Get Mystery Box with random crypto!

አሮራ (ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል) ምዕራፍ _7 ‹‹እንግዲህ ይሄ የእኛ ገስት ሀውስ | አትሮኖስ

አሮራ
(ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል)
ምዕራፍ _7
‹‹እንግዲህ ይሄ የእኛ ገስት ሀውስ ነው፡፡በኃላ ልጀቹ ሁሉንም ክፍልም ሆነ  አጠቃይ ግቢውን እያዞሩ ያሳዩሀል…አሁን ግን እናውራ፡፡››
በሰማው ነገር ስለተደነቀ‹‹አሀ ያንተ ገስትሀውስ ነው ማለት ነው?››ሲል መልሶ ጠየቀው፡፡
‹‹አዎ እኛ ነው፡፡››
‹‹ጥሩ ..ግን አንተ ስለምትፈልግው ነገር ከማውራታችን በፊት እኔ እንዲመለሱልኝ የምፈልጋቸው መአት ጥያቄዎች አሉኝ፡፡ እስከአሁንም በውስጤ አፍኜ የያዝኳቸው አመቺውን ጊዜ ስጠብቅ ነበር፡፡››
‹‹ጥሩ ብዙ ጥያቄዎች እንደሚኖሩህ እኔም እጠብቃለሁ…ሁሉንም ጥያቄዎች ለመመለስ እሞክራለሁ፡፡››
‹‹እሺ ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኃላ ያለሁበት ቦታ እንዴት መጣህ? ለዛውም በመፈቻ ቀኔ ላይ?፡፡››
‹‹ምንመ መሰለህ የዛሬ ሰባት አመት በፊት ከአባትህ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ተለያየን …በወቅቱ ወንድሜ እናንተ አጠገብ እንድደርስ አይፈልገም ነበር፡፡ከዛ ከእናንተም ሆነ ከሌላው ቤተሰብ ተነጥዬ የራሴን ኑሮ መኖር ጀመርኩ፡፡››
‹‹እና ሲሞት ቀብሩ ላይ ሁሉ አልመጣህም…ምንም ብትቀያየሙ ብቸኛ ወንድምህ አይደል?››ሲል በጥንካሬ ሞገተው፡፡
‹‹አውቃለሁ..ግን በወቀቱ እኔ ሀገር ውስጥ አልነበርኩም፤፤ ወንድሜ ከሞተ ከሶስት አመት በኃላ ተመልሼ ስመጣ ነው መርዶውን የሰማሁት..በዛን ጊዜ  ስለአንተ እስርቤት መግባትህን ሰማሁ…ያው የነገሩኝ ደስ የማይል ነገር ስለበር ምንም ለማድረግ አልተደፋፈርኩም..››
‹‹ታዲያ አሁንስ ምን አዲስ ነገር ተገኘና ልታገኘኝ ወሰንክ?››
‹‹እንደአጋጣሚ ጠበቃህ ከነበረ ሰው ጋር የሆነ ቦታ ተገናኘንና ስለአንተ ተነሳ….የተፈጠረውን ነገር አስረዳኝ፡፡ በእውነት በጣም ነው ያዘንኩትም በራሴም ያፈርኩት….የሰው ወሬ ሰምቼ ችላ ከምልህ ቀርቤ አንተኑ ስለሁኔታው ብጠይቅህ ጥሩ ነበር…በጊዜው ልደርስልህና ልሟገትልህ ይገባ ነበር፡፡ከእድሜህ ላይ ሶስት አመት ሲባክን ዝም ብዬ በማየቴ በጣም ይቅርታ..››
‹‹አረ ነገሩ እንጂ ችግር የለውም..ደግሞ ምንም የባከነ ጊዜ የለኝም…ሶስት አመት በእስር በማሳለፌ ምንም የምቆጭበት ነገር የለም…ብዙ ነገር ተምሬበታለሁ፤ ከብዙ ድንቅ ሰዎች ጋር ተዋውቄ ብዙ የህይወት ተሞክሮ ከእነሱ አግኝቼለሁ..አዲስ ሞያ ተምሬለሁ፤ትእግስትን ….መረጋጋትንና …ጥሞናን ..አረ ብዙ ብዙ..ደግሞም በእሷ ምክንያት ሌላ 30 አመት ያህል ብታሰር እንኳን ቅንጣት ቅሬታ አይሰማኝም…››
‹‹ያን  ያህል ታፈቅራታለህ ማለት ነው?››
‹‹መጠንና ወሰን በሌለው ሁኔታ አፈቅራታለሁ…ደፈራት ብለው ሲከሱኝ በጣም ነው ያስገረሙኝ፡፡ እሷ እኮ የእኔው ነች፡፡ ልቤ ውስጥም ነፍሴ ላይም ያለችው እሷ ነች..እሷ ፊት ላይ ምታርፍ አንድ ጥፊ እንኳን ልቤ ላይ ጠባሳ ትተዋለች፡፡እንዴት ሰው የገዛ ልቡን በቢላዋ ወግቶ ያደማል…?እኔ እሷን እንኳን ልደፍራታ የለፍቃዷ  እጇን አልጨብጥም፡፡››
ፈዞ በተመስጦ ሲያዳምጠው የነበረው አጎቱ‹‹እሷስ ግን …?ማለቴ ያንተን ያህል ታፈቅርሀለች?››
‹‹እሱን ለማወቅ አልችልም…..እኔ እርግጠኛ ምሆነው በእኔ ማፈቅር ነው…ደግሞ የእኔ ፍቅር ጥልቅና ስምጥ ስለሆነ ለእኔም ለእሷም ይበቃል….ብቻዬንም ቢሆን ለሁለታችን የሚሆነውን ፍቅር ማመንጨት እችላለሁ፡፡››


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj