Get Mystery Box with random crypto!

'የማይሆን ነገር ለምን ታወሪያለሽ...?መጠበቅም ከሆነ ችግር የለውም..? የገዛ ቤትሽ ሆነሽ እስከ | አትሮኖስ

"የማይሆን ነገር ለምን ታወሪያለሽ...?መጠበቅም ከሆነ ችግር የለውም..? የገዛ ቤትሽ ሆነሽ እስከፈለግሽበት መጠበቅ ትቺያለሽ…እዚህ ማይመጥንሽ ቤት ውስጥ ግን አይሆንም፡፡"

"አይ እማዬ   አባቱ አረጋዊያን መኖሪያ ውስጥ ነው የሚኖሩት... አደራ ብሎኛል፡፡ ስለዚህ እሳቸውን ወደ እዚህ አመጣቸውና እየተንከብኮቸው እጠብቀዋለሁ..፡

."ልጄ አንቺ  ሁሉም ነገር ያለሽ ለጋ ወጣት ልጅ ነሽ.. እንዲህ ባለ የኪራይ ቤት ኩርምት ብለሽ የምትኖሪበት ምክንያት አይታየኝም ..ወደ አደግሽበት ቤት መመለስ ካልፈለግሽ እንኳን  የራስሽ አፓርትመንት አለሽ...እዛ ገብተሽ መኖር ትቺያለሽ..ከፈለግሽም አባቱን ወደ እዛ ወስደሽ በሞጎዚት እንክብካቤ እንዲደረግለት ማድረግ ትቺያለሽ… እኔ ምንም ተቃውሞ የለኝም፡፡
እናቷ ቀኑን ሙሉ እሷን ለማሳመን ስትጨቀጭቃት  ውላ በመጨረሻም ተስፋ በመቁረጥ በሀዘን ተሰብራ ወደቤቷ ተመለሰች፡፡

ይቀጥላል