Get Mystery Box with random crypto!

የ እናቴ ልጅ ክፍል አስር ይገርማል እንደ ቀልድ ቀን ቀንን እየተካ አመታት | አትሮኖስ

የ እናቴ ልጅ
ክፍል አስር

ይገርማል እንደ ቀልድ ቀን ቀንን እየተካ አመታት ይቆጠራሉ !! ዕፃናት ያድጋሉ ወጣቶች ጎልማሳ ይሆናሉ ጎልማሶች ያረጃሉ  አዳዲስ ሕይወት ይመጣል የቆየውም ያልፋል ፡ ለሁሉም ወር ተራ ነው ፡
ዛሬ ለማማዬ ሁለተኛ አመቷን አከበርንላት ፡እኔና ባዩሽ ብቻ በትንሿ የክራይ ቤታችን !!ሁለት ቁጥር ሻማ ሳበራ ፡ ድንገት የባነንኩ ይመስል ያሳለፍኩት ምስቅልቅል ከፊቴ መጥቶ ተደቀነ ፡ የወንድሜ ጭካኔ የእናቴ  ጥላቻ አሁን እንደተደረገ ይታየኝ ጀመር ፡ እንደ አዲስ አንገበገበኝ ያምሽት፡  እናቴ እሩሩ ልብ ቢኖራት ኖሮ  ጨክና  አትተወኝም ነበር  ይቅር ትለኝ ነበር ፡ ለሊቱ ከመንጋቱ በፊት ዲቃላህን ይዘህልኝ ጥፋ በጭራሽ እንዳላይህ የሚለው የእናቴ የቁጣ ቃል ዳግም አይምሮዬላይ ተንጫጫብኝ ፡የአቤል ያፈጠጠ ውሸት እና ማስመሰል ሁሉም ተመላለሰብኝ ፡በጣም ተከዝኩ ፡  .....
ባዩሽ ነበረች ያባነነችኝ "አንተ ምን ሆነሃል ሻማውን ጎትታ ልትጥለው ነበር እኮ "አለችኝ
"ውይ የሆነ አሳብ ውስጥ ገብቼ እኮ "አልኳት
"ምንድነው እሱ ናቲዬ ስራቦታ ችግር አለ እንዴ?"አለችኝ እያሳሰባት ፡
"አይ ስለ ስራ አይደለም እንደው እናቴ ትዝ ብላኝ ...."ብዬ ቀእንጥልጥል ተውኩት
"እንደው ናቲዬ ካመጣህው አይቀር እንደው እኔም ብሆን እያስብኩልህ ነው እስከመቼ ነው ከእናትህ ተደብቀህ ልጅ የምታሳድገው በጣም ያሳስባል?!"አለች
"አይ አይ ተደብቄ አይደለም እሷ ናት በለሊት ከነ ዕፃን ልጅ ያባረረችኝ  ምንም እርህራሄ አነበራትም ይህን ያደረገችው ለክብሯ በማሰብ ነበር  የኔ ነገር ምንም አላስጨነቃትም ፡ በዛላይ የኔ ..."ብዬ ዝም አልኩ
"ያንተ ምን?"
"ተይው በቃ እንደው ስሜታዊ ሆኜ ነው"አልኳትና ዝም ብዬ አየዋት ፡እስከዛሬ ትክክለኛውን ሚስጥሬን አልነገርኳትም ፡
"ንገረኝ ነገርን በውስጥ መያዝ ጥሩ አይደለም ፡"አለችኝ
"አይ እንደው ነገሩ ትንሽ የሚከብድ ነው ፡በእርግጥ እንደሞኝ ካላየሺኝ የደበኩሽን ሚስጥር ዛሬ እነግርሻለው ፡"
"ናቲዬ አንተን እንደሞኝ ላይ በጭራሽ አንተ እኮ ሰው ያደረከኝ ሰው ነህ ፡ "አለችኝ ዕንባ ባዘሉ አይኖቿ እያየችኝ
"እነግርሻለው ግን ያለማቋረጥ ስሚኝ እና ደሞ የምነግርሽ ነገር ለማመን ቢከብድም እውነት ነው "አልኳት ፡አንገቷን ነቅንቃ በጉጉት ጆሮዋን አቅንታ ታዳምጠኝ ጀመር ፡ባዩሽ የኔንና የወንድሜን አስተዳደግ ከመጀመሪያ ጀምሮ ስነግራት ፡ፈገግ እያለች አንዴም ኮስተር እያለች ተከታተለችኝ ፡ በመጨረሻም የአቤልን ለውጥና ፡ በድንንገት የልጅ አባት መሆንና ፡ በኔላይ ያለምንም አፍረት እንዳላከከብኝ ፡እናቴም ይህን አምና መቀበሏንና ፡ሁለቱም ተጋግዘው ከቤት እንዳስወጡኝ ስነግራት ፊቷ በአንዴ ተለዋወጠ ፡ሰውነቷ የተንቀጠቀጠ መሰለ ፡በመገረም እንደ አዲስ ሰው ታየኝ ጀመር ፡ ዝምብዬ የምትለኝን ለመስማት ስጠባበቅ ድንገት ከተቀመጠችበት ተነስታ "እውነትም ሞኝ ነህ የሞኝ ሞኝ ፡እንዴት ባልወለድከው ልጅ የኔናት ብለህ ትሰቃያለህ ፡እንዴት እንዲ እንዲያደርግህ ትፈቅድለታለህ እንዴት ፡ እሺ የሆነስ ሆነና ተመልሰህ ሄደህ እናትህን ማሳመን አልነበረብህም ፡ እንደዛ በዚች ዕፃን ልጅ የተነሳ እንደሴት አዝለህ ወተት እያፈላህ  የተሰቃየኽው ባላረከው ነገር ነው ፡ያሳዝናል ፡ "ብላ ወቀሳም አዘኔታም ያለበት ጩኽት ጮኽችብኝ
ግራገባኝ ነገሩ ከኔ በቀር ለማንም አይገባውም ማለት ነው እኔ እኮ ስለ እናቴ ነው ይህን የምከፍለው  እሷ ከኔ ይልቅ ለአቤል ቦታ አላት ያ ስሜት እንደተጠበቀ ካልኖረ የምታብድ ነው የሚመስለኝ ,,,,,, አይኔን ጨፍኜ ነገሮችን እንደ አዲስ ለማየት ሞከርኩ.......

ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj