Get Mystery Box with random crypto!

አሮራ (ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል) ምዕራፍ _8 ‹‹የሚገርም ነው…ይህቺን ልጅን | አትሮኖስ

አሮራ
(ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል)
ምዕራፍ _8

‹‹የሚገርም ነው…ይህቺን ልጅንማ ከመሄዴ በፊት ታስተዋውቀኛለህ?››
‹‹የት ነው የምትሄደው….?››
‹‹ይሄውልህ እዚህ ሀገር ውስጥ የምቆው ግፋ ቢል ለ15 ቀን ብቻ ነው፡፡ከዛ ወደካናዳ እሄዳለሁ፡፡››
‹‹ምነው ለእረፍት ነው?››
‹‹አይ ለስራ ነው….ከአንድ አለማ አቀፍ የመአድን አምራች ካምፓኒ ጋር የተለየ አይነት የስራ እድል አግኝቼያለሁ…የዚህ ድርጅት ዋና መቀመጫው ከናዳ ነው፡፡ግን ደቡብ አሜሪካ ሀገሮች ውስጥ ብዙ የማዕድን ማውጫ ቦታዎች አሉት….እኔ ከዛ ድርጅት ጋር ቢያንስ ለቀጣዬቹ 5 አመታት አብሬ ለመስራት ነው የምሄደው…ምን አልባትም በአመት ሁለቴ ወይም አንዴ ብቻ ነው መጥቼ ላያችሁ የምችለው፡፡ይሄ ስራ የሁላችንንም ህይወት ነው ከመሰረቱ የሚቀይረው..እና በዚህ የስኬት መንገድ ከጎኔ እንድትሆን እፈልጋለሁ››…
‹‹ቤተሰቦችህን ይዘህ ነው የምትሄደው?››
‹‹አይ ማለቴ ልጆቹ የተሻለ ትምህርት እንዲማሩ ሰለምፈልግ ከሶስት ወር በኃላ ተመልሼ መጥቼ ወስዳቸዋለሁ… በተረፈ ሁሉም ነገር እንዳለ ነው የሚቀጥለው፡፡እዚህ ያለውን ንብረቴንም ሆነ ቤተሰቤን እንድትቆጣጠርልኝ ፈልጋለሁ..ይሄ ገስት ሀውስ በወር እስክ አንድ ሚሊዬን ብር የተጣራ ገቢ ያስገባል….በተጨማሪ ሌሎች ተያያዥ ቢዝነሶች አሉ..እነዛን ሁሉ በአንተ ስር ይሆናሉ…ከአምስት አመት በኃላ ደግሞ ጠቅልዬ ስመለስ በጥናት ላይ የተመሰረተ አንድ ግዙፍ ከምፓኒ እንከፍትና በጋራ እናስተዳድራለን፡፡አንተ የወንድሜ ልጅ ነህ …ያ ማለት ደግሞ ልጄ ነህ ማለት ነው፡፡››
‹‹አጎቴ ሀሳብ ደስ የሚል ነው..ግን እኔ በህይወቴ ተቀጥሮ ከመስራት ወጭ የራሴን አንድ የሰፈር ሱቅ እንኳና ከፍቼ አስተዳድሬ አላውቅም …ስለገስት ሀውስም ሆነ ስለሌላ ቢዝነስ ምነም የማውቀው ነገር የለኝም››
‹‹አውቃለሁ…ያ ብዙም ሊያስጨንቅህ አይገባም…ሁሉን ነገር ያሚያስረዱህና በደንብ እስክትለምድ ድረስ እንደረዳት ሆኖ የምታግዝህ አንድ ጥሩ ልጅ አለች….አንተ በቃኝ ብለህ እስክታሰናብታት ድረስ ረዳትህ ሆና ትሰራለች፡፡ይሄ ደግሞ የትርፍና የኪሳራ ጉዳይ አይደለም…ቤተሰበን የመሰብሰብ ጉዳይ ነው….ይሄ የራስህ ንብረት ነው..ከሰርክም አተረፍክም የራስህው ነው. ምርጫ ስለሌለህ ፈጣን ተማሪ ለመሆን መጣር ብቻ ነው የሚያዋጣህ፡እስከምሄድ ደግሞ እኔም አለው ዋና ዋና ነገሮችን አሳይሀለው››
‹‹ግን አጎቴ ባለቤትህ ከአንተ ጋር የማትሄድ ከሆነ ለምን ሀላፊነቱን ለእሷ አትሰጥም ነበር..እሷስ ብትሆን ንብረቷ በሌላ ሰው ቁጥጥር ስር ሲተዳደር ደስ ይላት ይመስልሀል››
ስለእሷ ምንም አታስብ፡፡ ንብረቷ በሌላ ሰው ቁጥጥር ስር ሳይሆነ በወንድሜ ልጅ ቁጥጥር ስር ነው የገባው…በዚህ መስማማት ግዴታዋ ነው፡፡በነገራችን ላይ ይሄንን ገስት ሀውስ ላይም ሆነ ጠቅላላ ንብረቴ ላይ በዚህ ይግባ በዚህ ይውጠ ብህ እንደምትወስን ሁሉ እሷ ላይም ያለህ ስልጣን እንደዛው ነው ሚሆነው….አንተ ያልፈቀድክበት ቦታ መሄድ አትችልም፤ አንተ ማታውቀውን ነገር ማድረግ አትችለም…ይሄንን ከመሄዴ በፊት ሁለታችሁም ባላችሁበት እንግራችኋላው፡፡
የሰውዬው ሁኔታና ጠቅላላ እቅዱ ሊጨበጥለት እልቻለም…፡፡‹‹ምን ያህል እንደምጠላው….ለአባቴ ሞት ለአባቴ የአመታት ስቃይና ህመም እሱን ተጠያቂ ሳደርግና ስረግመው እንደኖርኩ ቢያውቅ እንዲህ በድፍረት ንብረቱንም ሚስቱንም አሳልፎ አይሰጠኝም ነበር››ሲል አሰበ ፡፡

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj