Get Mystery Box with random crypto!

የ እናቴ ልጅ ክፍል አስራ አንድ አንዳንድ ሰዎች ልብ ብለን ካየን አብዛኛውን ጊ | አትሮኖስ

የ እናቴ ልጅ
ክፍል አስራ አንድ

አንዳንድ ሰዎች ልብ ብለን ካየን አብዛኛውን ጊዜ ከራሳቸው ይልቅ በሌላሰው ችግር ነው የሚቸገሩት ፡ የቤተሰባቸው አካል የሆነ ሰው ወይም ጓደኛቸው ፡ በሆነ ሰው የተበላሸውን ነገር ለማስተካከል ሲጥሩ ፡ ጊዜ አቸውን አቅማቸውን ያለ አግባብ ያባክናሉ ፡  እንደ እውነቱ ሁሉም የየራሱን የቤት ስራ ቢሰራ ኖሮ  ስንት አስቸጋሪ ነገሮች በተቀየሩ ነበር !! ነገርግን አንዱ በሕይወት ውስጥ ደክሞ ሲሸሽ ሌላው  ከራሱ ጋር አብሮ የሱንም ድክመት ተሸክሞ ለመለወጥ ይፍጨረጨራል ፡  ከእይወት እንደተረዳውት  ማንም የማንንም ሸክም መሸከም የለበትም ፡የሚለውን ነው ። ከቻልክ ሸክሙ እንዲቀልለት መንገዱን ማሳየት ነው!
ባዩሽ ሰሞኑን እንደ አዲስ ሰው ነው ስገባም ስወጣ የምታየኝ ከለት እለት አስተያየቷ ከበደኝ ፡ እይታዋ ውስጥ አዘኔታም ቢኖርም እንደሞኝ አድርጋም የቆጠረችኝ መሰለኝ ፡  ይህ ሁኔታዋ ደሞ እራሴን ደጋግሜ እንድፈትሽ አደረገኝ ፡  ለምንድነው እውነታውን የማላወጣው ፡ ለምን ለእናቴ ደብዳቤ አልፅፍላትም ፡እኔን ማየት ባትፈልግ እንኳ ፅሑፉን ማንበቧ አይቀርም ብዬ አሰብኩ ፡ይሄን አሳብ ደጋግሜ አወጣው አወረድኩት ፡ በመጨረሻ ወሰንኩና ለባዩሽ አማከርኳት ፡
"በዩ አንድ አሳብ አለኝ "አልኳት እራት በልተን ፡ማማንም አስተኝታት ፡ቡና ለማፍላት ስትቀመጥ ጠብቄ።አይን አይኔን እያየች ፡በጭንቅላቷ እንድቀጥል ምልክት ሰጠችኝ
"ምን መሰለሽ ለእናቴ ደብዳቤ ለመፃፍ አስቤ አለው ፡ "ስለምን ጉዳይ ?"አለች ባላወቀ
"ስለ አቤል ፡እንደዋሻት እና ዕፃኗ የኔ አለመሆኗን  ፡ብቻ ብዙ ነገር ወቀሳም ጭምር "አልኳት
"እንዴ ናቲዬ አሁን እሱ በድንገት የሚነገር ነገር አይደለም በመጀመሪያ ዝም ብለህ ወደቤት ተመልሰህ የእናትህን ደንነት ማረጋገጥ አለብህ እሱ ቀስ በቀስ የሚደርስ ነው "አለችኝ
"እና ዝም ብዬ ሄጄ የማትፈልገኝን እናቴን ማየት አለብኝ?አንቺኮ ስላልገባሽነው  የጥላቻዋን ጥግ ብታዪው ኖሮ አጠገቧ መድረስ ያስፈራሻል ፡ እኔ ምን ወዲወዲያ አስባለኝ እስካሁን ንዴቷ ይበርዳል ስለዚህ ዕፃኗ የኔ አለመሆኗን አስረግጬ ነው የምፅፍላት ፡ "
"እንደሱማ አይሆንም እውነት ብትቀበል እንኳ ከዚ በዋላ ማማን አሳልፎ የመስጠት አንጀት አለህ ፡ "አለችኝ ፡ የሰላም እንቅልፋን ወደምትለጥጠው ማማ እያሳየችኝ ፡ፈገግ አልኩ
"በዩ ማማ እኮ መቼም አትለየኝም ምክንያቱም በተዘዋዋሪ ያው ደሜ ናት የትም አላጣትም ቤተሰቤ ናት ፡"አልኳት ፡ ያ ተንከሲስ ልጅ ቢያምን እንኳ ማማን አሳልፌ አልሰጠውም የምፈልገው የእናቴን ይሁንታ ብቻ ነው ፡
"እሺ እናትህ ማወቋን እኔም የምፈልገው ጉዳይ ነው ነገርግን ከደብዳቤው በፊት ሄደህ እያት ምን አልባት ነገሮች ተቀይረው ይሆናል ሁለት አመት ቀላል አይደለም የሰውልጅ አሳቡን ለመቀያየር አንድ ቀን ይበቃዋል ባሁን ጊዜ ፡ ስለዚ ሄደህ በአካል ተገናኛቸው ወንድምህም ቢሆን ተፀፅቶ ይሆናል ፡የዕፃኗ እናትም ብትሆን አርፋ ላትቀመጥ ትችላለች ፡ "አለችኝ አንገቴን በመነቅነቅ ተስማማውላት ፡  ነገ ሁለት አመት ሙሉ ጨክኜ ከጠፋውት ሰፈር የእናቴ ቤት ልሄድ ቆረጥኩ ፡ ስወስን አካባቢው ናፈቀኝ ለገሐር ኤግዚቢሽን ማህከል እስታዲየም ፡ እሲጢፋኖስ ቤተክርስቲያን መስቀል አደባባይ ፡እሄድባቸው የነበሩት የሰፈሬ አቅርያቢያ በሙሉ ናፈቁኝ ፡ይገርማል ሁለት አመት እንዲ አጭር ናት ለካ እራሴን በማማ እና በስራ ወጥሬ አልታወቀኝም ፡ በሁለት አመት ውስጥ ቁም ነገር የሰራውት ማለቴ ለኑሮዬ የተመኘውትን መንጃ ፍቃድ በቅርቡ ማውጣቴ ነበር ፡ የገንዘብ ችግር አሁን የለብኝም እድሜ ለጉልበቴ የአቅሜን አግኝቻለው ፡  የወደፊትም አሳቤ ከዛም በላይ ነው ብዙ እቅዶች አሉኝ ማማ ጠንካራ ሰራተኛ አድርጋኛለች ፡ የነገ መሄዴን እና እናቴን ማግኘቴን ሳስበው ጨነቀኝ ፈርሃት ፍርሃትም አለኝ ፡ ,,,


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj