Get Mystery Box with random crypto!

የ እናቴ ልጅ ክፍል አስራ ሁለት አንድ ነገር ስትይዝ ወይም በበነገው የሆነ ጉዳ | አትሮኖስ

የ እናቴ ልጅ
ክፍል አስራ ሁለት

አንድ ነገር ስትይዝ ወይም በበነገው የሆነ ጉዳይ ካለህ ፡ አንተም አትተኛ ሌቱም ቶሎ አይነጋ ፡ የሌለ ነውቅርፍፍ የሚልብህ ፡ በዛላይ እያነሳህ የምትጥላቸው አሳቦች መብዛቱ ፡  በባዩሽ ሁሌም እንደቀናው ነው በነገራችን ላይ ፡ከተኛች  ምንድነው የሚባለው ...አዎ  መትረየስ ቢጮህ  አትነቃም ...ብዙ ጊዜ ማማ ለሊት ጡጦ ፈልጋ ወይም ዳይፐሩ ሲረጥብባት ፡ታለቅሳለች ፡ባዩሽ  አትሰማም ፡ ሐዛ ብዬም ነው  ማማን አዳሯን ከኔጋር የማደርገው ፡ ይህ የለሊቱ የህፃናት መቀስቀስ የሚያውቅ ያውቀዋል ፡ቀውጢ በሆነ እንቅልፍ ውስጥ ስትሆን ፡ የህፃን ለቅሶ ስትሰማ  አስበኽዋል ፡ከዛ ተነስተህ ታባብላለህ ፡አልሆን ይልሃል ወተቱ ማለቁን አስተውለህ ጡጦውን አጥበህ ወተት ትሞላለህ ፡ ዝም አልል ሲሉህ ገለጥለጥ አድርገህ መሽናታቸውን ታያለህ ፡ እናም ተራርሰው ታገኛቸዋለህ ፡ ዳይበር ትቀይራለህ ፡እንቅልፍ እንደሰካራም ቢያንገዳግድህም መፍትሄው እሱው ነውናትችለዋለህ  ፡ አስበው እኔ በድንገት ከነዚ ሁሉ ነገሮች ጋር ነው የተፋጠጥኩት ፡ከኑሮ መክበድ ብቻጋርም አይደለም ፡ አንዳንዴ ሳስበው የእናቴን መከራ ሊያሳየኝ ይሆን እንዴ ፡ እላለው ፡ ለብቻዋን በዕድሜ ተቀራራቢ የሆንነውን ልጆቿን አሳድጋለች አንድም ሰው ነብስ እስካወኩበት ጊዜ ድረስ ሲያግዛት አላየውም ፡እና ሳስበው የሁሉም እናቶች ብርታት አስደናቂ ነው ክብር ይገባቸዋል ብያለው። ስለ እናቴ ግን ሌላው ቀርቶ በምን ገቢ እንደምታስተዳድረን እስከዛሬም ድረስ ግልፅ አልሆነልኝም ፡  በእርግጥ በግንብ የተከለለ የተንጣለለ ግቢ ያለው  ቤት አለን  የክራይቤት አደለም ሰርቢስ ቤቶች ቢኖሩም አንድም ቀን አከራይታ አታውቅም ፡ ነገርግን ከሆነ ቦታ ገቢ አላት ግን አትነግረንም ፡ በወር አንዴ ብቻ ትወጣና ቆይታ ትመጣለች የዛን ሰሞን በወሩ መጀመሪያ ማለቴ ነው ፡ጤፉም አስቤዛውም ፡ለኔም የኪስ ገንዘብ ትሰጠኛለች ፡ከየት መጣ ምናምን የመጠየቅ መብት የለኝም ፡  እንዲ ናት እንግዲ እናቴ በሚስጥሮች የተሞላች ፡ ማውራት የማትወድ ..........
ባዩሽን ቀስቅሼ ከማማጎን እንድትተኛ ነገሬ ፡ወጣው ፡ የጠዋቱ ብርድ ያንዘፈዝፋል የአምሌ ዝናብ ነው ፡ወይ አይዘንብ ንጭንጭ ያደርገዋል ፡የለበስኩት ባለሹራብ ጃኬት ከብርዱም የሚያስጥል አይመስልም ፡ በዛላይ ከሰውነቴ ተጣብቋል  ሰውነቴ ጨምሯል ፡የምወፍረው እንደው ዝምብሎ ስላልሆነ ተመስገን እላለው በተስተካከለ ቁመናላይ ፈርጠም ያለ አካል ነው ያለኝ ፡ ብዙዎች ይወዱልኛል ፡አዲስ የያዝኩት ጓደኛዬ ወፈር ያለ ነው ፡እና ብዙ ጊዜ ይሄን ሰውነት ይዤ ስንቷን ነበር ጠብ የማደርግበት ይለኛል እስቃለው ፡ እውነት ሴቶች በቁመናህ ማማር ብቻ ጠብ የማለት ጉዳይ አልዋጥልህ ይለኛል ፡  ምናልባት ለሳምንታት ሊሆን ይችላል ፡ከዛ በዋላ ሴት ልጅ ከአንድ ወንድ የምትፈልገው ብዙ ነገር አላት ፡ እሱን ለሴቶቹ ልተወውና ፡  .....
ከአጠና ተራ    ሰባተኛ አቶቢስተራ በሚለው ታክሲ ተሳፍሬ ገባው ፡ የተቀመጥኩት ሦስተኛ ተደርቤ ነበርና ምቾት አልሰጠኝም ፡ እስከምወርድ ተጨነኩ ፡ ይሄ አዲሳባውስጥ የእዝብ ቁጥር መጨመር በየሄድንበት እንግዲ ምርጫ ስለሌለን ያቻችለናል አልችልም ብትል ምን ታመጣለህ !
ሰባተኛ ወርጄ የእስታዲየምን ታክሲ ለመያዝ ተወዘወዝኩ ፡ በዛላይ ካፊያው ፡ ከምሆድበት ቦታጋር ተዳምሮ ይብስ አሸበረኝ ፡ ወደታች አንድ ታክሲ ገንጠል ብሎ ሲሄድ ሰውን ቀድሜ ሮጥ አልኩኝ ፡ ስደርስ 'ይቅርታ አይጭንም 'አለኝ ኤጭ ብዬ ስመለስ  ፡ አንድ ፖጃሮ መኪና ውስጥ የተቀመጠሰው እጅ ተውለበለበልኝ ፡ ጠጋ ስል ሴት ናት ፡ ዕድሜም ተቀራራቢ ነን 'ውይ ለዚች ደሞ ይሄን መኪና ማን ሰጥቷት ነው ፡መቼም በዚ እድሜዋ ሰርታ አትገዛውም ፡ወይ ከውጪ መጥታ ፡ወይ አባቷ አብታም ነው ወይም ሙሰኛ ነው ፡ወይም አብታም ባል አላት ፡ወይ ወይም...'አልኩ ግን ምን አገባኝ ፡! በጣም ስጠጋት ፡አሁን ገባኝ በራሴ መንገድ ትንፋሽን ለሰከንድ የሚያቋርጥ ውበት ፡ ለዚማ እንኳን መኪና ዓለምን ይሰጧታል አልኩ ፡
"ግባ ወንድም "ብላ የመኪናውን በር ስትከፍተው ፈዘዝኩ
"ምነው ወደ እስታዲየም አይደለህም እንዴ?"አለችኝ
"ነኝ እሱማ "
"እና ግባሃ ታዲያ እኔም እኮ ወደዛው ስለሆንኩ ላድርስህ ብዬ ነው ፡ "አለችኝ ተረጋግታ እና በትላልቅ ውብ አይኖቿ ውስጤ ድረስ ሰርስራ እያየችኝ ፡አስተያየቷ አስጨነቀኝ ፡የሌለ አይን አፋር አድርጎኝ ቁጭ አለ
"እሺ ካላስቸገርኩሽ "አልኳትና ገባው ዋው ድሎቱ ፡ ቅድም ካጠና ተራ ስመጣ መቀመጫዬ አሳዝኖኝ ነበር ኪኪኪኪ
"ለምን ታስቸግረኛለህ ፡በነገራችን ላይ አውቅሃለው ፡ግን እረጅም ጊዜ አላየውህም "አለችኝ
"እኔን ታውቂኛለሽ ከምር?የት?"ብዬ ጠየኳት
"የሚገርም ትውውቅ ነው ያለን እዛው ኤግዚብሽን አካባቢ ነው የማውቅህ ከጉርምስናህ ጀምሮ ሁሌም ግን ስትደባደብ ነበር የምታጋጥመኝ ፡ እውነት በጣም ነበር የምትገርመኝ ፡ አንድም ቀን እረፍት የለውም እንዴ ፡ብዬ ሁላ እናቴን ጠይቄያት አውቃለው ፡"
"ከምርሽ !?"አልኳት አፈር ብዬ
"አዎ የእኛ ቤት ከእናተ ቤት በርግጥ ወደውስጥ ገባ ይላል ነገርግን ከእናቴ ጋር ወደ ሱቅ ስንሄድ ብዙ ጊዜ ሰፈር ውስጥ አይክ ነበር ወይ ሰትደባደብ ወይ ስትጎማለል ኪኪኪኪኪ እውነትበጣም ነበር በመገረም የማይህ ፡አሁንእንደዛ አነህ ግን "አለችኝ እየሳቀች ሳቋ እንዴት እንደሚያምር ፡  ይገርማል ሰፈራችን እንደዚህችም አይነት ሴት ነበር ኧረ እኔ ማንንም ልብ ብዬ አይቼም አላውቅ ፡ እንዳለችው ትንሽ ነገር ያስከፋኝና ሰው ካልገደልኩ ነው በዛላይ የሱሴ ብዛት ፡ ይኽው አሁን በማማ ምክንያት ሁሉም ቢቀርም ፡  እኔ የሌለብኝ የሴት ሱስ ነው  ቢኖርብኝማ ይእችን ልጅ አያት ነበር ሆሆሆ እንዴት ነው የምታምረው ፡ ወንድነቴን አስታወሰችኝ እኮ ....
እስታዲየም ስንደርስ ወሬያችን አላለቀም ነበር ፡ፀብ ማቆሜን ስነግራት እየሳቀች ተመስገን አለች ሆሆ የዚን ያክል አሸባሪ ነበርኩ እንዴ አልኩ ለራሴ ፡
ስልኳን ሰጠች ለማመን ከበደኝ ፡እንዲ ታደርጋለች ብዬ አላሰብኩም እንኳን በራሷ ፍቃድ ተጠይቃም የምትሰጥ አትመስልም ፡ ተስገብግቤ ነው የተቀበልኳት ፡እሷ እስታዲየም ጥላኝ የምሄድበት ስላለ ነው እንጂ ሰፈር አደርስህ ነበር አለችኝ አመስግኛት ሄድኩ፡የልቤን ምት ጨምራብኝ ሌላ ስራ ጀመርኩ ልቤ ውስጥ
ሰፈር ስደርስ ላለመታወቅ ሽልሽል እያልኩ ነበር ፡ተሳክቶልኝ ፡ማንም ሳያየኝ ቤት ደርሼ የቤቱን መጥሪያ ተጫንኩት ,,,,,,,,,


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj