Get Mystery Box with random crypto!

የ እናቴ ልጅ ክፍል አምስት የቀንስራ ከጀመርኩ ቆየው ይኸው እንዳይለመድ የ | አትሮኖስ

የ እናቴ ልጅ
ክፍል አምስት

የቀንስራ ከጀመርኩ ቆየው ይኸው እንዳይለመድ የለም ለመድኩት ፡እንደበፊቱ ከመድከም ባለፈ አጠነከረኝ አይምሮይንም አሳምኜ ልክ እንደ ስፖርት በመውሰድ ሰጥ ለጥ ብዬ መስራት ጀመርኩ ፡ እናንተዬ ለካ  ፡የነገሩ ክብደት ሳይሆን ኑሯችንን የሚያከብድብን የኛው የመቀበል ጉዳይ ነው  ወሳኙ፡
ይኽው አምኜ በምሰራው ስራ ይበልጥ ጠንካራ ሆኛለው  እንደበፊቱ መጠጣት መቃም ቀርቷል ግን ትንሽ የከበደኝ የሲጋራው ነገር ነው ጨርሶ ለማቆም አልቻልኩም በርግጥ መጠኑን ከበፊቱ ቀንሻለው  ፡ በምግብ በኩል ሆድ ለቆብኛል አብዛኛው ገንዘቤ በምግብ ነው የሚያልቀው ፡እውነቴን ነው በዚ የኑሮ ውድነት መቆጠብ አይታሰብም ፡ምን አልባት ቆጥበህ ጫማ ትገዛ ይሆናል እንጂ  ቆጥበህ ቤት አትገዛም ኪኪኪ እንኳን ታራ ስራ ሰርተኽ ደና ደሞዝ የሚከፈላቸው እንኳ  እኔ ከምገዛው የተሻለ ጫማና ልብስ ቢገዙ እንጂ ሌላ ነገርማ እንጃ  ፡
እኔ በገዛ ፍቃዴ ከእናቴ ጡረተኝነት ለመውጣት እየታገልኩ ነው  ፡ አቤል ግን ከእናቴ ጋር እንደተጣበቀ  ነው  መርካቶም ስትሄድ መከተል ነው  ቤት ውስጥም አብሮ መንጎዳጎድ ነው  ለራሱ የሚሰጠው ጊዜ ያለ አይመስልም ፡ በተቻለው መጠን እየተንከባከባት ነው ፡የሚገርመኝ ደሞ ይህን እንድታውቅለት ይፈልጋል ፡እናቴን የግሉ አድርጎ ነው የቆጠራት ከኔጋ ለማውራት እድሉንም አይሰጣት ፡ እሷም ብትሆን ለሱ ያላት ነገር ከመንሰፍሰፍም በላይ ነው ፡ ,,,,,
ወቅቱ ዝናባማ ነበርና ብርዱም ውጪ የሚያስመሽ ስላልነበረ  ትንሽ ጨለም ከማለቱ ነበር ወደቤቴ ለመግባት የሰፈሬን መንገድ የተያያዝኩት ፡በአካባቢው ላይ የሚጫወቱ ዕፃናትን ሳይ ኑ ግቡ የሚልም የለም እንዴ ፡ምነው የዚን ያክል ሰው ቸልተኛ ይሆናል ፡በርግጥ እንደኛ ሰፋፊ ጊቢ እና ትንሽ የሀብታም ልጅ የሚባሉ ልጆች የሉበትም ፡  ከትናንሽ ቤቶች ውስጥ የወጡ ልጆች ናቸው ቤታቸው አጥር ስለሌለው ሰፈር ውስጥ ከላይ ታች እያሉ ነው የሚጫወቱት ፡ቢሆንም ግን ሲመሽ ግቡ እና አጥኑ የሚል ወላጅ ከሌለ ለነገ ማንነታቸው ከባድ ነው  ፡መብትና ግዴታቸውን የማያውቁ ልጆች ካደጉ በዋላ  ልመልስህ ብትለው ፡ አትችለውም ፡ ስለነሱ እያሰብኩ አንዱ የሰፈራችን ቅያስ ጋር ስደርስ ጉድ አየው ምን አትሉም ወንድሜን ከሴት ጋር ሲነታረክ በዛላይ ዕፃን ልጅ ከተሸከመች ልጅ እግር ሴት ጋር ትንሽ ሸሸግ ብዬ አውቃት እንደሆን ለማረጋገጥ ሞከርኩ ጨርሶ አይቻት አላውቅም ፡ በጣም ተቆጥታ ነው የምታወራው ፡እሱደሞእየለመናት ነው  ምንድነው ጉዳዩ,,,,,,,,,

,ደራሲ unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj