Get Mystery Box with random crypto!

#ህያብ ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ #ድርሰት_በኤርሚ ነሀሴ መጨረሻ ላይ ውጤት መጣ ተባለና አየን | አትሮኖስ

#ህያብ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በኤርሚ

ነሀሴ መጨረሻ ላይ ውጤት መጣ ተባለና አየን ጥሩ ውጤት ነው ያመጣሁት ግን ሩቅ ሀገር ነው የመደቡኝ ጎንደር ዩንቨርስቲ በምፈልገው ዲፓርትመንት(ህክምና)

እናቴን እና ልጄን ትቼ እንዴት ችዬ ይህን ያክል እርቃለሁ.. ትምህርቴን መተው እናቴን እንደመቅበር ነው። ሁላችንም ቢከብደንም ግዴታ ሄጄ መማር አለብኝ።
.....
ስራ ቦታዋ ሄጄ ለእናቴ ስነግራት እልልታዋን አቀለጠችው። ደንበኞቿ ምን እንደተፈጠረ ሲጠይቁኝ ነገርኳቸው እንኳን ደስ ያለሽ እያሉ እናቴን አቀፏት..... ከሁኔታቸው እኔ ሳልሆን እናቴ ውጤት የመጣላት ነበር የሚመስለው....
......
ቤት ውስጥ ጎረቤቶቻችንና አንዳንድ የእናቴ ወዳጆች በተገኙበት መጠነኛ የሽኝት ዝግጅት ተደረገልኝ። ልለያት እንደሆነ ያላወቀችው ልጄም ከኔ እኩል ፍንድቅድቅ ብላለች። እንግዶች በልተው ማዕዱ ከፍ ካለ በኋላ እናቴ ወደ መሀል ወጣችና
"አንዴ ፀጥታ...." ብላ ጨብጨብ ስታደርግ ሁሉም ሰው ባንዴ ዝምምም አለ።

"በህይወቴ እንደዛሬ የተደሰትኩበት ቀን የለም ... ልጄ ዩንቨርስቲ ገባችልኝ። ይሄ ከምንም በላይ ትልቁ ህልሜ ነው። እዛ ሄዳ በስኬት እንደምትመለስ እተማመንባታለሁ። ትልቅ ነገርም ባይሆን ይሄን ስጦታ በእናንተ ፊት እሰጣታለሁ" ወደኔ መጥታ ጉንጬን አገላብጣ ከሳመችኝ በኋላ የተጠቀለለውን ስጦታ ሰጠችኝና"ክፈቺው..." አለችኝ። የተጠቀለለበትን ወረቀት ስከፍተው ሞባይል ከነ ቻርጀሩ ብቅ አለ። አላመንኩም እናቴ ለኔ የእጅ ስልክ ገዛችልኝ... በዚያን ጊዜ አብዛኛው ሰው ባለ ሞባይል እየሆነ ቢሆንም እኔ ይኖረኛል ብዬ ግን አላሰብኩም ነበር።

"አመሰግናለሁ እናቴ.... ደግሞ ቃል እገባልሻለሁ... አኮራሻለሁ"

"እተማመንብሻለሁ የኔ ጀግና.... ሳትሳቀቂ በናፈቅሺን ሰዓት መደወል ብቻ ነው...."ወደ ደረቷ ወስዳ ጥብቅ አድርጋ አቀፈችኝ። ይሄን እቅፍ እኮ ስወደው..............
ቃል ባትናገር እንኳን በእቅፏ ብቻ ብዙ መልዕክት የምታስተላልፍልኝ ይመስለኛል።
"በርቺ....
ባንቺ እተማመናለሁ....
እኔ አለሁልሽ...
እወድሻለሁ......." ብቻ ስታቅፈኝ ከዚህም በላይ ብዙ የምትለኝ ይመስለኛል።
..............

የምወዳት ልጄን እና እናቴን ተሰናብቼ ወደ አፄ ፋሲል ሀገር ጥንታዊቷ ጎንደር ተጓዝኩ ።
..........

ምዝገባ እና ሌሎች ፕሮሰሶች አልቀው ትምህርት የምንጀምርበት ቀን ደረሰ...... የመጀመሪያ ቀን እንደመሆኑ አብዛኛው ተማሪ ቀድሞ ክፍል ተገኝቷል ከነኛ መሀል አንዷ እኔ ነኝ።
.....
ከደቂቃዎች በኋላ
"ይሄ ሸበላ ብቻ እንዳይሆን የሚያስተምረን" ከኋላዬ ያለችው ልጅ ወደ ጆሮዬ ተጠግታ አንሾካሾከችልኝ። ከንግግሯ እኩል ቀና ብዬ ወደ ፊት ለፊቴ አየሁ..... " ዋው ውበት ..... ዋው ቁመና.... ዋው ደረት...." ብዙ ዋው የሚያስብሉ ነገሮችን ያሟላ ሸበላ ሰው.....
......
"እሺ ዛሬ ብዙም የምንማረው ነገር አይኖረንም እርስ በርሳችን እንተዋወቅና ኮርስ አውትላይን እሰጣችኋለሁ...... እምም ከፊት ልጀምር ስምሽን አስተዋውቂን እስኪ...." ምኑ ነው ምን አለ እስከምረጋጋ እንኳን ሌላ ሰው ቢጠይቅ

"ህያብ በዛብህ እባላለሁ የመጣሁት ከአዲስ አበባ" ጣቱን ከኔ ቀጥሎ ወዳለችው ልጅ ጠቆመ

"መቅደስ ገዛህኝ..... ከሀዋሳ
ተፈሪ ይልማ...... ከደሴ
አብሳላት አበበ.... ከአዳማ
የትናዬት ዘመረ..... ከአዲስ አበባ......" ሁሉም ስማቸውን እና የመጡበትን ከተማ ተናገሩ ሁላችንንም ከሰማ በኋላ

" የኔ ስም ደግሞ ዮናታን ይባላል የ...." ከዚህ በኋላ ያለውን አልሰማሁትም .... ዮናታን.... ዮኒ ስሙ ደስ ይላል መልኩም ደስ ይላል። ሳላውቀው ስለሱ ብዙ አሰብኩ.... እጄ ላይ ያረፈ ወረቀት ከሀሳቤ አነቃኝ

"ያልኩትን ሰምተሽኛል ህያብ" ድንብርብሬ ወቶ አይን አይኑን አየው ጀመር እሱም ትንሽ ካየኝ በኋላ

" ተወካይ እስክትመርጡ ድረስ አንቺ ተወካይ ሆነሽ እነኝህን ወረቀቶች ለሁሉም አዳርሺ...." መልሴን ሳይጠብቅ ክፍሉን ለቆ ወጣ። እንዴ ቆይ ደግሞ ስሜን እንዴት ባንዴ ያዘው..... ይገርማል
........
" እና እኔንም አፈዘዘኝ እያልሽኝ ነው" አለችኝ ከፊት ለፊቴ መጥታ

"ይቅርታ እህቴ ምን......"

."ቅድም አልሰማሽኝም የትናየት.... የትናዬት ነው ስሜ"

"እሺ የትናዬት የምትይው አልገባኝም"

"ቀስ ብሎ ይገባሻል ለማንኛውም የራሴን ልውሰድ." አንዱን ወረቀት አንስታ እየተቆናጠረች ከክፍሉ ወጣች።

"ወይ አምላኬ ስንት አይነት ሰው አለ" ብዬ ስዞር ሁሉም አፍጠው የሚያዩኝ እኔን ነው።

ህይወት ልክ በምኞታችን ውስጥ እንዳሰብናት ቀላልና ጣፋጭ አይደለችም። ልንመራት ያወጣነውን እቅድ አስጥላ በራሷ ምህዋር ላይ ታሽከረክረናለች። እምቢ ብለን ብናስቸግራት እንኳን ወይ ከራሳችን እቅድ ወይም ሽክርክሪቱ ከሚያመጣው ነገር ሳንቋደስ ሜዳ ላይ እንቀራለን።

ዩንቨርስቲ መግባትን ሳስብ የሚታየኝ ጠንክሮ መማርና መማር ብቻ ነበር። ግቢ ውስጥ ሆኜ ከትምህርቴ የበለጠ ቦታ እሰጠዋለሁ ብዬ የማስበው ምንም ነገር አልነበረም። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ የሆነ ሰው መጥቶ ይህን ጥያቄ ቢጠይቀኝ በመጠየቁ ልናደድበት እችል ነበር። ዛሬ ግን ያን እምነቴን የትላንት እቅዴን ሊያከሽፍ የሚችል ፍቅር ያዘኝ። ያውም ውድድር የበዛበት ፍቅር.....
አብሬው ልሁን ብዬ ባስብ እንኳን ከሱ እኔን አለማፍቀር ውጪ ከደርዘን በላይ ሴቶች ጋር መጋፈጥ ይኖርብኛል..... ያውም እኔ የማውቃቸው ብቻ።

ያለኝ አማራጭ አንድ ብቻ ነው ቢከብደኝም ስሜቴን አምቄ መያዝ እና በሰላም ትምህርቴን መቀጠል። ምንም ሳይተነፍሱ ሁሉንም በልብ መያዝ ከምንም በላይ ህመም ነው.... በተለይ ደግሞ ፍቅር ሲሆን...

ብዙ ጊዜ ይሄን አስባለሁ ለእናቴ ይሄ አይገባትም አይደል? ... ስኬቴን ለምትናፍቅ እናቴ ስል ከመጋፈጥ ይልቅ መሸሽን መርጫለሁ። የምሸሽበት ምክንያት ዋናው ቁም ነገሩ እኮ ማፍቀሬ አይደለም ፍቅር በየትኛውም ጊዜ እና ሁኔታ ውስጥ ሊከሰት የሚችል ስሜት ነው። ችግሩ ለዚህ ፍቅር ስል ብፋለም ለትምህርት የሚሆን ነፃ አይምሮ ላገኝ እችላለው ወይ? የበለጠው ችግር ደግሞ ያፈቀርኩት ሰው ሁሉንም ቀማሽ መሆኑ ነው።
፧፧፧፧፧፧
ከዛን ቀን ጀምሮ ማለትም ከመጀመሪያ የትምህርት ቀናችን ጀምሮ በዮኒ ፍቅር ተለክፊያለሁ። ፍቅር እንደያዘኝ እንኳን እያወኩ ላለማመን ከራሴ ጋር ለወራት ተከራክሪያለሁ። የትናዬት በየቀኑ እኔን ማስበርገግ ስራዬ ብላ ከያዘች ቆይታለች። በተለይ ዮናታን አስተምሮን ሲወጣ ወይ ከጎኔ ናት ወይም ከፊት ለፊቴ.... እልፍ ጊዜ እኮ አብረው አይቻቸዋለሁ... ብዙ ጊዜ ቢሮው ስትገባ ያዩዋት ነግረውኛል...... እኔ ደግሞ በተቃራኒው ከሱ ጋር የሚያገናኘን ድልድይ ሁላ ላፈርስ የምሞክር ሰው ነኝ። ለምን ይሄን ያክል የቤት ስራ እንደሆንኩባት አላውቅም። አሁን ግን መሮኛል ፀብ ላለመፍጠር እያልኩ እንደፈሪ መታየት መሮኛል።

ዛሬም እንደለመደችው ከጥሩ ትወና ጋር የአሽሙር ንግግሯን ተናግራኝ ከክፍሉ ወጣች። ብሽቅ ብዬ ወረቀቶቼን ሰብስቤ ተከትያት እየወጣሁ እያለ አንድ ሰው ከኋላዬ ያዘኝ። ዞር ስል ቢኒ ነው ከተማሪዎች ሁሉ የተለየው ዝምተኛ ልጅ።

"አቤት ቢኒ" አልኩት ኮስተር ብዬ... ግንባሬን አይቶ እጁን ከክንዴ ላይ አነሳ እና

"ይቅርታ ህያብ.... ጣልቃ ልገባ ፈልጌ አይደለም ግን እኔ የታየኝን አንድ ነገር ልበልሽ..."

"ምን"