Get Mystery Box with random crypto!

#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_አርባ_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ጎነኛው መቃብር ስር | አትሮኖስ

#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አርባ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ጎነኛው መቃብር ስር አንድ ሰው  እንደሀውልት ተገትሮ   ቆሟል...እዛ ያለ ይመስላል እንጂ በድኑ ብቻ እንዳለ ያስታውቃል። ሀዘኑ ሀዘኗን ቀሰበሰባት። ምኑ ይሆን የሞተበት"የማወቅ ጉጉት አደረባት።አንገቷን አሰገገችና ሀውልቱ ላይ የተፃፈውን ፁሁፍ አነበበች ወ/ሮ ቅድስት ሀምሳሉ 1980 ፡፡ 2015ዓ.ም ይላል።እድሜዋን በአእምሮዋ አሰላችው ።የሰውዬው  እድሜ ገመተች ..አርባ አመት ቢሆነው ነው በቃ ፍቅረኛው ወይም ሚስቱ ነች ስትል አሰበች።እንዲህ ካሠበች በኋላ ለሰውዬው  ያላት ሀዘኔታ ጨመረ፡፡

ለማታውቀው ሰው በዚህ መጠን ሰታዝን ይሄ የመጀመሪያ ገጠመኞ ነው። ምን አልባት እሷ  ገና ለገና ፍቅረኛ እንዲሆናት  የፈለገችው ሰው  ጥሏት ስለተሠወረ  እንዲህ እንቅሽቅሽ ካለች እሱ ደግሞ ፍቅረኛው ወይም ሚስቱ ለዘላለም ጥላው ሞታ ከምድር በታች አፈር ለብሳ ስትቀበር እንዴት ሊያዝን እንደሚችል አሰላችና ሰቀጠጣት...?ያው ለእሱ እያዘነች ቢመስላትም  በተዘዋዋሪ ለራሷ እያዘነች ነው። ወደኋላ  ተመለሰችና ለቃል አባት አምጥታ ሀውልቱ ላይ ካስቀመጥቻቸው አምስት የፅጌረዳ ዝንጣፊዎች መካከል ሁለቱን አነሳች ‹‹ይቅርታ በሚቀጥለው ስመጣ የእነዚህንም ፋንታ ይዤ መጣለሁ... ብድር ነው›› በማለት...ወደሰውዬው ሄደች.. አጠገቡ ቆመች...ከደቂቃዋች በኃላ ዞር ብሎ አያት አየችው.  ።

ጎንበስ አለችና አበባውን በሀውልቱ መሀከል ላይ አስቀመጠችው...፡፡ይደሰታል  ..ያመሰግነኛል ብላ ስትጠብቅ  በቅፅበታዊ ንዴት አይኖቹን አጉረጠረጠባት... ፊቱ በአንዴ ደም ለበሰ...አይኑ ውስጥ የሚንቀለቀል ከገሀነም እሳት የረገፈ ፍም ነው ያየችው..በዚህ መጠን ሰው አስፈርቷትም አስደንግጧትም አያወቅም....፡፡ጎንበስ አለና ያስቀመጠችውን አበባች አነሳና ብጥቅጥቅ አድርጓ ቆራረጣቸው፤ ተበታትነው መሬት ከመርገፍ የዳኑትን ወደ አፍ ከቶ  እያኘከና እየበጣጠቀ መትፍት ጀመረ…፡፡አንድ አምስት እርምጃ ወደ ኃላ ሸሸት አለችው...

‹‹እሷ አበባ ፈፅሞ አይገባትም.››."አሁን ይሄን መቃብር ብንከፍተው ስጋዋን እንዳለነው የምናገኘው..አፈር አይበላትም߹ ከበላትም ለአፈሩ አውዳሚ  አሲድ ነው የምትሆንበት ፤ምስጦችም አይበሏትም ከበሏትም ሰውነታቸው ተመርዞ ያልቃሉ"አላትና ጥሏት ሄደ...በህይወቷ በሞተ ሰው ላይ ሲሰነዘር የሰማችው በጣም መራርና አስከፊው  ወቀሳ ነው ፡፡በመሄዱ እፎይ አለች ..እዛ ከእሷና እሱ ውጭ  ሰው በሌለበት የቀብር ስፍራ  ሲጥ አድርጎ የሚገላግላት መስሏት በፍራቻ መንቀጥቀጥ ጀምራ ነበር ።አይ የሠው ልጅ ከደቂቃዎች በፊት   ለመኖር ያላት ጉጉት ተሟጦ አልቋል ስትል ነበር ..አሁን ደግሞ ህይወቷ ላይ ጥቃት እንዳይደርስ እየሠጋች ነው።እራሷን አረጋጋችና ኩስ ኩስ እያለች ከኋላ  ተከተለችው፡፡

ከመቃብር ቅጥር ጊቢ  ወጥቶ አስፓልት ጠርዝ ላይ ሲደርስ  እርምጃዋን ከእሱ እርምጃ ጋር ማስተካከል ቻለች....ዝም ብሎ መራመድን ቀጥሏል"ማኪያቶ ልጋብዝህ›› አለችው ..ሀሳብ ድንገት ነው የመጣላት፡፡

"አይ  ማኪያቶ አልወድም...አሁን  ጂን  ነው ምጠጣው"

‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው.. እንደውም እኔም እሱን ብጠጣ ጥሩ ይመስለኛል።››

"ጥሩ"
"መኪናዬን ግን  ፊታችን ያለው ሆቴል ነው ያቆምኩት… እዛ ብንጠጣ ቅር ይልሀል..?."ዝም ብሎ አቅጣጫውን ወደነገረችው ሆቴል አስተካከለ።ያ ማለት በሀሳቧ መስማማቱን ማሳያ አድራጋ ወሰደችውና ተከተለችው፡፡እንደዛው ጎን ለጎን እየተራመዱ ምንም ሳያነጋገሩ  ሆቴል ደረሱ..  በፅድ ተክሎች የተከበች ከለል ያለች ቦታ መርጠው ተቀመጡ የሚቀመጡበትንም ቦታ የመረጠችው እሷ ነች..)እሱ ለመጠጡ እንጂ ለቦታው ግድም ያለው አይመስልም፡፡

"ስለደረሰብህ ሀዘን በጣም አዝናለሁ››አለችው ፈራ ተባ እያለች፡፡

የእሷን አስተያየት ችላ አለና"አባትሽ ናቸው?"ሲል ጠየቃት…ደነገጠች

"ምን? ማን?"

"ቀብሩን ነው ያልኩሽ"

"እ...የእጮኛዬ አባት ናቸው...ማለቴ የፍቅረኛዬ...   ማለቴ የማፈቀረው ልጅ አባት"

"በአንድ ፅኚ እንጂ..የምን መወነባበድ ነው?"

"ወድጄ ይመስልሀል"

"የት ነው"

"ማ ?"
"እሱ...የምታፈቅሪው ልጅ"

"ገዳም ገባ"

መልሷን ከሰማ በኃላ ያዝንልኝና  ያፅናናኛል ብላ ስትጠብቅ

‹‹ተገላገለ" ብሎ እርፍ።

"እንዴት እንደዛ ልትል ቻልክ?"

"ያው አንድ ቀን ልቡን ሰብረሺው  ስቃይ ውስጥ ከሚገባ እንዲ በደህናው ጊዜ ገዳም መግባቱ ይሻለዋል"

"እንዴት ልቡን ልሰበር እችላለሁ ከራሴ በላይ እኮ ነው የማፈቅረው"

"እዛ የተኛችው ማለት ቅድም አበባ  የሠጠሻት ሴትም ከአመታት በፊት እንዲሁ አንቺ ያልሺውን ቃል  መቁጠር ከምችለው ጊዜ በላይ ብላኝ ነበር"

"ታዲያ ምን ተፈጠረ?"

"ያው እንዳልኩሽ ነዋ የልብ መሠበር"

"ሁሉም ታሪኮች ፍፃሜያቸው እንደምታስበው አይደሉም"

"ናቸው..ቆይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ?"

"ጠይቀኝ"

"አሁን ጥሎሽ ገዳም ከገባው ልጅ በፊት ፍቅረኛ ነበረሽ"

"አዎ ነበረኝ"

"ታፈቅሪው ነበር?"

"በወቅቱ አዎ አፈቅረው ነበር"

"ጥሩ ...እንደምታፈቅሪውስ ነግረሽው አታውቂም"

"በወቅቱማ እንዴት አልነግረው ...ፍቅረኛዬ ነበር...እንደማፈቅረው ብዙ ጊዜ ነግሬው አውቃለሁ።"

"በቃ መልሴ ተመልሶልኛል"

ድንግርግሯ ወጣ ።ምን ለማለት እንደፈለገ ምንም አልገባትም።

‹‹የምኑ መልስ?"

"ያው መጨረሻውን አየሽው߹ ከዛ ፍቅረኛሽ ጋር አሁን አብረሽ የለሽም...የሌላ ወንድ ፍቅር ፍለጋ በየመቃብር ሀውልቱ ትዞሪያለሽ ߹ያ ፍቅረኛሽ ግን ምን እየተሠማው እንደሆነ ምን ያህል እንዳዘነ ?በምን ያህል መጠን እየናፈቅሽው እንደሆነ ?ምንም ትዝ ብሎሽ አያውቅም አይደል?።"

ለወንዶች ያለው ውግንናና ለሴቶች ያለው ጥላቻ ጠርዝ የወጣ ነው ብላ ስላሰበች አበሳጫት።

"ምን እያልክ ነው..?ቺት ስላረገብኝ እኮ ነው  የተለያየነው"

"እ እንደዛ ነው?" አለና  ጅኑን አንስቶ ተጋተው
‹‹ምነው?  በቂ ምክንያት አይደለም?"

"ለወንድ አዎ .ለሴት ግን አይደለም"

"አልገባኝም?

"ሴት  መጀመሪያውኑ  ለመለየት  አቀባብለ እየጠበቀች ካልሆነ በስተቀር ፍቅረኛዋ ችት ስላደረገባት ብቻ አታባርረውም"

ዝም አለች። ይሄ  የአስፈሪው እንግዳ ሰው ንግግር ለሌሎች ሴቶች ይስራ አይስራ ባታውቅም  እሷን በተመለከተ ዝንፈት የለበትም...እናም ገፍታ ልትከራከረው አቅም  አላገኘችም።ለተወሰነ ደቂቆች በዝምታ እያሰላሠለች ጅኑን መሳብ ጀመረች።ድንዝዝ እንዲላት ፈልጋለች። ለዛሬም ቢሆን እንኳን  ሁሉን ነገር መርሳት።

"እስቲ ስለራስህ ንገረኝ...ስለእሷ...አበሳጭታህ  ስለሞተችው ሴት"

‹‹እርግጠኛ ነሽ መስማት ትፈልጊያሽ?››

‹‹አዎ በደንብ›› አለችና ለመስማት አቆብቆበች….አቀማመጧን አስተካከለች…ማውራት ጀመረ

‹‹የሶስት አመት ፍቅረኛና የአራት አመት ባለቤቴ ነች፡፡ከባለጉዳይ ጋር ስዳረቅ እና ከሀለቃዬ ጋር ስጨቃጨቅ ቆይቼ በድካም ውልቅልቅ ብዬ ወደ ቤቴ ስመጣ  በገዛ አልጋዬ ላይ ከገዛ ጓደኛዬ ጋር ተኝታ ደረስኩ።ከመተኛቷ በላይ ያበሳጨኝ ከእኔ ጋር ስትተኛ ሰምቼው የማላውቀውን በደስታ የመቃተት ድምፅ መስማቴ ነው። የወሲብ ፊልም አክተሮች እራሱ እሷ እያለከለከች እንዳለው አያለከልኩም። ለማንኛውም በአፍላ ስሜት ነቅናቂ ሙዚቃ በታጀበ ተራክቦ ላይ እያሉ ደረስኩባቸው።

እሱ በመስኮት ዘሎ ፈረጠጠ..እሷን ያዝኳት..።