Get Mystery Box with random crypto!

የ እናቴ ልጅ ክፍል አስራ ሦስት መጥሪያውን ተጭኜ ብዙ ነገር ወደውስጤ ተመላለ | አትሮኖስ

የ እናቴ ልጅ
ክፍል አስራ ሦስት

መጥሪያውን ተጭኜ ብዙ ነገር ወደውስጤ ተመላለሰብኝ ፡ፍርሃቴም ጨመረ ፣የእናቴ ቁጡ ፊት መጥቶ ሲደቀንብኝ ፣ወይም የአቤል ተንኮለኛና ትህቢተኛ ፊት ፣ በአንዴ ተመላለሱብኝ ፣ግን ልቤ እየመታ ከዚአካባቢ ተሰወር ቢለኝም እግሬ ግን አልንቀሳቀስ አለ ፣እግሬ በራሱ መመራት ጀመረደሞ ዛሬ ፣ አስገድዶ ያስቆመኝ መሰለኝ ፡ ከቆይታ በዋላ በሩ ተከፈተ ፡ በሩ ሲከፈት ያየውትን ማመን አቅቶኝ ዝም አልኩ ፡ በንሩ የከፈተችልኝ ተለቅ ያለች ሴትዮ ናት ፡በትንሹ እናቴን ትመስላለች ነገር ግን እናቴ አይደለችም ፡ ግራ ተጋብቼ ፈዝዤ ሳያት
"ምን ፈልገህ ነው ጌታው "አለችኝ ድንግርግር አልኩኝ
"ኧራ አንተው ምን ይዘጋሃን ፡አትናገር ከሆን በሩን መልሼው ልግባ"አለችኝ ፡እናቴ የት ሄዳ ነው በሕይወቴ እኛቤት ሌላ ሰው ገብቶ አይቼ አላውቅም ፡እና ማናት ወይስ አዲስ ፀባይ አምጥታ ብቸኝነት ሰልችቷት ፡ማከራየት ጀመረች ፡ወይስ አቤል ቤቱን አሸጣት ፡ዘገነነኝ ፡"አንቺ ማማነሽ "አልኳት ቀጥሎ የምሰማው ነገር እንዳያሳምመኝ ፡እየፈራው
"ኧራ አንተ እራስ ማነኝ ነው የምትል ፡ምን ፈልገህ ነው?"አለችኝ ትህግስቷ እያለቀ
"እኔ የዘውድነሽ ልጅ ነኝ ፡ናታኒየም እባላለው አንቺ ማነሽ ፣እሷ የት ሄዳ ነው?"ብዬ እየተናነቀኝ አከታትዬ ጠየኳት፡ልክ ተናግሬ እንደጨረስኩ መጮኽ ጀመረች ፡ድንብርብሬ ወጣ ፡ ጩኽቷን ሳታቋርጥ ጎትታ ወደውስጥ አስገብታኝ ተጠመጠመችብኝ፡ጭንቀቴ እና ድንጋጤዬ ይበልጥ ጨመረ ፡
"እናቴስ እናቴ ምን ሆና ነው እባክሽ ?ሞታ ነው አንቺ ማነሽ "አልኳት ከእቅፏ ለመውጣት እየታገልኩ ፡ልክ እንደኔ ግዙፍ ናት ፊቷ ብቻ ነው የሴት ቅርፅ ያለው ፡
"እናትህ አለች መቼስ መኖር ከተባለ ፡ብላ ዕንባዋን ማዝራት ጀመረች ፡ከዚ በዋላ ትህግስት አጣው ፡ሴትዮዋን ባለችበት ጥዬ ፡ወደማውቀው ቤት ሮጬ ገባው ፡ስገባ ያየውት ነገር አሳቆ እና አስደንግጦ ባለውበት አቆመኝ ፡ትልቁ ሳሎናችን ልዩ ሆኖ አምሯል  ነገር ግን ፡ ማሃል ላይ በዊልቸር የተቀመጠች ሴት አለች ፡ ምን ልሁን በቁሜ ነበር ከፊቷ ሄጄ የተንበረከኩት ፡እናቴ  እኔ ዘንበል ልበልላት አንገቷን ወደጎን ዘንበል አድርጋ ተቀምጣለች ፡ ሳላስበው ስሜቴ ፈንቅሎኝ ወጣ ፡ በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፅ አውጥቼ አለቀስኩ ፡ እናቴ እጇ መንቀጥቀጥ ጀመረ  አፍጥጣ ስታየኝ ቆይታ ፡አፏን ለመክፈት ታገለች ፡ልትናገር ፈልጋ ግን አልቻለችም ሲያቅታት የዕንባ ዘለላዎችን ታወርድ ጀመር ፡ ይሄኔ ሴትዮዋ ድንገት ወደቤት ገብታ "እልልልልል ....."ማለት ጀመረች ፡ ቀናብዬ አየዋት ምንድነው እልል ታው የኔ መምጣት ነው  ፡የእናቴን እጅ ያዝኳቸው እንቅጥቃጤ አቸው ለጉድ ነው 
"እሰይ እሰይ ዘውድዬ ተንቀሳቀሰች ፡እንኳን መጣህላት ፡ልጇን ስታይ አነባች "አለች  ተነስቼ ወደ ሴትዮዋ ሄድኩና ያዝኳት"ማነሽ አንቺ ?ምን ሆና ነው?"አልኳት
"ኧረ ዋይ እኔን ልቀቀኝማ ፡ "አለችኝ እያረጋጋችኝ
"እሺ ምን ሆና ነው እናቴ "አልኳት
"እሷማ እንግዲ የዛሬ አመት አካባቢ ነው ፡እኔም እንደው ተቀይማ ከቤተሰቡ ተነጥላ የቆየች እህቴን አፈላልጌ ያገኘውበት ሰሞን ነው ፡ እንደው ይቅርታዋን ተቀብዬ ተደስቼ ፡ ለባለቤቴም ጎጃም ነው የምንኖረው ደውዬ አሳውቄ እህቴን ማገኘቴን ፡ እሱም ፡በደስታዬ ተደስቶ ነበረ ፡መቼም ካገኘዋት በዋላ በቃ እንግዲያውስ ያለችበትን ካወቅኩ ፡ተመልሼ ወዳገሬ ልሄድ እያሰብኩ ፡ እንደው በደንገት አይሆኑ ወነች ዋይ እህቴ ፡  "ብላ ለቅሶዋን ጀመረች
"እሺ ምን ተፈጥሮ ነው "አልኳት ፡አንድም ቀን  እህት አለኝ ስትል ሰምቻት አላውቅም ፡ ለነገሩ መቼ ምን ተናግራ ታውቅና
"እንደው ወደ ማታ ነው አቤልም አልገባ እኔና እሷ እየተጫወትን በር ተንኳኳ ልትከፍት ሄደች ፡እና ብዙ ስትቆይብኝ ምን ሆነች ብዬ ስወጣ ፡ በሩ ላይ ተዘርራ አገኘዋት ፡ እንደው አንዴ ጩኽቴን ብለቀው ፡ እንደው አቤል ከየት መጣ ሳይባል ደረሰልኝ ከዛማ ለሁለት ሆነን ምኑን ከምን እናርገው ፡ ብቻ አቤል ተሸክሟት እኔ ከዋላዋላ ፡ ክኒሊክ አደረስናት ፡ ግን እነሱ የሚችሉትም አልመሰለኝ ፡አንፑላንሱን ጠርተው ከሌላ ወስፒታል ወሰዷት ግን ይኽው እኔ ዝግት ልበል ድንጋጤና አወዳደቋ ከፉመሆን ተጨማምሮ ተዘግታ ቀረች "ብላ ለቅሶዋን ቀጠለች
"እንዴት ማን እንዳንኳኳ አላያችውም ገፍትረዋት ነው"
"ኧረ ምኑን አውቄ  አኪሞቹ ስትወድቅ አናቷን ተመታለች ፡ቀስበቀስ ደናትሆናለች ነው ያሉት ይኽው አመት ሆናት ያው ነው እኔም ከባሌም ተጣልቼ እዚሁ ነኝ እንዴት አንድያ እህቴን እንዲሆና ልተዋት"
"ለፖሊስ አላሳወቃችሁም "አልኳት ግራ ገብቶኝ
"እሱማ እኔ ደጋግሜ ብዬ ነበረ ፡ አቤል ነው ምንም አያረግም ፡ ያለኝ "አለችኝ
"አሁን እሱ የት ነው "ብዬ ጮውኩ ፡ይሄ ተንከሲስ ምን አድርጓት ነው ፡ ድሮም የእናቴና የሱ ግንኙነት በሬ ካራጁ ነው ፡ እናቴን ጠጋብዬ አየዋት በፍቅር አይን ያየችኝ መሰለኝ እጄን እጇ ውስጥ ሳስገባው ያዝ አደረገችኝ ፡ የአቤልን መምጣት በጉጉት መጠባበቅ ጀመርኩ ፡ ወይኔ እናቴን የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ,,,,,,,,,,,,,

ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj