Get Mystery Box with random crypto!

የእናቴ ልጅ ክፍል ሃያ ሁለት እናቴ  ይዛ የቆየችውን ሚስጢሯን ሁሉ ስለነገረች | አትሮኖስ

የእናቴ ልጅ
ክፍል ሃያ ሁለት

እናቴ  ይዛ የቆየችውን ሚስጢሯን ሁሉ ስለነገረችኝ ከእሷው እኩል ነው እፎይ ያልኩት እሷላይ ያለኝ ጥያቄ ሁሉ ተመልሶልኛል ፡ ነገርግን አዲስ አሳብ ደሞ ተተክቷል ያባቴ ጉዳይ ፡ አባቴን የገለፀችበት መንገድ ብዙም ውበት ባይኖረውም ፡ እሱን በሕይወት ባገኘው ብዬ ተመኘው ፡ ምንገጥሞት ይሆን የት ሄዶ ይሆን ፡ገለውት ይሆን እያልኩ ፡ ማሰቤ አልቀረም ፡ ለእናቴም ብንፈልገውስ ብያት ነበር እሱ የማይሆን ነው እሱ በሕይወት ካለ በፍፁም እኛን ፈልጎ አያጣንም ምክንያቱም እንኳን እኛን ሆነ ብሎ የሚደበቀውን ጠላቱን እንኳ ፈልፍሎ የሚያወጣ ሰው ነው ብላ አሳቤን ውድቅ አደረገችብኝ እናም እኔ ስለአባቴ መሞት በከፊል ይሆናል ብዬ አመንኩ ........
በጠዋት ተነስቼ ጊቢውስጥ እሮጥ እሮጥ እያልኩ ስፖርት እየሰራው ነበር ላለመረበሽ ብጠነቀቅም ፡እናቴ ግን ሰምታኝ ነው መሰል ቱታዋን አድርጋ መጣች ሳኩባት ደሞ እንዴት ነው የሚያምርባት ይሄ ቱታ መቼም ለመዝናናት ነው የሚሆነው ነጭ ከመሆኑ ሰውነቷ ላይ ስትር ማለቱ  እናቴ አልመሰለችኝም ፡ሁላ በዚ ቱታ ስፖርት አያዋጣም አልኩ ለራሴ ፡አጠገቤ ሮጥ እሮጥ እንደማለት ስትል ቀልድ እንደነገሩት ሰው ፍርፍር ብዬ መሳቅ ጀመር ከአለባበሷ ጋር አሯሯጧ ያስቃል "ኧረ እናቴ ምንድነው ማበረታቻ ነው ወይስ ከምርሽን ነው"አልኳት መሮጤን ሳላቋርጥ
"እንዴ ምን ችግር አለው ስፖርት ለጤንነት "ብላ ሳቀች ፡
"ግን እኮ አይን በሚያጠፋ ነጭ ቱታ አይሆንም አታበላሺው ወጣ ስንል ታደርጊዋለሽ "አልኳት
"እ ኪኪኪኪ ስለሌለኝ እኮ ነው ስፈልግ ይሄንን ነው ያገኘውት በተቻለኝ መጠን እንግዲ መሬት አልቀመጥም "ብላ ሳቀች እና ትንሽ ዱብ ዱብ አለች አብራኝ ትንፋሿ ቁርጥ ቂርጥ እያለ ማውራት ሲከለክላት ቆም አለች  ሰውነቷን እንድታላቅቅ እና ለዛሬ እንዲበቃት ነገርኳት ሳያት ግን ዋና አላማዋ እስፖርት መስራት አልመሰለኝም ።ትንሽ ጠበቀችኝና እኔንም አስቆመችኝ እና ጊቢ ውስጥ ካለው አንድአግዳሚ ወንበር ላይ ሄደን ተቀመጥን
"ናቲዬ አንድ ማስተካከል ያለብኝ ጉዳይ አለ እና ጊዜው ደሞ ደርሷል "አለችኝ
"ምንድነው እናቴ አብረን እናስተካክለዋለን ብቻሽን ከአሁን በዋላ አትቸገሪም ማድረግ ያለብኝን ሁሉ ለእናቴ ያለ ገደብ አደርጋለው " አልኳት
"ምን መሰለ ወደፊት ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም ፡እና ስለመገናኛው ቤታችን ነገሬህ የለ ይህንን የምታውቀው አንተ ብቻ ነህ እንደእውነቱ ከሆነ በፊት ላይ ወንድምህ ትክክለኛ አስተዋይ ነገሮችን መቆጣጠር የሚችል ይመስለኝ ነበርና ለሱ ነበር ያንን ቤት ያሰብኩት ነገር ግን አሁን እሱን አሳቤን ትቼዋለው ቅጣቱንም ያገኛል ፡ እና ምን ልልህ ነው መሰለህ ቤቱን ባንተ ስም ማዘዋወር እፈልጋለው ይህንን ስናደርግ ደሞ ማንም እንዲያውቅ አልፈልግም እሺ ፡ወደፊት ትዳር ስትሂዝ ያለምንም የቤት አሳብ እንድትኖር እፈልጋለው ላደረገንህ ነገር ሁሉ መካሻዬ ነው በእርግጥ ዞሮ ዞሮ ያው ለእናንተ ነበር "አለችኝ እጄን ያዝ አድርጋ
"እናቴ ግን አቤል ..."ከማለቴ አቋርጣኝ
"አቤል ማለትህን አቁም እሱን መስተካከል የኔ ፈንታ ነው እሱ የሰራኝን መስማት ከፈለክ  እንግዲ ስማ ፡ አንተ በሌለህበት ጊዜ ቤቴን በቁሜ ሊያሸጠኝ ያላረገው ጥረት የለም ፡ከዚ ከማነው ...ጋሽ ግዛው ከተባለ ሰው ጋር ለዛውም ቤት ድረስ እያመጣው ፡ አይሆንም በማለቴ እንዴት እንደተቀየረብኝ ፡ከዛእንግዲ ያቺ የማማ እናት መጥታ ጉዴን ስትነግረኝ በድንጋጤ እንደዛ ሆንኩኝ እሱ ግን ሁኔታዬ ሳያሳስበው አሳቡ ቤቱ ላይ በመሆኑ ደና አኪም እንኳ አንዳያየኝ ቤት ዘግቶ ትድናለች እያለ አፍኖኝ ነበር  የቤቱን ካርታ ያልፈለገበት ቦታ አልነበረም እንደማልናገር እያወቀ አስሬ ጠይቆኛል በግዴታ ሊያስፈርመኝ አስቦ ነበር ፡እሱ እንደማይሳካለት ሲያውቅ እኔን ተስፋ አሳጥቶ እንድሞትለት በማሰብ ሴት ቤቴድረስ እያመጠ አይኔ እያየ ያሳድር ነበር ።እንደውም ደግነሽ ባትኖር አንቆ ይገለኝ ነበር ብዬ ነው ማስበው አሁንም አስተያየቱን አልወደውም ፡ብቻ ልጄን የቱጋር ስህተት ሰርቼእንዳጣውት አላውቅም አንተ ግን ተጠንቀቅልኝ አደራህን እንዲ ባይባልም እንኳ የእናትህ ልጅ ቢሆንም እንኳ ተጠንቀቀው አደራ ወንድምህን ውደደው ነገርግን ባህሪው ከባድ ነው እሱን ተጠንቀቅ  ከኔ የሚበልጥ ወዳጅ የለውም እናቱ ነኝ ግን ለኔም አይመለስም ፡ስለዚ እኔ አንድ ያሰብኩለት ነገር አለ እሱን አስተካክዬ ከአገር እንዲወጣ አደርገዋለው እስከዛው እራስህን ጠብቅ "አለችኝ ኡፍፍፍፍ ይጨንቃል ወንድሜ ቤቱን በላይዋላይ ስለመሸጥ መደራደር ምን አይነት የገንዘብ ፍቅር ነው የገባበት ፡ከባድ ነው ፡ከእናቴ ጋር ስናወራ ቆየን ስለወደፊቱ ስንመካከር  ስለ እኔም ስትጠይቀኝ ስለ አዲሷ ጓደኛዬ ብሌን ነገርኳት እሷም ሴትልጅን እንዴት መያዝ እንዳለበኝ ስታስረዳኝ ቆየች እነደግነሽ ተነስተው ቁርስ ለመስራት ተፍ ተፍ ሲሉ ማማም ተነስታ ወደኛ መጥታ መጫወት ጀመረች ።አቤል እናቴ የነገረችኝ ነገር ውስጤ ቢቀመጥም ፡አሁን ላይ ያለበት ሁኔታ ግን እንደዛ አይመስልም እሱም እንደተነሳ ሁላችንንም በፍቅር ነው ሰላም ያለን ፡በእርግጥ መች እንደሚናደድ አያስታውቅም ።
በራችን መጥሪያው ሲጮህ በር ሊከፍት በፍጥነት ሲሄድ እናቴ ተስፋ በቆረጠ አተያይ ከዋላው ስትመለከተው ጨነቀኝ በዚመጠን እናቴ አቤል ላይ ትሆናለች ብዬ አላውቅም በጣም ጎድቷታል
"ምን ፈለክ "ብሎ አቤል ሲጮህ እናቴ ወደኔ አየች ተነስቼ ወደበሩ ሄድኩኝ ስደርስ አንድ አባት እየለመኑ ነው ሲያዩኝ ደነገጡ ለሁለት አንድ ነገር የምናረጋቸው ይምሰላቸው እንጃ
"ምንድነው የምትጮህባቸው ስለ እግዚያብሄር የሚልስው በዚ መልኩ ነው እንዴ የምታስተናግደው ኑ ግቡ "አልኳቸው አቤል ጨሰ ሽማግሌው ተርበተበቱ
"ማንንም ግቡ የማለት መብት ያለህ ነው የሚመስልህ "አለኝ ተናዶ
"ድጋሚ መልስ ብትሰጠኝ ከመሬት ነው የማደባልቅህ እሺ ደነዝ አቀመ ደካማ ናቸው ምን ያረጉኛል ብለህ ነው እርቧቸው ይሆናል "አልኩት እና አስገብቼ ጥግላይ አስቀመጥኳቸው አቤል እየተነጫነጨ ሄደ
እናቴ መጥታ ሽማግሌውን እያየች "እንዴ አባባ እርሶ ኖት ለልጄ ይቅርታ ያድርጉለት  ስላላወቀ ነው ደግነሽ ቁርስ ታመጣሎታለች "ብላ ጠቀሰችኝ
"ምንድነው እማዬ ታውቋቸዋላቹ እንዴ "ብዬ ጠየኳት
"ያው እዚ አልፎ አልፎ ይመጣሉ በልመና ነው የሚተዳደሩት አስፖልቱ ጫፍ ላይ ላስቲክ ወጥረው ነው የሚኖሩት ፡እንደውም አንዴ ዝናብ ላስቲካቸውን አፍርሶባቸው ኑ እኔጋር ብላቸው ደግነሽ ብትለምናቸው እሺ አላሉም የሚገባኝን ኑሮ ነው የምኖረው አሉን አቤል ደሞ ጠልቷቸው ሊሞት ነው "አለችኝ ደግነሽ ምግብ በሰአን ጠቅጥቃ መጥታ ሰጠቻቸው ሽማግሌው በዛ ሲሏት ደግነሽ በፌስታሉ እንዲይዙትም ጭምር ነው ፡ዋላ ይበሉታል ብላ ወደስራዋ ተመለሰች ።ሽማግሌው አመሰገኑ ፡አንድ እየጎረሱ እኔን ቀስ ብለው አየት ያደርጉኛል እኔ ደሞ አጠገባቸው ቆሜ በማዘን እያየዋቸው ነው ለምን እንደው አላውቅም አንጀቴን በሉኝ ሽቁጥቁጥ ማለታቸው እረዘም ያለው ቁመናቸው ወደፊት ማዘንበሉ የለበሱት ስስ ቲሸርት የአጥንታቸው መቆጠር ፊታቸውን ሊሸፍነው በተቃረበው ጢማቸው ውስጥ ደከም ያለችው አይናቸው በቃ አሳዛኝ ፍጥረት ናቸው  ምስኪን አልኩ ።የጊቢ አችን በር ሲንኳኳ እዛው ስለነበርኩ ከፍቼ ወጣው አንድ ትንሽ ልጅ ነው ሲያየኝ እጁን ወደ ቆመ መኪና አመላክቶኝ እሮጠ