Get Mystery Box with random crypto!

የእናቴ ልጅ ክፍል ሃያ ስድስት ሰውን ከልብህ ስትጠላው ድምፁንም ሆነ አይኑን ለ | አትሮኖስ

የእናቴ ልጅ
ክፍል ሃያ ስድስት

ሰውን ከልብህ ስትጠላው ድምፁንም ሆነ አይኑን ለማየት ትጠላለህ ልክ የማይስማማህን ምግብ በግዴታ ብላ እንደመባል ነው የሚሆንብህ ። በሰአቱ የተሰማኝ ነገር  ለመናገር የማይቻል አስቸጋሪ ነበር ።
ወንድሜ ነብሰ ገዳይ ቀጥሮ ሊያስገድለኝ ተደራደረ በኔ በእናቱ ልጅ ላይ ።ለምን ብቻውን ወራሽ ለመሆን ለገንዘብ ብሎ ።'ምን አይነት ጊዜነው ክፉ ዘመን 'ብለው እናቶች አንዳንዴ የሚያማርሩት ያለነገር አይደለም ለካ ።እንደዚ አይነት የበዛ እራስ ወዳድነትእና ጥቅመኝነት ስላለ ነው ። ሰው እንዴት በሌላው ላይ ተረማምዶ ሕይወት ለመመስረት ይጥራል ። ሲሆን አቅምና ጉልበቱን አይምሮውን ተጠቅሞ እራሱን መለወጥ ሲኖርበት ባለፋበት ሀብት ላይ አይኑን ጥሎ  ሰውን እስከማጥፋት መድረስ ተገቢነው።  እውነትም ከባድ ጊዜ ወንድም በወንድሙ ላይ የሚነሳበት መሰሪነት የበዛበት ።
እናቴ ሽማግሌውን በጥያቄ ማጠደፉን አላቆም አለች እሳቸውም ዝም ብለው አቤልን ማየት ሆነ  ባዩሽ እያለቀሰች በመዘፍዘፊያ ውሃ አምጥታ ደሜን በጨርቅ እያረጠበች ትጠራርጋለች  ደግነሽ እልልልታዋ ወደኡኡታ ተቀይሮባታል
"ኡኡኡኡ እኔን አፈር ልብላ እኔን አክስትህን የኔሸበላ እንዲሁ ጠርተው ከመንገድ ሊያስቀሩህ ?የስራቸውን ይስጣቸው መዳኒዓለም ። እኔማ መጀመሪያም ሰትወጣ ደስ አላለኝም ነበር"እያለች ታለቅሳለች
"እባክዎት ማነው እንዲ ያደረገው ይንገሩኝ አባቴ "አለች እናቴ  ድምጿ ፍርሐት ያዘለ ነው ።ሽማግሌው እንዲነግሯት አልፈለኩም ለነገሩ እሳቸውም ዝም ብለዋት ነበር  ።እናቴ የልጇን የመጨረሻ አውሬነት ስታውቅ ምንልትሆን ትችላለች ፡ይህንን ነው የፈራውት ።እንጂማ አቤልን አንቄ ብገድለው እንኳ አሁን ላይ ቅር አይለኝም ነበር  ። ሽማግሌው ፡ያጎነበሰ ሰውነታቸው ቀጥ ብሎ መቆሙ በራሱ ገርሞኛል እኛ ድቅቅ ያሉ ሰውዬ በሳምንቱ ውስጥ ምን አግኝተው ነው እንዲ ቆፍጠን ያሉት ከክሳታቸው በቀር ተለውጠዋሉ  ። እናቴ ውትወታዋን አላቋረጠችም ሽማግሌው ደሞ ቃላት ያጡ ይመስል አቤል ላይ እንዳረፉ ነው ።አቤል ምንም ነገር ሳይተነፍስ ቆይቶ ድንገት የባነነ ይመስል ።
"አንቺ ባዩሽ ጓደኛውን ሊያገኝ ነው የወጣው አላልሽም ነበር እንዴ "አላት ባዩሽ አቀረቀረች
"እንዴ እሱማ እሱ የነገረንን ነው የሆነሰው በስልክ ጠርቶት ነው እንደውም ያንተው ጓደኛ እንደሆነነው ናቲ የነገረን አይደልእንዴ ናቲ ? ደሞስ የሆነ ሆነና ወጥተን እንፈልገው ስልህ ይመጣል ምን ይሆናል እያልክ ያዘናጋኽን አንተ አይደለህ "አለች አክስቴ ደግነሽ ቆጣ ብላ ።
እናቴ በጥርጣሬ ወደ አቤል ዞረች አይኗን ለመሸሽ ይመስል ተንቀሳቀሰ ፡  እናቴ ወደ አቤል ተጠግታ
"አንተ አንድ ነገር አድርገሃል እንዴ?"አለች ድምጿ እየተንቀጠቀጠ
"ኧረ እማዬ እኔ እኔ መቼ አአገኘውት እዚሁ ካካንቺ ጋር አአልነበርኩም "አለ እየተንተባተበ ።
"ባትሆን ይሻላል ከሆነ መቼም ይቅር አልልህም "ከማለቷ ።የሽማግሌው ቁጣ ገንፍሎ ወጣ ፍፁም ሌላ ሰው ሆኑ በፍጥነት እናቴን ከአቤል ዞር አድርገዋት ፊትለፊት አቤልን ተጋፈጡት  ከኪሳቸው የሚያብለጨልጭ ስለት አውጥተው የአቤል አንገት ላይ ቀሰሩት ፡አቤል እንዲ አይነት ነገር ገጥሞት ስለማያውቅ በድንጋጤ ፡ የእናታችንን ስም ጠራ ሽማግሌው በቁጣ "አንተ ነህ ወንድምህን ልታስገድል የነበረው አንተ ሳታየኝ በጨለማውስጥ ከዛ ከይሲ ነብሰ ገዳይ ጋር ስትደራደር አይቼሃለው ፡እዛ የቆማችሁበት ጨለማ ውስጥ ተደብቄ ሰምቻችዋለው ።ከዛ ምን እንዳደረኩ ታውቃለህ በፍጥነት እዚ መጣው ናቲ ከቤት ወጥቶ እናንተ የጠራችሁት ቦታ እንዳይመጣ ፀልዬ ነበር ነገር ግን መጣ ስለዚ እሱ አንተ የተጎዳህ መስሎት ሲሮጥ ከመንገድ ያገኘውትን ዱላ ይዤ ተከተልኩት ግን የሱንያክል መፍጠን አልቻልኩም ። እዛ ስደርስ የመጨረሻ እስትንፋሱን ሊዘጋው ቅጥረኛህ በዚ ስለት ሊሰነዝርበት ሲል የሞት ሞቴን በዱላ አናቱን አልኩና ጣልኩት ። ለትንሽ ልጄን አጥቼው ነበር ።አንተ አቤል መባል አልነበረብህም አንተ ቃዬል ነህ "ብለው አቤልን በጥፊ አጮሉት አቤል ሶፋውላይ በቁሙ ወደቀ ። እናቴ አበደች የምትይዝ የምትጨብጠው ጠፋት ። ደግነሽ የቤቴ ጉድ ብላ ለቅሶዋን አባሰችው ።ባዩሽ አፏን በሁለት እጆቿ ይዛ በድንጋጤ ቆማለች ።እኔ የሽማግሌው ከኔም በላይ ሆነው ተበሳጭተው እንደዛ ሲሆኑ ሳይ ተገርሜአለው በዚች ጥቂት ጊዜ ምን ያክል ቢወዱኝ ነው የኔ ተቆርቋሪ የሆኑት ።
"አንተ አንተ በቃ መቼም አታርፍም ደሞአሁን ምንድነው  ያልከኝን ሁሉ አድርጌ ጉዞህን አስተካከልኩ አሁን እሺ ምንድነው ከሱ ጋር የሚያጣላህ "ብላ ቁጭ ብላ እናታችን አለቀሰች አቤል ምን ያክል እንደሚሰባብራት አውቃለው እናቴ አሳዘነችኝ እናት ናትና ።
"አንተ መቼም ወደውጪ አትሄድም መቀጣት አለብህ ባለጌ እኔ ነበርኩ አቤል ያልኩህ ስትወለድ አንተ ግን የአቤልነት ጫፍ የለህም ሴጣን "አሉ ሽማግሌው ስሜታዊ ሆነው ።እሳቸው በቁጣውስጥ ሆነው የተናገሩት ነገር አምልጦአቸው ቢወጣም ፡እኛ በቤት ውስጥ ያለነው ሰዎች ሁሉ በአንድነት ምን ብለን ድምፅ አወጣን ። በተለይእናቴ አይኗም ሳይቀር ፈጠጠ ።በዚ ጊዜ ግን እኔ የሌለኝን ብርታት ከየት እንዳመጣሁት አላውቅም ተነስቼ ከፊትለፊታቸው ቆምኩ ።
"እርሶ ማን ነዎት ለሱ ስም ያወጡለት "አልኳቸው።መናገራቸውን ያወቁ አይመስልም ደነገጡ
"ይንገሩኝ እርሶ ማን ነዎት"ጮውኩ
"እኔ ምን አልኩ እባክህ ናቲ ተው "አሉ ተጨንቀው ወደ እናቴ እያዩ
"አንዴ ተናግረዋል እኔነኝ ስም ያወጣውለት ብለዋል "አልኳቸው ።እናቴ እንደመንገዳገድ እያረጋት መጣችና ሽማግሌውን በትኩረት አየቻቸው ። ድንጋጤዋ ጨመረ የለበሱትን ቲሸርት በጎን በኩል ገለፅ አድርጋ አንድ ምልክት አየች ከዛ በዋላ "ግዛው !!!!!!"ብላ ጮሃ ወደመሬት ወረደች መሬት ከመንካቷ በፊት ሽማግሌው ፈጥነው ያዟት ..........

Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj