይለኛል"አለች።
ምን እንደሚመልስላት ግራ ገባው ።የንግግሯ መነሻና መዳረሻውም ሊጨበጥለት አልቻለም።
"የእኔ እመቤት ምንድነው ሚሸትሽ ?አመመሽ እንዴ?"
"ወንዶች እንዲህ በጣም ሲጠጉኝ ያመኛል ..በዚህ አለም ላይ ብቸኛ ችግሬ ወንዶች ናቸው...."
በንግግሯ በጣም ከመደንገጡ የተነሳ ድንገት በእጆቹ ኤሌክትሪክ እንደጨበጠ ሰው ሽምቅቅ አለ። ብዙ ቆይቶ ሊያበሳጫት አልፈለገም።ከተቀመጠበት ተነስቶ ቆመና ወደኃላው ሶስት እርምጃ ተራመደ "የእኔ እመቤት ምን አይነት ስሜት ውስጥ እንዳለሽና እንዴት አይነት ጭለማ ውስጥሽን እንዳጠቆረው አላውቅም ..እኔ አመጣጤ ድምፅሽ ምን ያህል ውብ እንደሆነና የተጫወትሻቸው ሁሉም ሙዚቃዎች እንከን አልባ እንደሆኑ ልነግርሽ ነበር "
"አውቃለሁ...ድምፄም ሆነ የተጫወትኳቸው ሙዚቃዎች እንከን አልባ እንደሆኑ በደንብ አውቃለሁ...ምክንያቱም ሀዘኔን ነበር የበተንኩት... ቁስሌን ነበር  በጣቴ የቆሰቆስኩት...ምሬቴን ነበር ለፈጣሪ ያሰማሁት ...እና ታዲያ እንዴት ላያምር ይችላል ብለህ ጠበቅክ...?ለማንኛውም ሲጋራ ይዘሀል...በጣም ጠማኝ".
"አይ አልያዝኩም ግን ባር ያሉት ጎደኞቼ ውስጥ የሚያጨሱ ስላሉ ልልክልሽ እችላለሁ..."
"እባክህ ...ከአድናቆትህ በላይ የሚጠቅመኝ እሱ ነው"
"እሺ ልክልሻለሁ ...ለማንኛውም መንግስቱ እባላለሁ...ያንቺ አሮራ እንደሚባል ነግረውኛል።ሌላስ...መጠጥ ትፈልጊ ይሆ?።"
"ደስ ያለህን ላክልኝ "አለችው ።ከክፍሉ ውስጥ ሲወጣ ጋርድ ግራ ተጋባ..ፈጠን ብሎ በሩን ከፈተና ወደውስጥ ተመለከተ ሁሉ ነገር ሰላም መሆኑን ሲያይ ተንፈስ አለ።
መንግስ ቀጥታ ወደ ናይትክለብ  ተመለሰ። ከአንድ ጓደኛው አንድ ባኮ ሲጋራ ከአንድ ጠርሙስ ጎርደን ጅን ጋር በ አንድ አስተናጋጅ በኩል ላከላትና ጓደኞቹ  ተሰናብቶ ወጥቶ ወደ ቤቱ ሄደ።በጣም ነበር የረበሸችው፤እንደዛ መንፈሷ የተሠበረች  ሴት  ለዛውም ገና ጮርቃ ወጣት በህይወቱ አጋጥሞት አያቅም። የትኛው የተረገመ ወንድ ይሆን  ገና ከህይወት መነሻዋ ጋር ያለችን ውብ ሴት እንደዚህ ወልቅልቅ እንድትል ያደረጋት ...?ደህና እንቅልፍ ሳይተኛ ስለእሷ ሲያስብ ምን ሆና ይሆን በማለት መላ ምት  ሲደረድር እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር እንዲሁ ሲገላበጥ ነጋበት።
በእንደዚህ አይነት ሁኔታና አጋጣሚ ነበር አሮሯ እና መንግስቱ ለመጀመሪያ ቀን የተገናኙትና የተዋወቁት


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj