Get Mystery Box with random crypto!

የ እናቴ ልጅ ክፍል ስድስት ቤት ከገባው በጣም ቆየው አቤል ግን አልመጣም | አትሮኖስ

የ እናቴ ልጅ
ክፍል ስድስት

ቤት ከገባው በጣም ቆየው አቤል ግን አልመጣም እናቴ በተደጋጋሚ ወጣ እያለች ትመለሳለች እንደጨነቃት ያስታውቃል ልጇ እንዲ ሲያመሽ የመጀመሪያው ነው ፡ እኔ ብሆን ባድርም ግድ የላት የኔ ነገር ድሮ ነው የበቃት እኔም ብሆን አዘኔታዋን አልፈልገውም ፡ምክንያቱም ለዚሁሉ መገፋት የኔም ድርሻ አለበት ፡ ፍቅሯን ፈልጌ አንዳንዴ ብወቅሳትም ፡ ስህተቱ የኔም መሆኑን ካመንኩ ቆይቻለው እና ዛሬ ላይ ዝቅ ብዬ እየሰራው እራሴን ለማስተካከል መወሰኔ ከዛ አንፃር ነው  ,,,,,,,,,
እናቴ በጣም ሲብስባት ወደ እኔ ዞረች
"ስማ ከለሊቱ ስድስት ሰአት ሆኗል ወንድምህ አልገባም !አንተ ግን እዚ ተቀምጠሃል  ትንሽ እንኳ አይጨንቅህም?!" ብላ አፈጠጠችብኝ
"ምን ማድረግ እችላለው ከመጠበቅ ውጪ ፡እኔና እሱ እንደው ከተራራቅን ቆይተናል ፡ምን እንደሚያደርግ ምን እንደሚያስብ ከነማን ጋር ጓደኛ እንደሆነ አላውቅም ፡ ስለዚ  አዲስ ያመጣው ባህሪም ካለ እንግዲ ከኔ ይበልጥ የሚቀርበው አንቺን ነው "ብያት ፊቴን ወደቲቪው መለስኩ
"ምን ማለት ነው ?!"ብላ ቱግ አለች
"እንዴ ካንቺ ጋር ቀን ላይ የተነጋገራችሁት ነገር ካለ አስታውሺ ፡ ወይም ጓደኛ ካለው ከነሱ ጋር የሚያከብረው ነገር ካለው ፡ አይታወቅም  ትልቅ ልጅ ነው አንዳንዴ የሚያምረው ነገር ሊኖርም ይችላል"ብዬ ዝም ።እናቴ ልትመታኝ የፈለገች መሰለች ተጠግታኝ በቁጣ ስታየኝ ቆይታ
"እሱ እንዳንተ አይደለም ከአጠገቤ ተለይቶ አያውቅም ደጁን አያውቀውም ከመሸ ልጄን አውቀዋለው ይሄኔ አንድ ቦታ ተጨንቆ ነው የሚሆነው ወይኔ ልጄን ተነስ አሁን አፍህን መክፈትህን ትተህ ፍለጋ እንውጣ ፡ "ብላ ጎተተችኝ ፡ወይ እናቴ ምንአለ ከዚሁሉ ፍቅር ትንሽ ቀንሳ በሰጠችኝ ብዬ ተመኘው ፡
  ወደ በሩ ስትጣደፍ ስስ ነገር መልበሷን ልብ አልኩ ለማንኛውም ብዬ ወደክፍሌ ገብቼ ወፈር ያለውን ጃኬቴን ያዝኩላት እና ቀድማኝ የጊቢውን በር ከፍታ እየወጣች "ፍጠን" አለችኝ የቤቱን በር እየዘጋው ፡ መጣው ከማለቴ እናቴ ስትጮኽ ሰማዋት ፡በፈጣሪ ሰውነቴ ለሁለት የተተረከከ ነበር የመሰለኝ ፡ እናንተ ድንጋጤ ለካ ያስሮጣል ከመቼው ፡እናቴ አጠገብ እንደደረስኩ እኔነኝ የማውቀው  ፡እናቴ ደግማ ግን አልጮኽችም ፡አካባቢውን በጥንቃቄ እየቃኘች ከቆየች በዋላ በትልቅዬ ዘንቢል የተቀመጠ ነገር አነሳችና ወደግቢ ገብታ በሩን ዘጋች እኔ እንኳ ከጊቢ ውጪ መሆኔን የዘነጋች ነው የምትመስለው ፡
"እናቴ ኧረ በሩን ክፈቺልኝ"አልኳት ፡
"ናግባ ይሄ ምን ጉድ ነው!"ብላ በሩን ከፍታ አስገባችኝ ወደ ዘንቢሉ እየተጠጋው
"ምንድነው"አልኳት
"ዕፃን ልጅ ነው አይታይኽም "አለችኝ
"አአ አዎ አአ የውት"አልኩኝ በድንጋጤ ቃላቴን እየጎተትኩ ፡ ጉድ ፈላ አቤልን ዕፃን ልጅ ከታቀፈች ሴት ጋር አይቼው ነበር  ይህን ለእናተሰ ብነግራት አታምነኝም ፡በቃ በታማኙ ልጇ የሚመጣባት ሰው አትፈልግም ፡ እናቴ ለአቤል ያላት ፍቅር ጥልቅ ነው ፡እንዲነው እንዲያነው  ብሎ ለእናቴ መንገር ከበደኝ..
"ና ወደቤት ይዘነው እንግባ ማነው አምጥቶ የጣለብኝ ሆሆ ብለው ብለው የትም ሲልከሰከሱ ወልደው መጣያ ያድርጉኝ እኔ ከሰው አልቀርብ አልደርስባቸው ምን ፍለጋ ነው ሀብታም ናት ብለው ነው ፡እስኪ ከዚ ሁሉ ጊቢ የኔ በምን ታያቸው ፡ ልጄን ልፈልግ ወይስ የነሱን ዕፃን ላስተናግድ ምን አይነት ቀን ነው ዛሬ"እያለች እያጉረመረመች ከዘንቢል ውስጥ ድንገት ንቅት ብላ አይኗን የምታቁለጨልጭ ዕፃን አውጥታ ወደላይ በመያዝ "ውይ ጭካኔ ሴት ናት "ብላ ወደኔ ዞረች  ፡እኔ አይምሮዬ ሁሉ አቤል ጋር ነው በቃ አቤል እሱ ቀርቶ ልጁን ልኮልናል ፡ የት ተደብቆ ይሆን ይህን ድራማ የፈጠረው ጉድ ነው አልኩ ፡ እናቴ ዕፃኗን ሶፋው ላይ አጋድማ ዘንቢል ውስጥ ጡጦ ይኖር እንደው ብላ ስትፈላልግ በዛውም አንድ ደብዳቤ አገኘች ደብዳቤውን ይዛ ወደኔ ስትዞር ፡የጊቢ በር ተንኳኳ ሁለታችንም ለአፍታ በድንጋጤ ተያየን ፡ከዛ እኔ እሮጥ ብዬ በር ከፈትኩ አቤል ነበር ምንም ነገር አልሆነም ለመጀመሪያ ጊዜ አከበረኝ ይቅርታ የጓደኛዬ ልደት ነበር አለ ዝም አልኩ ።እናቴ አቤል መምጣቱን ስታይ እፎይ አለች  ፡እና ወደ ዕፃኗ እያሳየች "ጉድ ሆንን እኮ አቡ ተመልከት የጣሉብንን "ስትለው እንደ አዲስ ተገረመ እኔ የፊቱ ገፅታ አስገረመኝ ምንም አልመሰለውም ከጉዳዩ ለመሸሽ እራሱን አሳምኖ እንደመጣ ገባኝ ፡እናቴ የያዘችውን ደብዳቤ ለማንበብ ተዘጋጀች  ,,,,,,,,,,

ደራሲ unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj