Get Mystery Box with random crypto!

የ እናቴ ልጅ ክፍል አራት አንድ ቀን በጣም ደካክሞኝ ስለነበረ ምንም አይነ | አትሮኖስ

የ እናቴ ልጅ

ክፍል አራት

አንድ ቀን በጣም ደካክሞኝ ስለነበረ ምንም አይነት መጠጥ ሳልጠጣ በጊዜ ወደቤት ገባው ፣ እናቴ ቡና አቀራርባ ቤቱን ሞቅ አድርጋው ነበር አቤል ከሷትይዩ ካለው ሶፋላይ ተቀምጦ የቡና ቁርስ ፈንድሻ እየዘገነ ወደ አፉ ይልካል የኔ መምጣት ግድም አልሰጠው እናቴ ግን ያልተለመደ ስለሆነባት አተኩራብኛለች ፣ ምንም ሳልናገር ሄጄ ከቴሌቪዠኑ አጠገብ ተቀመጥኩ የኳስ ነገር ስለማይሆንልኝ በቲቪ የሚተላለፈው ጨዋታ አይላይት ቢሆንም እራሴንአሳርፌ ማየት ጀመርኩ አቤል ምቾት የሰጠው አይመስልም ሲያጉረመርም ሰማውት እናቴ ደሞ ዝም እንዲል ምልክት ትሰጠዋለች ፣ ውስጤ ቢናደድም ታገስኩ ፣እንደው ይሄልጅ ከዕፃንነታችን ጀምሮ እንደ ታላቅ እነቴ ስወደው ስከላከልለት ኖሬ ያለው ድንገት ሲጎረምስ እኔላይ ያለው ጥላቻ እንዲ አብጦ ሊፈነዳ የደረሰው ፡በኔ አይለኝነት ነው ወይስ ሌላ ችግር አለ ብዬ እራሴን መጠየቄ አልቀረም ብቻ እንደፈለገ ፡ በጣም የሚገርማቹ እኔ የዚ የተንጣለለ ጊቢ ባለቤት ሁሉም ነገር ከየት ይምጣ ከየት የሚነግረኝ ሰው ባይኖርም ሁሉነገር የተሟላበት ቤት ባለቤት ኪኪኪ ውይ ባለቤት አልኩኝ የቆንጆዋ የቤቱ ባለቤት ልጅ እኔ ፡ በእልህ የቤቱን ምግብ አልበላም ብዬ ፡ አንድ የሚገነባ ዕንፃ ላይ የቀን ስራ ተቀጠርኩ ይኽው በዛ ምክንያት ነው ዛል ብዬ የመጣሁት ፡ከእናቴ የኪስ ገንዘብ ለመውሰድ ምን አቅለሰለሰኝ በዛላይ የአቤል ግልምጫ ፡እሱ እንደው ሁሉም የኔ ማለት ከጀመረ ቆየ እሷም የአይኗ ብሌን አድርጋዋለች ፡እናት ግን እንዲ ስታዳላ አይገርምም በርግጥ እኔ ጥፋት የለብኝም ማለት አልችልም ግን እኔን በፀባይ መክራ ከማስተካከል ውጪ ከነ ልጇ እኔ ላይ ማመፅ ተገቢ ነው ? ይሁን እስኪ ዞር ብዬ ወደ እናቴ አየው ትኩረቷን ሙሉ በሙሉ ወደ አቤል መልሳለች ትንሽ ቀናው ምን አለ ከዚ ፍቅር ቀንሳ ትንሽ በሰጠችኝ ፡አሁን እኮ ሁሉንም ነገር ትቼ ሰላማዊ ለመሆን እየጣርኩ ነው የበለጠ የእናቴን ፍቅር ባገኝ እበረታ ነበር ፡ የቀንስራው የመጀመሪያዬ በመሆኑ እጄ ባሬላ የያዝኩበት ውሃ ቋጥሯል ፊቴ አመድ መስሏል ሰውነቴ ዝሏል እናቴ ግን በጭራሽ ግድ አልሰጣትም በርግጥ ብዙም አላየችኝም ።አቤል እኔ ስገባ ያቆመውን ወሬ ነው መሰል ቀጠለላት ፈገግ ፈገግ እያለ የእናቴን ቱኩረት በቀላሉ ነበር የሚስበው "
"እማ ታውቂያለሽ ጋሼ ግዛው ግን ምላሳቸው ምንድነው የሚባለው ጤፍ ይቆላል"ብሎ አቤል ሲስቅ ፡ እናቴ አብራው ሳቀች
"ክፉ ደላላ ነው ምን ሲል ነው የኔን ቤት ያየው መቼም ያለምክንያት አናግሮህ የማያውቀውን ልጅ ስለቤት ሽያጭ አያወራህም "ስትል ሰማዋት ልቤ ደነገጠ ምን የቤት ሽያጭ ፡ሲያወሩ እኔ ካለው እንኳ አልቆጠሩኝም ፡ አቤል ነገሩን ለማለስለስ ቃላት ሲመርጥ ተሰማኝ
"ኧረ እማ ሰውዬውኩ ስለ እኛ ቤት እኮ ያነሳው ጉዳይ የለም ብቻ ቡና እየጠጣው ድንገት ነው መቶ የተቀላቀለው ፡ከዛ ነው እንግዲ የወይዘሮ ሸዋረገድን ቤት በሃያ ሚሊዮን ብር አሻሻጥኳት እያሉ ሲያወሩ የሰማውት ከዛ ወደኔ ዞረው የአበባ ልጅ አይደለህም እንዴ አሉኝ ነኝ አልኳቸው ፡ከዛ ያወንድምህ በወጣበት አንተ ወጣህ " አሉ ሲል እናቴ የኔን ስም እንዳይጠራ እጇን አፏላይ በማድረግ አስጠነቀቀች እኔ ትኩረቴ ቲቪ ላይ የሆነ አስመስዬ ንግግራቸውን ማድመጥ ጀመርኩ "እና እማዬ ሰውዬው ያቁኛል ብዬ እንኳ አልገመትኩም እና ምን አሉኝ መሰለሽ ከእናንተ ቤት እኮ በግማሽ ያንሳል ፡ይኽው በአንድጊዜ አብታም አደረኳት "አሉኝ ብሎ ፈገግታው ይብስ ጨመረ እናቴ"ዝም በለው ባክህ እሱ ለሷብሎ አይደለም ደላላ ለራሱ ጥቅም ነው የሚሰራው "አለችና እናቴ ቡናውን መቅዳት ጀመረች
"እሱስ እማ ባለፈው የማማ ሸዋረገድን ልጅ አይቼው ነበር የሆነች ሱቅ ተከፍቶለት የራሱን ስራ ነው የሚሰራው በዛላይ የቤት መኪናም ገዝቷል አይገርምሽም "አላት እናቴ መልስ ሳትሰጠው የቀዳችውን ቡና ማማሰል ጀመረች ቀስብዬ ወደ አቤል ስመለከት እየተቁነጠነጠ ነው ፡እንዴ ይሄ ነገር ምንድነው የአቤል ፍላጎት አሳሰበኝ ከመቼው ትልቅ ሰው ሆኖ ነው ስለቤት ሽያጭ የሚያወራት በውስጤ ይሄንን ነው መፍራት አልኩኝ እናቴ ወደኔ ዞራ
"ቡና ልቅዳልህ አለችኝ"
"እሺ ግን አልበላውም "አልኳት እየደበረኝ ፡ አቤል የሽሙጥ ሳቅ ሳቀ ፡እናቴ ከተቀመጠችበት ስትነሳ ፡አቤል "ተይ አትነሺ እማ እኔ እሰጠዋለው "ብሎ ወደ ክችን ገባ እናቴ እሺ ብላ ቁጭ አለች
አቤል ወዲያው ነው የተመለሰው ሰአኑላይ ግማሽ እንጀራ በአንድ አይነት ወጥ አድርጎ አምጥቶ አስቀመጠልኝና ከእናቴ አጠገብ በመቀመጥ ፡የቅድሙን ወሬ ድጋሚ እያሰማመረ ያወራት ጀመር እናቴ ወሬው የጣማት አልመሰለኝም በዝምታ ታዳምጣለች ፡ እኔ ይሄኔ ነው አቤል ፍፁም ሌላ ሰው የመሰለኝ ለእናቴአዘንኩላት በሙሉ ልቧ ነው የምትወደው የሷ ምርጡ እና ልዩ ልጇ ነው ****


ደራሲ unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj