Get Mystery Box with random crypto!

'የትናየት ካንቺ የምትፈልገው ይህንን ነው... ማለትም ፀብ.... ከሷ የተሻልኩ ነኝ ብለሽ ካሰብሽ | አትሮኖስ

"የትናየት ካንቺ የምትፈልገው ይህንን ነው... ማለትም ፀብ.... ከሷ የተሻልኩ ነኝ ብለሽ ካሰብሽ እቅዷን ቀድመሽ አክሽፊባት...."

"ማለት..... እንዴት አድርጌ"

"እኔ አግዝሻለሁ..." እንስማማ አይነት እጁን ዘረጋልኝ። ሳላወላውል ጨበጥኩት.... ተገኝቶ ነው ይቺን የሰው ቆንጥር ከአጠገቤ የሚያርቅልኝ

ወደ መነሻ

አስታወሳችሁ መነሻዬን እንጂ መድረሻዬን ሳላውቅ እግሬ ወደመራኝ እየሄድኩ ነው ብያችሁ ነበር። አዎ መንገዴንቨ አላቋረጥኩም። ከእርምጃዬ እኩል ትዝታዬ በልቤ ውስጥ ይፈሳል በአይምሮዬም ውስጥ ይመላለሳል።

ከተማውን ሙሉ ለሙሉ መልቀቄን ያስተዋልኩት ከፊት ለፊቴ ያለው ሰፊ የግጦሽ ሜዳ ላይ የእረኛዎችን ድምፅ ስሰማ ነው።

ድንገት እኔን አልፎ ሲጥጥ ብሎ የቆመ መኪና ከሀሳቤ አንቅቶ አስበረገገኝ። ቅድም ሳይገጨኝ ያለፈው መኪና.... ከውስጡ አንድ ሰው ወረደና ወደኔ መጣ። በድንጋጤ ደርቄ ነው የቀረሁት

"ህያብ በዚህ መልኩ አገኝሻለሁ ብዬ አልጠበኩም ነበር" አጠገቤ መጥቶ ክንዴን ያዘኝ ልክ እንደመጀመሪያው ቀን ልዩነቱ ያኔ ከኋላ አሁን ግን ከፊት ለፊት መሆኑ ነው

"ቅድም አንተ ነበርክ"

"አዎ ግን አንቺ መሆንሽን ለመለየት ጊዜ ወሰደብኝ ህያቤ በጣም ተጎሳቁለሻል አንቺ እንደሆንሽ ያወኩት "ዞር በሉልኝ አስማሳዮች" ብለሽ ስትናገሪ በሰማውት ድምፅሽ ነው አረማመድሽ ደግሞ አረጋገጠለኝ። እናም ተከተልኩሽ.... የምትሄጅበትን መድረሻሽን ለማወቅ ተከተልኩሽ ግን እንደማየው.......

"ቢኒ እኔ...." ቃላቶቼ አፌ ላይ ተንገዋለሉ። ወደራሱ አስጠግቶ እቅፍ አደረገኝ።

"እሽሽሽሽሽሽሽ ይገባኛል ምንም አታስረጂኝ"

በህይወት መንገድ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ተገናኘን..... እኔና ቢኒ

ይቀጥላል