Get Mystery Box with random crypto!

አንገቷን ፈጥርቄ ወዘዘዝኳት...ብርቱኳን እየሠነጠቁ ይገባበዙበት የነበረ ቢላዋ መሰለኝ ከአልጋው ጎ | አትሮኖስ

አንገቷን ፈጥርቄ ወዘዘዝኳት...ብርቱኳን እየሠነጠቁ ይገባበዙበት የነበረ ቢላዋ መሰለኝ ከአልጋው ጎን ካለ ጠረጰዛ ላይ አየሁ።አነሳሁት...።ልክ እንደፋሲካ ዶሮ አንገቷን በጥሼ ልጥለው ዝግጅ ሆንኩ።ግን ወዲያው ሀሳቤን ቀየርኩ።ምን አልባት እግዚያብሄር የዚህቺን ሴት ነፍስ ዛሬ ወደራሱ ሊወስድ ወስኖ እኔን እንደማስፈፀሚያ መሳሪያ እየተጠቀመብኝ ቢሆንስ...?የሚል ሀሳብ በምናቤ ተሠነቀረብኝ።ይቅርታ እጠይቀዋለሁ እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ ፈፅሞ እግዚያብሄርን ልተባበረው አልችልም። ወሰንኩ። ቢላዋውን ወለሉ ላይ ወረወርኩና እሷን ገፋታትሬ ከቤቴ አባረርኳት።

በታሪኩ ተመስጬ‹‹እሼ  ከዛስ ምን ተፈጠረ…?አግኝተሀት አታውቅም ?››ስል  ጠየቅኩት

<<ከወር ብኋላ...አገኘኋት ߹በተለመደ የዘወትር የስራ ላይ ገጠመኞች ድክም ብሎኝ እግሬን እየጎተትኩ ተዘግቶ ወደሚጠብቀኝ ቤት እያዘገምኩ ነው።በቤቴና በመስሪያ ቤቴ መካከል ያለውን ድልድይ መሻገር ስጀምር ድንገት አንድ ክስተት አይኔን ያዘኝ።የሆነች እንስት ወደጥልቁ ገደላማ ወንዝ እራሷን ወርውራ ለመሞት አቅዳ ይመስለኛል የድልድዩ የኮንክሪት መከለያ ላይ ወጥታ ትታያለች።አዎ ግምቴ ትክክል ነው እራሷን ለማጥፋት እየተዘጋጀች ነው።ላተርፋት ወሰንኩና እርምጃዬን ፈጠን አድርጌ ቀረብኳት...።ስጠጋት የማውቃት ሴት ነች።ከወር በፊት ከቤቴ ያባረርኮት የቀድሞ ሚስቴ ነበረች።ሀሳቤን ቀየርኩና እርምጃዬን ገታሁ።ፊቴን አዞርኩና ወደቤቴ መራመድ ጀመርኩ።ይህቺን ሴት እግዚያብሄር ሊወስዳት ስለፈለገ የራሱን መውሰጃ መንገድ ለሁለተኛ ጊዜ አዘጋጅቶላት ሳለ እኔ ምን ቤት ነኝ በውሳኔው ጣልቃ የምገበው...?አሁን እንደመሻቴ እሷን ከሞት ብታደጋት ዳግመኛ እግዚያብሄርን መፈታተን አይሆንብኝምን?አዎ ጣልቃ መግባት የለብኝም።"ቾቾቾ" የሚሌ የውሀ መንቦጫረቅ ድምፅ ከኃለዬ ሰማው... ውስጤ በሀዘን ስብርብር አለ..."ነፍስ ይማር ከማለት ውጭ ምን ማድረግ እችላለሁ?ምንም።
//
ከዛ በማግስቱ ከፖሊስ ጣቢያ ሬሳዋን ተረክቤ ቅድም ያየሽው ቦታ አምጥቼ ቀበርኮት..እና ይሄው በየሳምንቱ እየመጣሁ ለምን እንደዛ እንዳደረገቺኝ እጠይቃታለሁ…..ምንድነው ያጎደልኩብሽ….?መቼ ነው እንዲህ አንጀትሽን የሚበጥስ                ስህተት የተሳሳትኩት…..? እያልኩ ጠይቃታለሁ.. እንደታዘብሺው መልስ የላትም

ታሪኩን ነግሯት ሲያበቃ  ትንፍሽ አጥሯት ነበር?‹‹ለምንድነው ግን በድንገት ግራ የሚያጋብ ሰዎች ወደ ህይወቴ የሚገብቡት? ››
ከቦርሳዋ ብሮች አወጣችና ጠረጰዛ ላይ ወረወረች።
"ተነስ እንሂድ"
‹‹እንዴ ገና ጠጥቼ እኮ አልበቃኝም"
"አውቃለሁ...እቤትም ሰፈርም እንቀይር"
"ተይ አንቺ ልጅ እዚሁ ጥለሺኝ ሂጂ።"
"አይ ገና መገናኘታችን እኮ ነው...ደግሞ ሁለታችንም በአንድ አይነት በሽታ ነው እየተሠቃየን ያለነው.. በሽታችን ተመሣሣይ ከሆነ ደግሞ   የምድንበትም የመድሀኒት አይነት ተመሳሳይ ነው የሚሆነው ...እና…››
"እና ምን?"
"እናማ ተነስና መድሀኒታችንን  አብረን እንፈልግ"

ተስማማና ብርጭቆው ውስጥ የቀረችውን ጅን በአንድ ትንፋሽ በመጨለጥ  በሀሳቧ ተስማምቶ ተነሳ።ተያይዘው መኪና ውስጥ ገቡ። የት ነው? ወዴት ነው ብሎ አልጠየቃትም…መኪና ውስጥ ከገቡ በኃላ ምንም አላወሩም..ዝም ብሎ በመስኮት አሻግሮ አይኖቹን ወደውጭ ልኮ በመንገድ ጠርዝና ከማዶ የሚከወኑ ነገሮችን እየታዘበ ነው፤‹‹ምን አልባትም  በድኑ ብቻ ይሆናል አብሯት ያለው።  " እንደፈለገ ይሁን ዋናው እንደእኔ የታመመ የእኔን ህመም የታመመ ሠው ከጎኔ መኖሩን ነው።››ስትል አሰበች፡፡ቀጥታ ወደ ራሷ ቤት ነው ይዛው የሄደችው ߹ወደእናቷ አይደለም?ወደቃል ቤትም አይደለም߹እናቷ ወደአዘጋጀችላት የራሷ አፓርታማ ነው።ለምን እንደዛ ለማድረግ እንደፈለገች አታውቅም...ብቻ ስሜቷ ነው ያዘዛት...።
///
…እቤት ደርሱና ከሆቴል ቴክአዌይ ያሰሩትን ምሳ ከበሉ በኃላ ጀምረዉ የነበርነውን መጠጥ  ቀጠሉበት፡፡
ከአንድ ምናምን ሰዓት ትርኪ ምርኪ ወሬዋች ስያወሩ ከቆዩ በሃላ ድንገት ሰውዬው‹‹…እስኪ ገዳም የገባውን  ሰውዬሽን  ፎቶ አሳይኝ›› አላት
‹‹ለምን ፈለከው?››ጠየቀችው::
‹‹እንዲሁ….ምን ያህል ቆንጆ ቢሆን ነው እንዲህ ስብርብር ሰእስክትይ ያፈቀርሽው የሚለውን ለማወቅ ነው፡፡››አላት፡

ፈገግ አልችና‹‹…የእሱ ዋናው ውበቱ በውስጡ ߹ልቡ ላይ ነው ያለው….ያንን ደግሞ ፎቶ አያሳይም››በማለት ሞባይሏን ከጎኗ በማንሳት ከፍታ ፈልግ ፈልግ አድርጋ አንድ አብረው ሰልፊ የተነሳሱትን ፎቶ ሰጠችው››
ቀረብና ራቅ እያደረገ ደጋግሞ አየውና‹‹….እራሱ ነው››አለ፡፡
ግራ ገባት‹‹እራሱ ምን ?››
‹‹ፎቶውን የጠየቅኩሽ በጣም እየሰከርኩ ስሄድ ነገሮችን የማስታወስ ችሎታዬ ስለሚጨምር የሆነ ነገር ትዝ ብሎኝ ነው፡፡››
‹‹ማለት ቃልዬን ታውቀዋለህ?››
‹‹አይ አላውቀውም..ግን እዛ ሰውዬ ቀብር ላይ ልክ ዛሬ ካአንቺ ጋር እንደተገጣጠምን ከእሱ ጋርም ሁለት ቀን ተገጣጥመናል፡፡››
‹‹ምን?እየቀለድክብኝ እንዳይሆን?››
‹‹አይ በፍፅም እኔ ቀልድ የምወድ ሰው አይደለሁም .››.አላት….ዥው አለባት…ከስካሩ ጋር የሰማችውን ዜና መቋቋም አልቻለችም፡፡
‹‹ቃል ገዳም ካልገባ ከእኔ እየሸሸና እየተደበቀ ነው፡፡እኔ የህይወቴን ትልቁን ቁማር ተበልቼያለሁ፡፡ ምርጥ ፍቅሬን ባል የሚሆነኝን ሰው አስይዤ ቁማር ተጫውቼያለሁ..እናም ተበልቼ እሱን በማስረከብ ባዶዬን ቀርቼያለሁ፡፡ አዎ ቃል ፊት ለፊት እኔ ጋር ቀርቦ ምርጫው እንዳልሆንኩና እንደማያፈቅረኝ መንገር ስለከበደው ተስፋ ቆርጬ ሌላ ህይወት እስክጀምር ተደብቆኝ  እየጠበቀ ነው…አዎ አሁን የገባኝ ያ ነው፡፡ምን አልባትም ተጫውቼ ስለተበላሁት ቁማር ምስጢር አውቆ ተጠይፎኝም ሊሆን ይችላል፡፡ ›› ጭልምም አለባትና ሸርተት ብላ እዛው ሶፋ ላይ ተዘረጋጋች…..
‹‹…ተረጋጊ እንጂ …ማነሽ ቆንጆ ….አረ ተነሽ››የሰውዬው ድምፅ ትንሽ ትንሽ በሰመመን ውስጥ ይሰማታል፡…..
                                  
                 ተፈፀመ