Get Mystery Box with random crypto!

የ እናቴ ልጅ ክፍል ዘጠኝ አንዳንዴ ወዴት እንደምትሄድ ሳታውቅ፡ ግን እግር | አትሮኖስ

የ እናቴ ልጅ
ክፍል ዘጠኝ

አንዳንዴ ወዴት እንደምትሄድ ሳታውቅ፡ ግን እግርህ መራመዱ አይገርምህም ? በቃ አንተ መድረሻህን አላሳወከውም ፡እሱ ግን ይንቀሳቀሳል ፡ እግራችን አመፀኛ ሆኖ  'የት እንደምንሄድ ካልነገርከኝ ካልወሰንክ አልንቀሳቀስም 'ቢል ኖሮ ምን ይውጠን ነበር ? በእርግጠኝነት ብዙ ሆቻችን አንድ ቦታ ተዘፍዝፈን እንቀር ነበር ጥሩ እነቱ እግር አልሄድ አይል ፡ የት እንደምሄድ ሳላውቅ ዕፃን ልጅና ሻንጣ ተሸክሜ የሌሊቱን ብርድ ቻል አድርጌ  ጉዞዬን ቀጠልኩ ፡  ሰፈራችን ውስጥ አንድም ነብስ አለመንቃቱ ጠቀመኝ  ማንም አላየኝም  ሌላው ቀርቶ ውሾቹ እንኳ እንቅልፍ ጥሏቸው ጥግጥጉን ተረፍርፈዋል ፡ ተመስገን አይለኛና ተፈሪ በሆንኩበት ሰፈር ልጅ ታቅፌ በለሊት ብታይ ፡እናቶቹ የቡና ማጣጫ ፣ አባቶቹ የመጠጥቤት ውሎ ማድመቂያ ፣ጎረምሶቹ የጫት ቤት ሙድ መያዣ ነበረ የሚያደርጉኝ ፡ 
   ከሰፈራችን ለቅቄ ስወጣ እፎይ አልኩ ፡ የመስቀል አደባባይን አስባልት ይዤ ወደፊት ተራመድኩ  ፡ያው ሰፈራችን ከኢግዝብሽን ማህከል ጀርባ እንደመሆኑ መጠን ፡ በለሊት ወደ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የሚሄድ ሰው አይታጣም እና ጠንቀቅ ማለቱን አልዘነጋሁትም ፡ አልፎ አልፎ ነጠላ የለበሱ እናቶች ባጠገቤ እልፍ ሲሉ እራሴን ሰብሰብ አደርጋለው ፡  ይህ ሁኔታዬ ለራሴ አሳዘነኝ ፡እራስህን በሌላ ሰው መነፅር አይተህ ለራስህ አዝነህ አታውቅም ? አዎ በቃ እንደዛ ....በእስጢፋኖስ በኩል ሳልፍ ቆም ብዬ ተሳለምኩና ፀሎት አደረኩ ' ቅዱስ እስጢፋኖስ ከአምላኬ ጋር አስታርቀኝ ፈጣሪዬ ፈተናዬን ይቀንስልኝ ዘንድ እርዳኝ 'አልኩ  አንድም ቀን ፀልዬ ስለማላውቅ ምን እንደምል ፣እንዴት እንደሚለመንም አላውቅ ፡ግን በራሴ መንገድ ለፈጣሪዬ እንዲደርስልኝ ዕንባ ዘለላዎችን በለሊት አንጠባጠብኩ ፡  የታቀፍኳትን ዕፃን አየዋት የሰላም እንቅልፍ ላይ ነች ፡ በዚ በዚ አድናቂዋ ነኝ አንዴም አላለቀሰች ፡ እኔን ማስጨነቅ አለመፈለጓ ጥሩ ነው ፡ ምን አልባት ፈጣሪዬ በዚ እየረዳኝ ይሆናል ተመስገን ማለትን በዚ አጋጣሚ ተማርኩ ...
ለካ ላይችል አይሰጥም የሚሉት እናቶቻችን ወደው አይደለም ፡የአለምን አዙሪት ትችለዋለህ ስቃዩ ከብዶ አልቻልኩም ብትልም ችለህ ቆመ ትራመዳለ ፣ርሃብ አልችልም ብትል ብቸኝነት አልችልም፣ ከሰው መለየት አልችልም  ሰው ማስቸገር አልችልበትም ብትል ፡ ምንም አታመጣም እስትንፋስህ እስካለች ፡አለመቻልን እራሱ ትችለዋለ ......
ከማማ ጋር ጎዳና ከወጣን ሰነባበትን ፡ ቤት ንብረት ያለው ሰው ብቻ አይደለም ለካ የሚያስጠጋህ ፡እነሱንማ አየናቸው ከንፈር ከመምጠጥ በዘለለ ምንም አይፈይዱልህም ፡  ካላቸው ሚሊዮን ብሮች መሃል አስር ብር ሰጥተው ላንተ ባደረጉት ነገር አካብደው ፅድቅ የሚጠብቁ ስንቶቹ መሰሉህ ፡አንድ ስንዝር ሕይወትህን የማይቀይር ሳንቲሞች ሰጥተው ፡ለምን አትሰራም ብለው የምክር አገልግሎት የሚሰጡህ በቱ የሚሉ ቁጠራቸው ፡  ከእነሱ በተሻለ መጠጊያ የሰጠችኝ እትዬ ባዩሽ ምስጋና ይድረሳት ፡ኮልፌ ላስቲክ ወጥራ ነው የምትኖረው ፡ ብዙ ነገር ያየች ናት ፡የኑሮ አጋጣሚ ባዶ እጇን አስቀርቶ ጎዳና ያወጣት ፡ ፊቷ እንደ ከሰል ቢጠቁርም ልቧ የነፃ ፡ አዛኝ ፡ የነበረኝን ገንዘብ በሁለት ወር ውስጥ ለክራይ እና ለሚበላ ለማማ ወተት ስገዛ ጨርሼ መግቢያው ጠፍቶኝ ስንከራተት ውዬ ደክሜ ድልድይ ስር ቁጭ ብዬ  ሳዛጋ ነበር ያገኘችኝ ዕድሜዋ ልክ እንደ እናቴ ነው አርባዎቹ ውስጥ ፡ አጠገቤ መጥታ ስትቆም እብድ መስላኝ ነበር ፡በዋላ ስረዳት ለካንስ አሳዝኛት ኖሯል ፡  ስላለውበት ሁኔታ ጠየቀችኝ ነገርኳት ዕፃኗን ግን የራሴናት ነው ያልኳት ፡ከዚ በዋላማ የማንም ልትሆን አትችልም ፡ ከዛ ነው እንግዲ ወደቤቴ ና ብላኝ የወሰደችኝ ፡መጀመሪያ የእውነት ቤት መስሎኝ ነበር በዋላ ግን የላስቲኳን ቤት ሳይ ቀፈፈኝ እንዴት በዚ መጠን ወርጄ እገኛለው ብዬ ተናነቀኝ ፡ ግን ምን አማራጭ አለኝ ምንም የስቃዬ መጀመሪያ ሊጀምር ነው አልኩ ፡ ባዩሽ ግን ሁሉም ደና ይሆንልሃል አለችኝ ለጊዜው እዚ እረፍ  የጨካኞቹን ቤት አከራዮች ሆድ የምትሞላበት አቅም ላይ አይደለም ያለኽው ከጠበበንም ሰፋ እናደርገዋለን ፡ አለችኝ  አዘን ብሶቴን ዋጥ አድርጌ ይሁን አልኩ ፡  ለጊዜው ነው እንጂ ማማንማ እዚ እንድታድግ አላደርግም ፡ ብዬ ወሰንኩ
   ከባዩሽ ጋር በጣም እየተለማመድን ስንመጣ የዋህ ልቧ ይገርመኝ ጀመረ  ያገኘችውን ሁሉ እኛን ለማስደሰት ብላ ይዛ ትመጣለች ደግ ነች ፡ ይሄ ደግነቷ እንዳምናት አደረገኝና ፡በቃ ማማን እሷ ጋር እያስቀመጥኩ ለምን አልሰራም ብዬ ወሰንኩ  እና ስራ መስራት ከባዩሽጋር ተስማምቼ መንቀሳቀስ ጀመርኩ  ኮልፌ አካባቢ ሰፊዎች አሉ እና ለነሱ ጣቃ ከመኪና ላይ ማውረድ መጫን በቃ ያገኘውትን ነገር ሰራው ፡ ጎዳና ላይ ወጥቶ ላስቲክ ቤት ከመኖር የከፋ ነገር አለ እንዴ ሂሉኝታ ደና ሰንብት አልኩ ፡ጉልበቴን ተጠቀምኩት ፡ ገንዘብ አገኝ ጀመር ፡ እና ገንዘብ ሳገኝ የመጀመሪያ እቅዴ ማማንና ባዩሽን ከላስኪቱ ቤት ማላቀቅ ነበር እናም ተሳክቶልኝ አነስተኛ ቤት ተከራይተን ገባን ፡ ባዩሽ ትንሽ አስቸግራኝ ነበር እኔ ግን አንቺ ማለት የእናቴ ምትክ ነሽ አንቺ በሕይወቴ ውስጥ ቦታ አለሽ ስለዚ መቼም ትቼሽ አልሄድም አልኳት በመጨረሻ ተስማማች ፡ ኑሮ ተጀመረ ፡ አንድቀን ባዩሽ  እንዲ አቸኝ
"እኔ የምልህ ናቲ እንደው የዝህች ልጅ እናት በቃ ዝም ነው የምትባለው ?ምን ልባት እኮ ወደ እናትህ ቤት ተመልሳ መጥታ ልጄን ብላ ጠይቃ ይሆናል ፡መቼም ሴት ልጅ እንዴት እንዳማጠች ስታውቅ ሁሉን ትረሳለች ማለት ከባድ ነው "አለችኝ
"ባያ ዝም በይኝ እሷ በጭራሽ አትመጣም አረብ አገር ሳትሄድ አትቀርም "አልኳት ውሸት ቀላቅዬ ፡እንዴት ብዬ ወንድሜ አላኮብኝ ነው ብዬ አወራለው ለሰሚውም ግራ ነው
"አይ እንደው እኮ ብትመጣ አንዴ እንኳ ጥሩ ነበር ፡የልደት ቀኗን እንኳ አታውቀውም "ስትለኝ በጣም ተገረምኩ ፡እውነት ለመናገር ትዝ ብሎኝም አያውቅ ነበረ ከችግር ለመውጣት ከመፍጨርጨር በቀር
"ባክሽ አንዱን ቀን ማክበር ነው የሦስት ወር ነበረች እሱን አስልቼ ማክበር ነውኪኪኪኪ እንደውም ለምን በሃያ ሰባት አናከብርላትም በቃ የመዳኒዓለምን ቀን ያዢውና ሁለተኛ ዐመቷን እናከብርላታለን"አልኳት ባዩሽ ወይ አንተ ልጅ ብላ ሳቀች "ሌላው ክትባት ወስዳ አታውቅም አይደል በቅርቡ አኪም ሊያያት ይገባል"ብላ አከለች ፡ወይጉድ ማማዬ በዛ መሰሪ ወንድሜ የተነሳ ስንት ነገር ቀርቶባታል ,,,,,,,,,,


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj