Get Mystery Box with random crypto!

አሮራ (ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል) ምዕራፍ _9 እንዴት አድርጎ የዘመናት ብስጭ | አትሮኖስ

አሮራ
(ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል)
ምዕራፍ _9

እንዴት አድርጎ የዘመናት ብስጭቱንና ቂሙን ሊበቀል እንደሚችል ግን የተሰበበትና የተጠና እቅድ የለውም….እንደዚህ ሎቶሪ በመሰለ ቅፅበታዊ አጋጣሚ ሰውዬው ጠቅላላ በህይወቱ ሙሉ የለፋበትንና የደከመበት ሀብት ሁሉ እጁ  እንደሚገባ  እንዴት ሊያስብ ችሎ ነው.እቅድ ሚኖረው..ግን ደግሞ በጣም በቂ ጊዜ አለው…አመታት ንብረቱም የሰውዬው ቤቱም ሆነ ሚስቱ በእጁ ይቆያል..እናም ዘና ብለ ምን ማድረግ እንዳለበት ያስብበታል፡፡
‹‹ምነው ተከዝክ?››
‹‹አይ ብቻ ይሄን ሁሉ ኃላፊነት ለእኔ መስጠትህ አልተዋጠልኝም….ሌላ አማራጭ ካለህ ብታስበበት ደስ ይለኛል?››አለው ..በውስጡ ስለሆነው ነገር በመደሰት ፡፡
‹‹አይ ይሄ ለአማራጭ የሚቀርብ አይደለም…ለንብረቶቼ አስተዳዳሪ የምቀጥር ቢሆን የብዙ ሰው ሲቪ ሰብስቤ
ልምዳቸውንን ፀባያቸውን በማጥተናት ከዚህ ያኛው ይሻላል ብዬ ማማረጥ እችል ነበር፡፡አሁን ግን እንደራሴ የማምነውን ስጋዬ እና እንደልጄ ለሆነ ሰው የእኔ ሆነውን ነገር ሁሉ በአደራ መስጠት ነው የምፈልገው፡ይሄ ደግሞ ውጭ ለምሄድባቸው አምስት አመታት ብቻ ሳይሆን እስከወዲያኛው እጣችን የተሳሰረ ነው፡፡የእኛንም ሆነ የመጪ ቤተሰቦቻችንን ዕጣ ፋንታ አብረን እንገነባለን፡፡የእኔ ልጆችም ሆኑ አንተ የምታፈቅራትን ልጅ አግብተህ የምትወልዳቸው ልጆች ነጋቸው ብሩህ እንዲሆን አብረን እንለፋለን፡፡ ደግሞም እናሳካዋለን ፡፡››
‹‹እሺ ካልክ…አሁን ግን የሆነ ቦታ ደርሼ ለመምጣት ፈልጌ ነበር››
ፈገግ ብሎ‹የት ልጅቷ ጋር?››
አቀረቀረ..
‹‹እሺ ጥሩ …ግን መጀመሪያ ትዕግስትን ልጥራና ገስት ሀውሱን አዙራ ታሳይህ..ከዛ የፈለክበት መሄድ ትችላለህ…ለመሆኑ መኪና መንዳት ትችላለህ?››
‹‹አዎ ግን መንጃ ፍቃዴ አልታደሰም››
‹‹እሺ ለጊዜው የምትፈልገው ቦታ ትዕግስት ይዛህ ትሂድ…እና እንዳሳደስክ የራስህ መኪና ተዘጋጅቷልሀል፡፡
‹‹አጎቴ በጣም ነው የማመሰግነው…..አሰቸገርኩህ››
‹‹አይ በቤተሰብ መካከል አስቸገርኩህ አስቸገርከኝ የሚሉ ቃላት ጥቅም ላይ አይውሉም››አለና መጥሪያውን አንጫረረ..ከ5 ደቅቃ በኃላ አንድ ልጅ እግር ወንዳወንድ አቋም ያላት ልጅ በራፉን አልፋ ገባች፡፡
‹‹እንዴት ናችሁ ጋሼ ፈለከኝ?››
‹‹አዎ ፈልጌሽ ነው..ተዋወቂ የነገርኩሽ ትልቁ ልጄ እሱ ነው፡፡››
ልክ ከዚህ በፊት እንደምተዋወቁና ለረጅም ጊዜ ሳይተያዩ እንደቆዩ ወዳጆች  እሮጣ ሄዳ ተጠመጠመችበት፡፡
‹‹በይ እንግዲህ ከዚህች ሰዓት ጀመሮ ሀለቃሽ እኔ ሳልሆን እሱ ነው….ለእኔ ትታዢ እንደነበረው ከቻልሽ ከዛም በላይ ለእሱ ታዘዢ ..እንደነገርኩሽ ለስራው አዲስ ስለሆነ ሁሉንም ነገር በትዕግስት አሳይው.. .እስከፈለገሽ ጊዜ ድረስ እረዳቱ ሆነሽ ትቀጥያለሽ..በይ አሁን ግቢውን በማስጎብኘት ጀመሩ..››
‹‹እሺ ጋሼ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ..እንሂድ ሀለቃ›› አለች..
ያለ ምንም ንግግር  መቀመጫውን ለቀቀና በዝምታ ተከተላት፡፡
ምዕራፍ-
‹‹ክፍሎቹን ሆነ ግቢውን እንዲሁም ዋና ዋና ነገሮች ለመጎብኘት ከ40 ደቂቃ በላይ ነው የወሰደባቸው…፡፡በወቅቱ ስራ ላይ ካሉ ሰራተኞች ጋርም አስተዋቀችው..እንደጨረሱ››መንጃ ፍቃዴ  ስላልታደሰ መኪና መንዳት አልችልም…የሆነ ቦታ ትወስጂኛለሽ?›› ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹በደስታ ነዋ፡፡››አለችና ገስት ሀውሱ መኪና ማቆሚያ ወደ ቆመችውን የድርጅቱን መኪና ይዛው ሄደች… ገቢና ከጎና አስቀምጣ መኪናውን አስነሳችና  ግቢውን ለቀው ወጡ፡፡‹‹ወደየት ልንዳው?››
‹‹22-ቨክቶሪያ ናይት ክለብ….ታውቂዋለሽ?››


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj