Get Mystery Box with random crypto!

የእናቴ ልጅ ክፍል ሃያ አምስት ጨለማውን ፈራውት አፉን ከፍቶ ሊበላኝ የተዘጋጀ | አትሮኖስ

የእናቴ ልጅ
ክፍል ሃያ አምስት

ጨለማውን ፈራውት አፉን ከፍቶ ሊበላኝ የተዘጋጀ መሰለኝ ፡ ለማንም የማይመለሰው ልቤ ተልፈሰፈሰብኝ ፡ እናቴን ሳስባት ደሞ ይበልጥ ሆዴ ባባ ።አቅም አጥቼ በተዘረርኩበት መሬት ላይ ሆኜ ስለሷ አዘንኩ ። ደጋግማ አስጠንቅቃኝ ነበር 'ወንድምህን መውደድ ትችላለህ ግን እንዳታምነው ተጠንቀቅ ከኔ ከእናቱ የበለጠ ወዳጅ የለውም ነገር ግን ለኔም አይመለስም' የሚለው የናቴ ንግግር ጆሮዬላይ አቃጨለ ፡ እራሴን ለማበረታታትና ለመነሳት ሞከርኩ  ነገርግን ተህዛዝ የተቀበለው ልጅ በርግጫ ብሎ አስተኛኝ ምቱ አይለኛ ነው  በጣም አመመኝ ጥርሴ ተናጋ ከአፌ ደም ሲፈስ ይሰማኛል ።
"አዝናለው እኔ እንዲ እንዲሆን አልፈለኩም ፡የወንድምህ ትህዛዝ ነው ፡ እንዲ ካላደረኩ ደሞ የማጣው ነገር አለ "አለኝ ።ድምፁን አወኩት ፡በስልክ ወንድምህን ይዘውታል ያለኝ ሰው ነው ። በራሴ ተናደድኩ እንዴት የእናቴን ማስጠንቀቂያ ችላ አልኩ ፡ይህ ሰው ስልኬን ከየት አምጥቶ ሊደውል ይችላል ።አቤል እስካልሰጠው ድረስ ፡እንዴት አልመረመርኩም ።
"ይኽውልህ ወንድም በፍፁም ወደውጪ የመሄድ እቅድ የለውም እሱ የሚፈልገው እዚሁ ቀርቶ ለብቻው የእናቱ ወራሽ መሆን ብቻ ነው  ያደሞ አንተ እስካለህ አይሆንም ስለዚህ አንተ ዞር ማለት አለብህ ለዚ ደሞ ከኔ ጋር ስምምነት ደርሰናል ፡ ከሚያገኘው ውርስ አንድ ሦስተኛው የኔ ነው የሚሆነው ፡ ይህን ስምምነት  እውን ለማድረግ ደሞ እኔ ስራዬን መጨረስ አለብኝ ፡እና በጣም ይቅርታ አድርግልኝ በሰላም ልሸኝህ እገደዳለው "ብሎ ከለበሰው ኮት ኪስ ውስጥ በጨለማውስጥ የሚያብለጨልጭ ስለት አወጣ ፡እናም በአይል ወደኔ ሲሰነዝር አይኔን ጨፈንኩ ፡ ስለቱ ግን ሲወድቅ ተሰማኝ እሱም ከፍተኛ ድምፅ አሰማ ፡በፍጥነት አይኔን ገለጥኩ ፡ለማመን በሚከብድ ሁኔታ ፡ባለጩቤው የአቤል ቅጥረኛ መሬት ወድቋል ፡በሱ ፈንታ ሌላ ሰው ወፍራም ዱላ ይዞ ወደኔ አጎንብሶ እየነካካኝ ቁና ቁና ሲተነፍስ አየው ፡ ሰውዬው ከወደቀው ሰው የሞባይል ስልኩን ወሰዱና ፊቴላይ አበሩብኝ እና "ልጄ የኔ ልጅ ናቲ ደና ነህ ደርሼልሃለው ለትንሽ ነው እኮ የቀደሙኝ  አብሬህ መሮጥ ባለመቻሌ ነው ወይኔ "አሉ ።አወቅኳቸው ቤታችን የሚመጡት ሽማግሌ አቶ መብራቱ ። በጣም ተደነቅኩ በዚ ሰአት እሳቸውእዚ ምን ይሰራሉ ።እጃቸውን ሰጡኝ እጃቸውን ለመያዝ ሞከርኩ አቅም አጣው "የኔ ልጅ ለእናትህ ስትል በርታ እባክህ "ብለው እጄን ይዘው ሊያቆሙኝ ታገሉ ፡ እናም ተሳክቶላቸው አነሱኝ ፡እሳቸው እራሳቸው ቆፍጠን ብለዋል እንዲ ጠንካራ አይመስሉም ነበር ፡ እኔን እንደምንም ወደ እራሴ እንድመለስ ጥረት አደረጉ ፡ ብዥ ቢልብኝም እራሴን ችዬ ቆምኩ ፡
"መራመድ የምትችል ይመስልሃል "አሉኝ
"እእኔጃ እየዞረብኝ ነው"አልኳቸው
"እኔን ለኔ ይዙርብኝ ልጄ "አሉኝና በዱላ ያጋደሙትን ቅጥረኛ ጎንበስ ብለው በፊትለፊቱ ገለቀጡት እናም የለበሰውን ሸሚዝ ይዞት በነበረው ስለት ቀደው ካወለቁት በዋላ ጭንቅላቴን ጥምጥም አድርገው አሰሩኝ እንዲ ካደረጉልኝ በዋላ ጠንከር አልኩ ከአፌ የሚወርደው ደምም ቀንሷል ፡
"አሁን መጠንከር አለብህ ወንጀለኛውን ፊትለፊት ለማጋፈጥ ፡መጎበዝ አለብህ ፡ይህንን የማይረባ ነብሰገዳይ ፡የምንደብቅበት ቦታ ብናገኝ ጥሩ ነበር  ምክንያቱም በወንድምህ ላይ የሚመሰክረው ብቸኛው ተባባሪ ነው "አሉኝ ይሄንን ስሰማ ለማመን ከበደኝ እሳቸው ወንድሜ እንዳለበት በምን አወቁ ።አፍጥጬ ሳያቸው
"ይገባኛል ደና ስትሆን ለጥያቄዎችህ ሁሉ መልሱን እሰጥሃለው ፡አሁን ግን ይህ ልጅ ከመንቃቱ በፊት ወስደን የምናቆይበት ቦታ ቢኖር ጥሩ ነበር "አሉኝ
"እእሺ ወወደቤት ይይዘነው እንሂድ "አልኳቸው እንደምንም ቃላቶቼን እየጎተትኩ ፡በዛላይ መንፈሴ የሌለ ነው ስብር ያለው ፡
"እንዴ ቤት እናንተ ጋር "አሉኝ በመጠራጠር
"አዎ"አልኳቸው እሳቸው እንዳሉት ልጁ እንዲያመልጠኝ አልፈለኩም ፡ በጭራሽ አቅም አጥቼ እንጂ እዚው ቦጫጭቄ ብጥለው እወድ ነበር ነገር ግን ሰውነቴ ሁሉ ዝሏል ብዙ ደም ሳይፈሰኝ አልቀረም
"ግን እንዴት "አሉኝ
"በመጀመሪያ እኔ ወደ ቤት እሄዳለው እርሶ ከዋላዋላ ተከተሉኝ ምን አልባት ሊፈልጉኝ ወጣ ካሉ ለመጠንቀቅ ነው በር አካባቢ ማንም ከሌለ ወደጊቢ ይዘነው ገብተን ሰርቢስ ቤት እንቆልፍበታለን "አልኳቸው  በአሳቤ ተስማሙ እና ገዳዬን አንስተው እየጎተቱ መራመድ ጀመሩ ፡የጥንካሬ አቸው ሁኔታ አስገረመኝ ፡ ገዳዬን የመቱበት ዱላ ምንኛ አይለኛ እንደሆነ ያስታውቃል እኔ ተደግፌበት እየሄድኩ ነው ከባድ ነው እሱም እንደኔ ደሙ እየወረደ ነው ፡ ቤት አካባቢ ስንደርስ ገዳዬ ነቃ ፡እናም ሽማግሌውን ታገላቸው ፡እሳቸውም የዋዛ አይደሉም ዝም የማይል ከሆነ ጉሮሮውን እንደሚበጥሱለት ተናገሩ ድምፃቸው እንኳን ለሱ ለኔም አስፈራኝ ፡ ፀጥ አለ ጩቤውን ጎኑላይ ሻጥ እንዳደረጉት"ምንም አይነት ድምፅ ሳታሰማ ተንቀሳቀስ ፡ቀጥል ፡አለበለዚያ ያው ልጄን ታውቀዋለህ አሁን ጠንከር ብሎ ቆሟል እድሜለኔ በል ቅድም ገና መሬት ሰትወድቅ ተነስቶ ይገልህ ነበር "አሉት ወደኔ እያሳዩት ፡አይኑ ወደ እኔ ተቁለጨለጩ ፡ፈራኝ ፡ የጊቢያችን በርላይ ደርሰን ቆም አልን ማንም አልወጣም ፡ ደስ አለኝ ለነገሩ አቤል አንድ ነገር ፈጥሮ ነው እንዳይወጡ ያደረጋቸው ፡ይሄ ከይሲ ልቤ የመጨረሻ ጠላው ፡ለሱ የነበረኝ ነገር እንዳለ ተቆርጦ ሲወድቅ ተሰማኝ ።ጊቢ ገቡ ተን በቀስታ ከዚበፊት አቤልን ካሰርኩበት ሰርፒስ ቤት አስገባነው ከነ ማስጠንቀቂያው ።አርፎ ከተቀመጠ ከሱጋር ምንም ፀብ እንደማይኖረኝ ነገርኩት ፡ በፍርሃት አንገቱን ወዘወዘ ፡።
ከዛ ወደ ትልቁ ቤት ከሽማግሌው ጋር ሄድን በመጀመሪያ ሽማግሌው በሩን ሲያንኳኩ
"ጭራሽ ታንኳኳለህ እንዲ አስጨንቀኽኝ ናግባ አሁን ሆሆ"አለች እናቴ ሽማግሌው
"እኔ ነኝ "ብለው ሲገቡ
"ምን እርሶ እንዴት ገቡ ቁልፍ ከየት አመጡ"በጭንቀት ተናግራ ሳጨርስ
"አንተ ለማኝ በዚ ሰአት ደሞ ምን ትሰራለህ "አለ አቤል በድንፋታ
"እኔም አለው እናቴ "ብዬ በደም የተበከለ ሰውነቴን ይዤ ስገባ እናቴ ኡኡ ታዋን አቀለጠችው ደግነሽም ተከተለች ባዩሽም አልቀረች ። ሽማግሌው ሰው እንዳይሰማ እያሉ ተከላከሏቸው እንደምንም እንዲረጋጉ አድርገው ይልቅ ደሙን እንጠበው ።አሉ እናቴ ዱርዬዎች ናቸው ልጄን ያጠቁት ብላ ሽማግሌውን በጥያቄ አጣደፈች እሳቸው መልሰሰ ከመስጠት ይልቅ አቤል ላይ በቁጣ እንዳፈጠጡ ቀሩ አቤል እኔን በማየቱ እራሱን ሊስት ምንም አልቀረውም ፡ ..............

Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj