Get Mystery Box with random crypto!

#ህያብ ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #ድርሰት_ኤርሚ ከቤት ስወጣ ማንም ያየኝ የለም ለነገሩ ማን ሊ | አትሮኖስ

#ህያብ


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_ኤርሚ

ከቤት ስወጣ ማንም ያየኝ የለም ለነገሩ ማን ሊያየኝ ይችላል... እንደሚሰበር እንቁላል የሚንከባከቡኝን ሁሉ አጥቻለው..... እየሄድኩ ነው....መነሻዬን አስታውሳለሁ መድረሻዬን ግን እንጃ.....

ማሰብና ማስታወስ ቢደክመኝም አይምሮዬ ወደማልፈልገው ጊዜ ሽምጥ ጋለበ.... ወደዛ የሁሉም ነገር ጅማሬ የመከራዬ ሀ ወደሆነው ጊዜ....

በአንድ አነስተኛ የገጠር ከተማ ውስጥ ከእናቴ ጋር ነበር የምኖረው። አባቴን ገና በልጅነቴ ነው በካንሰር በሽታ ያጣሁት። የልጅነት ጊዜዬን እንደማንኛውም ልጅ በጨዋታ እና በሳቅ ነው ያሳለፍኩት። ምንም እንኳን በቤታችን ብዙ የጎደሉ ነገሮች ቢኖሩም እናቴ ለኔ ደስታ አብዝታ ትደክማለች።

ፓስቲ እና ጠላ በመሸጥ ለኔም ሆነ ለሷ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ታሟላለች። ሁል ጊዜም ባይሆንም ችግር እና ረሀብ አልፎ አልፎ ቤታችንን ያንኳኳል፤
እናቴን ሲያማት.....
.....
በዛን ሰዓት ምን እንደሆነ ባይገባኝም እናቴን አልፎ አልፎ ከበድ ባለ ሁኔታ ያማት ነበር። አንዴ አሟት ከተኛች ሳምንት እና ከዛ በላይ ያስተኛታል። ሀኪም ቤት እንድትሄድ ደጋግሜ ብጨቀጭቃትም የሁል ጊዜም መልሷ አይሆንም ነው፤ ብያት ብያት እምቢ ስትለኝ በሚያማት ሰዓት ከአጠገቧ ሳልለይ እንከባከባት ነበር።
....
ከእለታት በአንዱ ቀን ከትምህርት ቤት ስመለስ በራችንን ተዘግቶ አገኘሁት.... እናቴ በዚህ ሰዓት የጠላ ጣሳዎቿን ደርድራ ፓስቲዋን በርንዳ ላይ እየጠበሰች መገኘት ነበረባት....
.....
በሩን ከፍቼ ወደ ውስጥ ስገባ የሽቦ አልጋዋ ላይ እጥፍጥፍ ብላ ተኝታ አገኘኋት

"እማ ምን ሆነሽ ነው አመመሽ እንዴ?' እጄን ግንባሯ ላይ አድርጌ ትኩሳቷን አየሁ.... በጣም ግላለች

'እማዬ አተኩሶሻል እኮ እባክሽ ዛሬ እምቢ አትበይኝ ሆስፒታል እንሂድ' ከወገቧ ቀና ለማለት ስትሞክር አገዝኳትና ትራሱን ከጀርባዋ አስደገፍኳት....
.....
"አይሆንም ልጄ.... ደግሞ ልሂድ ብልስ በምን ገንዘብ .... ይልቅ መድሀኒት አልቆብኛል ሂጂና ግዢልኝ፤ ይህን ወረቀት ስታሳያቸው ይሰጡሻል...." የሆነች ትንሽዬ ወረቀት ከእጅ ቦርሳዋ ውስጥ አውጥታ ከብር ጋር ሰጠችኝ....
......
..
" በይ ታዲያ መጀመሪያ መክሰስሽን ብይና ነው የምትሄጂው" እሺ ብያት ዩኒፎርሜን ቀይሬ ምግብ አቀረብኩና እምቢ ብትለኝም በግድ እያጎረስኳት ትንሽ አብራኝ በላች።
....
....
ከተማችን ያለው አንድ የመንግስት ፋርማሲ ብቻ ነው። እሱም ለሰፈራችን ራቅ ስለሚል በሩጫ መሄድ ይጠበቅብኛል። የእናቴን ጉንጭ ስሜና ቶሎ እንደምመለስ ነግሪያት እየሮጥኩ ከቤት ወጣሁ
....
....
ነፋሻማው አየር ቀሚሴን ወደላይ እያነሳው እኔም እንዳይገልጠኝ ለመከላከል እየሞከርኩ እየሮጥኩ እያለ አንድ ሰው ስሜን የጠራኝ መሰለኝ። ድጋሚ
" ሚጣ" አለኝ ማነው የጠራኝ ብዬ ዞር ስል ሸክም ከአጠገቡ ያስቀመጠ ጎረምሳ ልጅ እጁን አውለበለበልኝ። አቅጣጫዬን ቀይሬ በፍጥነት አጠገቡ ደረስኩና
' አቤት የሚያሸክምህ አጥተህ ነው አልኩት' ከሁኔታው ሳየው ምኑም የኛን ከተማ ሰው አይመስልም ምናልባት ከሌላ ቦታ ለስራ መጥቶ ይሆናል ብዬ መላ ምቴን አስቀመጥኩ።
...
...
ያልገባኝን ፈገግታ ከለገሰኝ በኋላ "አዎ ሚጣዬ እስኪ አሸክሚኝ" አለኝ።
'የምችለው አይመስለኝም ግን እሺ ልሞክር' አልኩትና ጎነበስ ብዬ ሸክሙን ያዝ አደርኩና ቀና ብዬ አየሁት የማይገባኝን አስተያዬት እያየኝ ነው።
'ምነው መሸከም አትፈልግም እኔ እቸኩላለሁ ለእናቴ መድኃኒቱን መግዛት አለብኝ' አልኩት ቆጣ ብዬ

"አይ እንደዛ አይደለም ይሄን አንቺም ለማሸከም ይከብድሻል እኔም እንጃ የምችለው አይመስለኝም... ውስጥ አነስ ያለ ሌላ ሸክም አለ እንደውም እሱን አሸክሚኝ አይዞሽ አትቆይም" ምላሼን ሳይጠብቅ ፊቱን አዙሮ በጭቃ እየተሰራ ወዳለ ጅምር ቤት ገባ። ዘግዬት ብዬ ተከተልኩትና ወደ ውስጥ ስገባ ዘሎ በጥፊ ደረገመብኝ። ተንደርድሬ መሬቱ ላይ ተደፋሁ.... ለመጮህ አፌን እንደከፈትኩ ፀጉሬን ይዞ አፌ ውስጥ ጨርቅ ጠቀጠቀብኝ።
.....
በመንፈራገጥ እና በድብደባ በዛለ ሰውነቴ ላይ ከላዬ ሆኖ በስሜት ይጨፍራል....
......
ከባድ የሆነ የህመም ስሜት ይሰማኛል........
ቀስ በቀስ በእንባ የራሰው አይኔ መከደን ጀመረ......
ከላዬ ላይ ያለው ሰው ምስል ወደ ብዙ ሰውነት ተቀየረ.......
ከዛ ደግሞ ድብዝዝ እያለ መጣ...... በስተመጨረሻም ድርግም ብሎ ጠፋ...

ጨለማ

ከምን ያክል ሰዓት በኋላ እንደሆነ አላውቅም.... ራሴን እዛ ጅምር የጭቃ ቤት ውስጥ ተኝቼ አገኘሁት። እንደምንም እየተንገዳገድኩ ከቤቱ ውስጥ ወጣሁ... ልብሴ በደም ተነክሯል፣ የሚሰማኝ የህመም ጥዝጣዜ ራሴን ሊያስተኝ ደርሷል ግን እንደምንም ተቋቁሜ ለመራመድ ሞከርኩ።
.....
ብርሀን ለጨለማ ቦታዋን ብታስረክብም ደማቋ የምሽት ጨረቃ አካባቢውን በብርሀን ሞልታዋለች....

በቀስታ እየተራመድኩ ወደ መንገዱ ወጣሁ። አሁንም ደሜ አልቆመም በቀስታ ከጭኔ ላይ ሲወርድ ይሰማኛል። ከሩቅ ነጠላ ለብሶ የሚመጣ ሰው አየሁ አንደበቴን ከፍቼ ለመጣራት መከርኩ ግን በምጥ የወጡት ቃላቶች እንኳን ለሌላ ለኔም የሚሰሙ አልነበሩም።

ያለኝ አማራጭ ወደሚመጣበት አቅጣጫ ተራምጄ እንዲያየኝ ማድረግ ነው። እየቀረብኩት ስመጣ ቄስ እንደሆኑ ተረዳሁ.... አጠገባቸው ለመድረስ ትንሽ ሲቀረኝ ጉልበቴ ተብረከረከ፣ አቅሜ ተሟጠጠ፣ አጠገቤ መጥተው ያዙኝና

" ምነው የኔ ልጅ ችግር አለ ምን ሆነሽ ነው?" ድምፃቸው ከሩቅ የሆነ ያክል ይሰማኛል ። ልቤን ስልብ የሚያደርግ ህመም ተሰማኝ ከዛ በኋላ አላስታውስም
......
"ልጄ የኔ ስስት.... ምን አድርገውብኝ ነው? እባክሽ ተነሽ ሚጣዬ ተነሽልኝ..... የኔ ብቸኛ ልጅ... ያላንቺ ማን አለኝ.... ትተሽኝ እንዳትሄጂ.... ተስፋዬ.... ነገን የማይብሽ.... " አይኔን ሳልገልጥ የሰማኋቸው የእናቴ በሳግና በለቅሶ የታጀቡ ቃላቶች ናቸው... ከዛ ከባዱ ጨለማ ይውጠኛል።
ትንሽ ትንሽ ዙሪያዬ እየተፈጠረ ያለውን ነገር ባውቅም አይኔን ለመክፈት ወሰድ መለስ የሚያደርገኝን ጨለማ እና የተጫነኝ ከባድ ነገር መታገል ግድ ሆኖብኛል።
.....
"አሁንስ አልነቃችም አይደል" አለ የሆነ ጎርናና ድምፅ

" አልነቃችም ኢንስፔክተር ልጄን እንደዚህ ያደረገውን ሰው አገኛችሁት?" እማዬ ናት

" አይ... ወይዘሮ ወይንሸት አላገኘነውም እሱን ለመያዝ የልጆት ቃል ያስፈልገናል" የበር መዘጋት ድምፅ ተሰማኝ እኔም ወደዛው ጨለማ የሄድኩ መሰለኝ.... እንቅልፍ
....

ዛሬ የተሻለ ጥንካሬ ይሰማኛል። ልክ አይኔን ስግልጥ እናቴን አጠገቤ አየኋት የአልጋውን ጠርዝ ተደግፋ እንቅልፍ ወስዷታል። እጄን አንቀሳቅሼ ፊቷን ስዳስሳት ተነሳች... ወዲያው እልልታዋን አቀለጠችው።

"ልጄ ነቃሽልኝ የኔ ስስት.... ተመስገን ልጄ ነቃች" ዶክተሩ ምርመራ እስከሚያደርግልኝ ውጪ እንድትቆይና ነገራትና አንዳንድ ህክምናዎች ካደረገልኝ በኋላ

"ፖሊስ መጥቶ ቃልሽን ይወስዳል... እንደዚ ያደረገሽ አውሬ እንዲያዝ ከፈለግሽ ምንም ሳትፈሪ ሁሉንም ለመናገር ሞክሪ.... ደግሞ አይዞሽ በሚያስፈልግሽ ሁሉ ከአጠገብሽ አለን..." ብሎኝ ክፍሉን ለቆ እንደወጣ ሁለት ፖሊሶች ተከታትለው ገቡ።
....
ከ አንድ ወር በኋላ
የሰፈር ሰው ሰምቶ ስለነበር ግማሹ ሲያዝን ግማሹ ደግሞ የራሱን መላምት ማስቀመጥ ጀመረ።
"ፈልጋ ነው እንጂ ሳትፈልግ ማን ሊነካት..." በነገር የምትታወቀው ብርቄ