Get Mystery Box with random crypto!

የእናቴ ልጅ ክፍል ስምንት ለካንስ የሰው ልጅ አንዴ ውሸትን መለማመድ ከጀመረ  እ | አትሮኖስ

የእናቴ ልጅ
ክፍል ስምንት

ለካንስ የሰው ልጅ አንዴ ውሸትን መለማመድ ከጀመረ  እንደ እውነት ነውና የሚቆጥረው ፡ ሌላው ቀርቶ ሰው ሲዋሽ ፊቱ ላይ የሚገለፅ አንዳች እንቅስቃሴ አለ ይባላል  ኖኖ ግን እሱ የሚሰራው ድንገት ተቸግሮ የሚዋሽ ሰው ሲሆን ብቻ ነው ፡ እንጂ ሆነ ብሎ ውሸትን መጠጊያው አድርጎ የሚኖረው ላይ አይደለም  በጣም የሚገርመኝ ደሞ ሰውየው እራሱ ውሸቱን እስከማመን የሚደርስበት ነገር ነው ፡  እውነት ለመናገር የወንድሜን ያላንዳች የገፅታ መለዋወጥ ፡ሁሉንም ነገር በኔላይ ማላከኩ ትልቅ ፍራቻን ፈጥሮብኛል ፡ፍራቻዬ ለራሴ ብቻም አይደለም ፡ ለሱም  ለእናቴም  ጭምር ነው ፡ምክንያቱም ይህን ልምድ ድንገት ያገኘው አይመስለኝመሰ እየተለማመደው ነው የመጣው ፡በዚ አይነት እናቴ በኔላይ ጥላቻ እንዲያድርባት ሰርቷል ማለት ነው ፡ እናቴ በበፊቱ እረባሽነቴ ብቻ ሳይሆን እሱ ፈጥሮ በሚነግራት ነገር ነው ልትጠላኝ የቻለችው ብዬ ደመደምኩ ፡ ይሄ ባህሪ ደሞ ፡ለቤተሰባችን ብቻ ሳይሆን አልፎ ወጥቶ የቀረቡትን በሙሉ ሊያሳዝን እንደሚችል ተሰማኝ ፡ከባድ ነገር ነው ፡
ዕፃኗን ታቅፌ መኝታ ክፍሌ ገብቼ ዘጋው ፡ እናቴ እርግማኗን ስታዥጎደጉድብኝ ይሰማኛል ፡በቃ እናቴን መከራከሬ እንደማያዋጣኝ ተገነዘብኩ ፡ምንም ያክል እውነት ብናገር የአቤልን ውሸት መደምሰስ እና የእናቴን ቀልብ መመለስ እንደማልችል ገብቶኛል ፡ ከኔ ይልቅ የታማኙ ለስላሳ ልጇ ቃላት ልቧን ይሞላዋል ፡አይለኛና ጉልበተኛ አልሸነፍ ባይ ብሆንም ፡ይሄ ነገር እናቴ ላይ እና ወንድሜላይ ሲሆን አይሰራልኝም ፡ በተለይ እናቴ የቱንም ያክል ብትጠላኝ ፡ እሷላይ መጨከን የሚችል አንጀት የለኝም ፡ እንኳንስ አንድ ነገር ሆና አይቼ ቀርቶ ፡መንገድ ላይ እንኳ ከሷ ዕድሜ የምትቀርብ ሴቴ አንዳች ችግር ገጥሟት ካየው ውስጤ ስፍስፍ ነው የሚልብኝ ፡  ወንድሜ በዚመጠን ቢጎዳኝም እሱላይ እጄን ማንሳት ይከብደኛል ፡እንደው በጩኽት እንኳ ሳናግረው እናቴ ስለምትከፋ ለሷ ስል ነገሮችን የምተው ነኝ ፡
ዕፄኗ አልጋዬ ላይ ፍልስስ ብላ አንቀላፍታለች ፡ጠጋ ብዬ ሳያት በአንድ ጎን ባለው ጉንጯ ላይ ፈገግ ያለች ትመስላለች ፡ ይሄን ፈገግታ አውቀዋለው አቤል ነው ወደጎን ፈገግ የሚለው  ልጅ እያለን በጣም ነበር የምወድለት ፡ ቅላቷ ልክ እንደ እናታችን ነው እኔም ሆንኩ አቤል ጠይም ነን ፡ ሁለታችንም መልከመልካም ፡ብንሆንም ፡ አቋምን በተመለከተ እንግዴ እኔ ረዘም ያልኩኗ የተስተካከለ አቋም ነው ያለኝ ፡ አቤል ወፈርፈር በማለቱ ቁመቱ ባያሳጣውም ከጊዜ በዋላ የመጣበት ውፍረት ትንሽ የቀነሰበት ነገር አለ ፡ እናታችን ቆጆ ናት ዕድሜዋ ወደ አርባ አምስት ነው ነገር ግን አሁንም ከፈለገች ፡ የምትወደውን ወደ ሕይወቷ ማምጣት የሚችል አቋም ላይ ናት ፡ 
የዕፃኗ መልክ ግን ከፈገግታዋ በቀር እኛ ቤት አይደለም ፡ የማላውቃትን እናቷን ቁንጅና ሳትወርስ አትቀርም ፡በጣም ታሳሳለች ፡ ገና ናት ከሶስት እና ከአራት ወር አታልፍም ፡ ምስኪን ከማይረቡ ሁለት መናጢዎች ተወልዳ ፡በእናቷ እቅፍ ውስጥ መሆን ሲገባት ፡ ምንም በማያውቀው እብዱ ነን ታኒየም ላይ ተጥላለች ፡  ለሊቱን ሙሉ ሳስብ ነበር እንዴት ነው የማደርጋት ፡ እኔም አንዱ ጥግ ወስጄ ጥያት ሕይወቴን ልቀጥል ፡ ወይስ እዚሁ ቤት ጥያት ልጥፋ፡ ወይስ አዝያት እያባበልኩ ፡ልመና ልውጣ ፡ ግራ ገባኝ ፡ እንቅልፍ እሚባል ባይኔ ሳይዞር ነው ያደርኩት ፡  ከለሊቱ አስራ አንድ ሰአት አካባቢ ፡የክፍሌ በር ተንኳኳ ደንግጬ ተነስቼ ከፈትኩ ፡ አቤል ነበር ኮስተር እንዳለ
"እስካሁን እዚ ነህ ከመነሳቷ በፊት ዲቃላህን ይዘህ አትሄድም "አለ ፡ማመን አቃተኝ
"የኔ ልጅ እንደሆነች ታስባለህ ?"አልኩት በጩኽት እኔ እንደሱ ቀስብሎ ማውራት አልችልም ለዛም ነው ሰው የማይረዳኝ
"ስለሱ አይመለከተኝም እናቴ ያለችህን ሰምተሃል እሷ ከመነሳቷ በፊት ከዚ ብትሄድ ይሻላል"አለኝ ግድ ሳይሰጠው
"ለምን ዲሄንሄ አናስመረምርም "
"ገንዘብ ካለህ አስመርምራ "አለኝ አይኑን እንደማርገብገብ ብሎ ስለዚ ጉዳይ ያሰበበት አይመስልም
"እሱ ወደፊት የማይቀር ነው እኔ ምንም እንዳላረኩ አውቃለው እናቴ እንድታምነኝ ስል ግን ተመልሼ መጥቼ ማስመርመሬ አይቀርም እንዳትረሳ ፡እኔ እንኳን ላስወልድ ቀርቶ የሴት ልጅ ከንፈር በቅጡም ስሜ አላውቅ  "አልኩት ፡በጣም ሳቀ መልሶ አፉን እጁ ላይ በመጫን ወደክፍሉ ገባ ።  ጭንቅላቴን ይዤ አሳብ እንዲመጣልኝ ወተወትኩ ፡ድፍን አለብኝ ፡ ወደ ዕፃኗ ተጠግቼ ቆምኩ ከእንቅልፏ ነቅታ አይኖቿ ይንከራተታሉ ፡ እልህ ያወኝ ፡ማንንም አልለማመጥም የሆንነውን እንሆናለን በቃ ፡ መንጃ ፍቃድ አወጣለው ብዬ ያስቀመጥኩት ጥቂተሰ ብር ነበረኝ እሱንአውጥቼ ያዝኩ ወፈር ያሉ ልቅሶቼን በሻንጣ ከተትኩ  እናቷ የላከችውን የዕፃኗን በቁጥር ያልበዛ ልብስ ያዝኩና  በፎጣ ጥቅልል አድርጌያት ተነስቼ ፡ወደበሩ አመራው እናቴ እንዳትሰማ በጥንቃቄ ነበር የምጓዘው ከግቢው ስወጣ አቤል ተከትሎኝ ኖሮ በፍጥነት ለዘላለሙ ይመስል በሩን ዘጋብኝ ጨለማው ገና አልገፈፈም ፡አምላኬን አንድ ነገር ለመንኩ እባክህ እናቴን ከዚ መሰሪ ልጅ ጠብቃት ፡ ,,,,

ደራሲ unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj