Get Mystery Box with random crypto!

የብሌን መኪና ከቤታችን ፊት ለፊት ቆሟል ጥድፍ ጥድፍ እያልኩ ተጠጋዋት የመኪናዋን በር ከፍታ አስገ | አትሮኖስ

የብሌን መኪና ከቤታችን ፊት ለፊት ቆሟል ጥድፍ ጥድፍ እያልኩ ተጠጋዋት የመኪናዋን በር ከፍታ አስገባችኝ ስገባ ያየሚያስደነግጠኝ ፊቷ ቀረበኝ
"አንተ የመጨረሻ የምታናድድ ልጅ "አለችኝ
"ምን አደረኩ "አልኳት
"ለምንድነው ስልክ የምትዘጋው በጣም ነው የተበሳጨውብህ ግን ሳይህ እረሳውልህ "ብላ ጉንጬን ሳመችኝ ኡፍፍፍፍ እሳቷን ለቃ ምንም እንዳልተፈጠረ ነው የምትሆነው
"ቻርጅ ጨርሶ ይሆናል "አልኳትና ጉንጬን ዳበስኩ
"እና ቻርጅ ማድረግ ነው እኔ መጥቼ ላርግልህ እንዴ"
"አይ እኔ አደርገዋለው"
"አድርገዋ ታዲያ"ብላ ተጠጋችኝ
"ተይ በቃ አታስጨንቂኝ እንዴ ማታ ኳስእያየው ስለነበር እረስቼው ነው ያደርኩት"አልኳት እኔን ማሳፈር ደስ ይላታል ፡
"ኪኪኪኪ ደስስስ ይለኛል አንተን ማስጨነቅ ፡አሁንማ ይሄንን ሁኔታህን ለምጄው ነው መሰል ከጠዋት እስከማታ ነው የማስብህ "
"ስራ የለሽም ማለት ነው"
"ስራዬ አንተ ሆነሃል ከልቤ ነው እየወደድኩህ ነው መሰል"
"አሂሂሂ ያዋከቡት ነገር ሆኖ በጊዜ እንዳታባርሪኝ "
"እንዳትባረር ከፈለክ ፀባይ ይኑርክ ፡አሁን ለምን ቁርስ አብረን አንበላም "
"አይ ቤት እየጠበቁኝ ነው በዛላይ ሻወር አልወሰድኩም  በዋላ እንገናኝ "አልኳት
ዝምብላ አየችኝ አስተያየቷ አንዳች ነገር የፈለገሰው ይመስላል ስሜት አለው
"ምነው "አልኳት
"ይሄን ሰውነት ያለ ጨርቅ ሳልኩት እናም በቃ......."ብላ ዝም አለች
"አንቺ ልጅ ግን እኔ ማለት ያለብኝን ሁሉ አንቺ ካልሺው እኔ ምን ልል ነው  ግልፅነትሽ በዛብኝ"አልኳት እያፈርኩ
"አንተ ማለት አይጠበቅብህም በታማኝነት ድርጊቱላይ ተሳተፍ ፡ አሁን አንድ ቦታ ብንሄድ በጣም ነበር ደስስስ የሚለኝ ግን ያው በቃ እንዳልክ በዋላ ላግኝህ ስልክህን እንዳትዘጋው ደሞ"አለችኝ
"እሺ አደራ ግን ይሄ የምታሯሩጭኝን ነገር በልኩ አድርጊው "አልኳት ፈገግ እያልኩ
"እጠነቀቃለው "ብላ ጠጋ አለችኝ እናም ሳላስበው ከንፈሬን ምጥጥጥ አድርጋ ሳመችኝ ፡ሰማይ ምድሩ ሲዞር ይሰማኛል ፀሐይ ሙቀቷን እንዳለ ከላይ የለቀቀችብኝ መሰለኝ ኧረ ደግነሽም እልልልልልልልልልልል ያለች መሰለኝ ,,,,

ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj