Get Mystery Box with random crypto!

የእናቴ ልጅ ክፍል ሃያ አራት አንዳንድ ጊዜ አለ ልብህ አስቀድሞ አንዳች አደጋ | አትሮኖስ

የእናቴ ልጅ
ክፍል ሃያ አራት

አንዳንድ ጊዜ አለ ልብህ አስቀድሞ አንዳች አደጋ እንደመጣ እና አስቀድመህ እንድትጠነቀቅ  የሚያሳስብህ ጊዜ ። ጭንቅ ጭንቅ ይልሃል፣ ፍርሃት ይወርሃል፣ ያቁነጠንጥሃል ፣ ብቻ እንዲ አይነት አጋጣሚ አለ ።
አቤል ከወጣ ጀምሮ አይምሮዬ አላረፈም ማን ይሆን የጠራው ፣ምን ሊፈጠር ይሆን እያልኩ ማሰቤን አልተውኩም ። እናቴ ከነደግነሽ ጋር እየተጫወተች አልፎ አልፎ ወደኔ አየት ታደርጋለች  በግንባሬ ወደ ውጭ ባሳያትም ኮስተር እያለች አርፈህ ተቀመጥ አይነት ምልክት ትሰጠኛለች ፡  ባዩሽ እላዩዋላይ እንደተጣበቀች እንቅልፍ የጣላትን ማማን ፀጉር እያሻሸች በደግነሽ ወሬ ተመስጣ ታዳምጣለች ፡  እኔ ግን የጫወታቸው እርዕስ እንኳ ምን እንደው በቅጡ አላዳመጥኩም ፡ ከረጅም ቆይታ በዋላ ስልኬ እሪ ብላ ስትጮህ እንዴት ከቂጤ ብድግ እንዳልኩ ፡እንዲ ደንግጬ አላውቅም ። እናቴ የኔ ድንጋጤ ተጋብቶባት
"ውይ ናቲዬ ልጄ እኔ ልደንግጥ "አለች የሷ ድንጋጤ እራሱ እያሳበቀባት ። ስልኬን ከጩኽቷ ለመገላገል አነሳዋት "ሃሉ "አልኩኝ ። በስልኩ ውስጥ የሚንሾካሸክ ድምፅ መጣ
"ናታኒየም ነህ"አለኝ
"አዎ ነኝ ማን ልበል "አልኩት የልቤን ምት ለመቆጣጠር እየሞከርኩ
"እኔን አታውቀኝም እባክህ መምጣት ትችላለህ ወንድምህን ይዘውታል  "አለኝ ። አይኖቼ ፈጠጡ
"መጣው ስልኩን እንዳትዘጋው "አልኩት ፡የማላውቀውን ሰው ። ይህን ያደረኩት እናቴን ላለማስጨነቅ ነበር  ሁሉም ወደኔ ሲያፈጡ ።
"ተረጋጉ የአቤልን መሄድ ድንገት የሰማ ጓደኛው ነው እኔንም ስለሚያውቀኝ ፡ወቀሳ ሊያቀርብልኝ ነው ለማንኛውም መጣው በሩ ላይ እየጠበቀኝ ነው እንደውም አቤልን በዛውም ይዘነው እንመለሳለን አታስቡ "ብያቸው ወጣው እናቴ ለማመን የተቸገረች ይመስላል በቀላሉ የምትሸወድአደለችም በእርግጥ ።
ከግቢ እንደወጣው ያልተዘጋውን ስልኬን ወደጆሮዬ አስጠግቼ "እሺ ማነህ አንተ ተናገር አሁን ከቤት ወጥቻለው  በግልፅ ምንድነው የሆነው "አልኩት ማነው እንዲ የተዳፈረኝ እኔ እኮ ናታኒየም ግዛው ነኝ ፡እንዴት ወንድሜን ይይዙታል ለዛውም በዚ ቀን እንዴት በንዴት ጦፍኩ
"እኔ ማንነታቸውን አላወቅኩም እኔና አቤል ተገናኝተን ነበር ሰላም ብሎኝ እንዳለፈ ጩኽት ሰማው ወደዋላዬ ስመለስ ሦስት ሰዎች ናቸው ይዘው ሲያዋክቡት አየው  በጣም ስለደነገጥኩ ጥጌን ይዤ ዝም አልኩ "አለ የሚያወራውን ለመመርመር ጊዜ አልነበረኝም እንዳለ ጭንቅላቴ ወንድሜጋር ነው አንድ ነገር ከመሆኑ በፊት ልደርስለት ብቻ ነው ያሰብኩት
"እና ወዴት ነው የወሰዱት በጋሽ ከድር ሱቅ በኩል ወደታች እየገፈታተሩ ነው የወሰዱት በፍቃደኝነት እየሄደ ስላልሆነ ልትደርስባቸው ትችላለህ ፍጠን እኔም  እዛው አካባቢ ነኝ "አለኝ ።ልቤ ፍጠን በሚል ምቱን ጨመረ ደሞ ለክፋቱ የመንገድ መብራት ጠፍቷል ፡ እየተወለካከፍኩ እሮጥኩ  ። ስሮጥ ከዋላዬ ሰው የተከተለኝ መሰለኝ እና ለአፍታ ዞር አልኩ ስዞር ቀስብሎ የሚራመድ ተለቅያለሰው ያየው መሰለኝ ።ችላ ብያቸው እሮጥኩ በስልክ የተጠቆምኩቀት አካባቢ ደረስኩ ጨለማው ከማየሉ ውጪ ምንም ነገር አይታይም  ። እጠብቅሃለው ያለው በስልክ ያናገረኝም ሰው የለም ፡ ነር ግን በጨለማው ውስጥ ዝምብዬ እሮጥኩ ወንድሜን በደስታው ቀን ምን ሊያደርጉብኝ ነው ። እያልኩ  ብዙ ከደከምኩ በዋላ ለምን ስልክ አልደውልም ብዬ ስልኬን ከኪሴ ለማውጣት ቆም አልኩ ። በዛው ቅስበት አንዳች ነገር አናቴ ላይ አረፈ ምቱ አይለኛ ስለነቀረ መቋቋም አልቻልኩም ተንገዳግጄ መሬት ላይ አረፍኩ ፡ ከተኛውበት ሆኜ ለማየት ሞከርኩ ፡ሁለት ወጣቶች ናቸው በግልፅ አልታዩኝም ፡ ጠጋ ብለው ። ካዩኝ በዋላ በቃ በትክክል መጨረስህን እርግጠኛ ሆነህ ደውልልኝ እኔ መሄድ አለብኝ ፡ አለው አንደኛው እየተንሾካሸከ ቢሆንም ድምፁ አልጠፋኝም ፡ መናገር ግን አቃተኝ ዕንባዬ ወረደ አለቀስኩ ከምር .......


,ደራሲ Unknown


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj