Get Mystery Box with random crypto!

አሮራ (ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል) ምዕራፍ _10 ስለናይት ክለቡ የሆነ ነገር | አትሮኖስ

አሮራ
(ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል)
ምዕራፍ _10


ስለናይት ክለቡ የሆነ ነገር በማወቋ ደስ አለው‹‹በቅርብ ገብተሸ ተውቂያለሽ……?አይ አዲሱ ፍሬንዴ ብዙም እደዛ አይነት ነገር ስለማይመቸው ስድስት ወር አለፈኝ መሰለኝ፡፡››
‹‹ከሶስት አመት በፊት አዚህ እያለሁ እዛ ሚሰራ የሆነ ሰው አውቅ ነበር….አሁን ይኑር አይኑር ለማጣራት ፈልጌ ነው››
‹‹ምን ?ስልክ ቁጥሩን አታውቅም….?››
‹‹እንደዛም ቢሆን ቀላል ነበር….ምንም የማገኝበት መንገድ የለም››
‹‹ምንድነው የሚሰራው?››
‹‹ሴት ነች…ዘፋኝ ነች››
‹‹ዘፋኝ…ታዲያ ምን ችግር አለው ..ዘፋኝ ከሆነችማ በቀላሉ ማጣራት እንችላለን፡፡ማነች እኔ እራሴ አውቃት ይሆናል?››
‹‹አሮራ ትባላለች፡፡››
ከፊቶቷመቀያየር መደነቋ እያስታወቀባት‹‹ጥቁሯን አልማዝ ነው ምትፈልገው?››አለችው፡፡
‹‹አዎ ጥቁር አልማዝ አላችኋት?››

‹‹አዎ ….ከዋናው ስሟ እኩል በዚህ ሰም ትታወቃለች….የማትበላዋ ወፍም ይሏታል..ብቻ ስመ ቡዙ ነች…ምን ጓደኛህ ነበረች?››
‹‹አይ እንዲሁ ነበር የመውቃት…አሁን  ለሆነ ጉዳይ ፈልጌያት ነው ››
‹‹ታዲያ እሷ እኮ ምን አልባት ለስራ ወደውጭ ሀገረ ካልሄደች ትገኛለች…እቤቱ እኮ የአባቷ ነው..እሱን አታውቅም?››
‹‹አውቃለሁ….ያው እንዳልሽው ሀገር ውስጥ ካልሆነች ብዬ ነው፡፡››
እስን እናጣራለን……ግን ሀለቃ እየሰራች ቢሆን እንኳን ከእሷ  ተገናኝቶ ለመነጋገር ነገሮች ቀላል አይሆኑልህም..ዘወተር በሶስትና አራት አውሬ በሆኑ ጋርዶች እንደተጠበቀች ነው፡ኢትዬጳያ ውስጥ ከእሷ በላይ ጥበቃ የሚደረግለት ሌላ ሰው እኔ የማውቀው የለም ምን አልባት ጠቅላይ ሚኒስቴር ካሆነ በስተቀር››
‹‹አውቃለሁ… ብቻ እሷ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ ትኑር እንጂ የማግኘቱን ዘዴ  አስብበታለሁ››
‹‹ስለዚህ አሁን መኖር አለመኖሯን ብቻ ነው የምታጣራው፡፡››
‹‹አዎ፡፡››ደረሱን ናይት ክለቡ ፊት ለፊት መኪናዋን አቆመች …‹‹ሀለቃ ሴት ስለሆንኩ ከአንተ ይልቅ እኔ እሻላለሁ ዘበኞቹን አሳስቄ የሆነ መረጃ ነድፌያቸው መጣሁ ››ብላ እዛው መኪናው ውስጥ ጥላው ገቢናውን ከፍታ ወረደች…ከእስር ቤት ከዋጣ ሁለት ቀን ሆኖታል ፡፡በዚህ ሁለት ቀን ካገኛቻውና ከናገራቸው ሰዎች ሁሉ ቀልቡ ሙሉ በሙሉ የተቀበላት ይህቺን ልጅ ነው፡፡‹‹ግልፅ..የሰውን ስሜት በፍጥነት የምትረዳ ድርዬ መሳይ ግን ስርዓት ያላት ሴት ነች›› አለ፡፡ከ15 ደቂቃ በሃላ ተመልሳ መጣችና  ገቢናዋን ከፍታ ገብታ ቁጭ አለች፡፡
‹‹እሺ… ምን አገኘሽ?›› አላት ፡፡
‹‹አለች፡፡በሳምንት ሁለት ቀን ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ እና እሮብ ለሀሙስ አጥቢያ ነው የምትሰራው አሉ፡፡››
‹‹ዛሬ ምንድነው ቀኑ፡፡››
‹‹ሀሙስ››
‹‹በስመ አብ ….ገና ቅዳሜ ድረስ..››
ትእግስት  ተደነጋገራት…‹‹ይሄ ሰውዬ ለምን አይነት ለጉዳይ ነው የፈለጋት ?›› ስትል በውስጧ አሰበች፡፡
‹‹..ጉዳዩ በጣም አስቸኮይ ነው እንዴ?››
‹‹አይ ቅዳሜ አይደል…እስከዛ ቢቆይ አችግር የለውም››አለ፡፡
አይኗን ሳለይ ለሶስት አመት መጠበቅ የቻልኩ ሰውዬ ለሶስት ቀን መጠበቅ ትዕግስት እንዴት አጣለሁ..?››ሲል እራሱን ገሰፀ..እዛ እስር ቤት ሆኖ ቴሌቭዝን በማየት ሱስ እሱን የሚስተካከለው የለም ነበር….ሰው ሁሉ ከሚያወራው ወሬ ወይም ከሚተላለፈው ፕሮግራም ስለሚማርኩት ይመስለዋል..እሱ ግን ምን አልባት የዘፈን ምርጫቸውን እሷን ያደርጋሉ በሚል ጉግት ነው፡፡ስትዘፍን ለመመልከት… ድምፆን ለመስማት ነው፡፡ብዙ ጠብቆ በሳምንት አንድ ቀን እንኳን ቢሰካለት ለእሱ ፋሲካው ነው፡፡


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj