Get Mystery Box with random crypto!

#ባል_አስይዞ_ቁማር›› ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ክረምቱ ሲመጣ ሰው | አትሮኖስ

#ባል_አስይዞ_ቁማር››


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ክረምቱ ሲመጣ ሰውነቷ ይሸማቀቃል።ዝናብ ትወዳለች ግን ነጎድጓድና መብረቅ ያስፈራታል። በሰማዩ ላይ ቀስተደመና ሲነጠፍ ልቧ ላይ የተጠመጠመ ኒሻን ይመስለትና ትፈነጥዛለች፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለሙ ከኢትዬጰያ መቀነት ጋር መመሳሰሉ ሁሌ እንዳስደመማት ነው።እርግጥ ሳታድግ የቀሰት ደመና የተሸመነባቸው ቀለሞች ሶስት ብቻ ሳይሆኑ ሰባት እንደሆኑ ማወቅ ችላለች።ግን ደግሞ ማወቅና ማመን ይለያያል...ዛሬም አይኖቾን አንጋጣ ቀስተደመናውን ሳታይ በትክክል ወደውስጧ ደምቀው በመግባት የሚውለበለብት እነዛው በልጅነቷ የምታውቃቸው ሶስቱ ቀለማት ብቻ ናቸው።አረንጓዴ ቢጫ ቀይ..."አንዴ አትለከፍ"ትላለች አክስቴ አዎ ልክፍት ነው።››አለች
በማግስቱ ጥዋት መድህኔ መጥቶ ጊፍቲን ወሰዳት….ስራ ስለምትገባ ቅያሪ ልብስና ለሁለቱም የሚሆን ቆንጆ ቁርስ አሰርቶ ነበር  ይዞ የመጣው….ልክ የእሷ እንዳልነበረና ከዚህ በፊት እንደማታውቀው ወንድ አይነት ትክ ብላ አየችው…አሳዛኝና እንስፍስፍ ወንድ ሆኖ ነው ያገኘችው...እንስፍስፍ ያለችው አፍቃሪ ላለማለት ጎርብጦት ነው….‹‹አሁን ጊፊቲን ካገኘ በኃላ ተቀይሮ ነው ወይስ በፊትም ከእኔ ጋር እያለ እንዲህ ነበር ..?››በወፍ በረር ወደኃላ መለስ ብላ ለእሷ የሚያደርግላትን እንክብካቤዎች ለማስታወስ ሞከረችና ሽምቅቅ ብላ ቶሎ ተመለሰች‹‹…ከእሱ ምንም የተለወጠ ነገር የለም ልዩነቱ እኔ መሆኔና ጊፊት መሆኗ ላይ ነው…እሷ ከእሱ የሚሰጣትን ፍቅርና እንክብካቤ በትህትና እና በምስጋና ተቀብላ በፈገግታ ምላሽ ስትሰጥ እኔ ግን በወቅቱ አደርግ የነበረው በብስጭት በመግፋትና በተቃውሞ ነበር ሞራሉን የምሰብረው….እንደውም አሁን መጠየቅ ያለብኝ ያን ሁሉ ጊዜ እንዴት ታግሶኝ ኖረ….?. ›ስትል ድምዳሜ ላይ ደረሰች፡፡
ልብሷን ቀየረችና ካመጣው ቁርስ አንድ ሁለቴ ጎርሳ ጉንጩን ሳመችውና ስትወጣ መድህኔ ደግሞ ወደልዩ ዞሮ‹‹…እንዴት ነው ግፍቲን ቢሮ ካደረስኮት በኃላ መጥቼ ወደቤት ልውሰድሽ እንዴ.?.››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ አልፈልግም..አላየህም እንዴ .?.መኪናዬ እኮ እዚህ ግቢ ውስጥ ነች…››
‹‹እንዴ..ለመንዳትም አቅም የለሽ ..መጥቶ ይውሰድሽ››ጊፍቲ መሀከል ገባች…‹‹.ይቺ ልጅ በፊት ሳገኛት እንደገመትኮት አይነት አይደለችም..ቀናና ጥሩ ሰው ነች..አሁን ሌላ ሴት ብትሆን እኮ ጭራሽ እንዲህ ስላለ ፍቅረኛዋን በግልምጫ ነበር የምታደባየው..መልሳ ብትወስድብኝስ በሚል ስጋት እራሷ ደንብራ አካባቢዋ ያለውን ሰዎች ሁሉ ታስደነብር  ነበር…››ስትል አብሰለሰለች
አይ ..አልፈለግም..እኔ በአሰኘኝ  ሰዓት መንዳት እችላለሁ..ደግሞ ብሔድም ከሰዓት ነው››
‹‹እሺ በቃ ቁረሱን  ተነሺና ብይ..እና ከፈለግሺኝ ደውይልኝ››አለና  ቤቱን ዘግተውላት ተያይዘው ሄዱ ፡እሷም መልሳ እራሷን ትራስ ውስጥ ቀበረችና ወደትካዜዋ ገባች..እራሷን ትራስ ውስጥ ስትከት የቃልን ጠረን በአፍንጫዋ እየተሹለከለከ ወደመላ ሰውነቷ በደምስሯ አማካይነት ተሰራጨና የንዝረት ስሜት በሰውነቷ ለቀቀባት፣
//
በሶስተኛ ቀን እናቷ መድሀኔ እየመራት ያለችበት ድረስ መጣች....ስታያት እንባዎን መቆጣጠር ነው ያቃታት....፡፡

"ምነው መድህኔ ..ምነው ልጄ እንዲህ እስክትሆን እንደው ሁሉ ነገር ቢቀር እህትህ አይደለች?"በማለት ወቀሰችው፡

"እትይ...ከገባችበት ነገር እንድትወጣ በተቻለኝ አቅም ያልጣርኩ ይመስልሻል...?..ሰሞኑን ስራ እንኳን በቅጡ መስራት አልቻልኩም...በቀን ከሶስት ጊዜ በላይ እየተመላለስኩ ለምናታለሁ..ግን ያው እንደምታይው ነች"አለ ..ጥረቱና ልፋቱ መና ስለቀረበት ቅር እንዳለው በሚያሳብቅ የምሬት ንግግር

የልዩ እናትም ከጠንካራ ንግግሯ መለስ አለችና"ልጄ የቻልከውን እንደምትሞክር አውቃለሁ ..የምናገረውን አትይብኝ ደንግጬ ነው"አለችው

"ችግር የለም ይገባኛል....አሁን እናንተ አውሩ ...እዚሁ አካባቢ ነኝ… ስትጨርሺ ደውይልኝ።"ብሎ እናትና ልጅን አፋጦ ወጥቶ ሄደ...እንደዚህ ያደረገው በነፃነት እንዲያወሩ በማሰብ እንደሆነ ሁለቱም ገብቷቸዋል ።ልዩ ግን ምንም የምታወራበት ጉልበት የላትም...ለዛውም ከእናቷ ጋር"

"ልጄ በራሴ አፍሬያለሁ...እኔ እኮ እራሴን እንደዘመናዊና ግልፅ እናት ነበር  የምቆጥረው ..ግን ተመልከቺ ልጄ በዚህ ልክ የምታፈቅረው ሰው ኖሮ እንኳን አላውቅም...."

"እማዬ እሱ የእኔ ጥፍት ስለሆነ አትዘኚ..."አለቻት።

‹‹አይ ልጄ ...ለነገሩ ተይው አሁን ነገሮች ከተበለሻሹ በኃላ ብናወራው ምን ፋይዳ አለው....?..አሁን ይበቃሻል ማልቀሱም ማዘኑም በገዛ ቤት ያምራል...ልጄ ወደ ቤታችን እንሂድ"አለቻት ፈራ ተባ እያለች...ልዩ ምንም አላለቻትም… የውስጧን ጥንካሬ አሰባስባ ቀስ ብላ ተነሳችና እግሯን እየጎተተች ወደ መኝታ ቤት ስትራመድ ውስጥ ገብታ በራሷ ላይ ልትቆልፍ መስሏት የሰጋችው እናት"ወዴት እየሄድሽ ነው ልጄ?"ስትል ጠየቀቻት፡፡

"መጣሁ… የማሳይሽ ነገር አለ›› በማለት ወደ ውስጥ ገባችና  ማንጠልጠያ ላይ ከተንጠለጠለው ቦርሳዋ ውስጥ እጇን ሰዳ  የምትፈልገውን እቃ ያዘችና ወደሳሎን ተመለሰች..."
እናቷ ፊት ለፊት አስቀመጠቻት ...እናቷ ደንግጣ አንዴ እሷን አንዴ ጠረጰዛው ላይ ያለውን ዕቃ በማፈራረቅ ታየው ጀመር… ‹እማ ..በቀደም ለት  ዝግጅት አለብኝ ብዬ እንደዛ ለግማሽ ቀን አምሬና ተሽቀርቅሬ እነዚህን ሁለት ቀለበቶች  ገዝቼ  ወደ እዚህ ቤት የመጣሁት ለቃልዬ ቀለበት ላስርለት ነበር..፡፡.በድፍረት እንዳፈቀርኩት ነግሬው እንዲያገባኝ ልጠይቀው ነበር...ስደርስ ግን ሁሉን ነገር ጣጥሎ ገዳም እንደገባ  የሚገልፅ ደብዳቤ ጥሎልኝ ሄዷል...ይሄ ሁሉ የእኔ ጥፍት ነው ። አረባም ፡፡››

"ምን አጠፋሽ የእኔ ማር....?.."

‹‹ምን ይሄን ሁሉ ጊዜ አዘገየሸ...ከ15 ቀን በፊት ላደርገው እችል ነበር እኮ...ከወር በፊትም ባደርገው ጥሩ  ነበር"

"ልጄ እንደው ቢጨንቅሽ ነው...ይሄ እንደሚመጣ በምን ልታውቂ ትቺያለሽ....?.."

"ደግሞ የዛሬ ሳምንት በጣም አበሳጭቼዋለሁ..››

"ምን አድርገሽ ልታበሳጪው ትቺያለሽ?"

‹‹ሰርቄ ነዋ...ሆቴል ልጋብዝህ ብዬ ወስጄ ሰረቅኩ...በእፍረት አንገቱን ደፍቶ የሠረቅሽውን መልሺ አለኝ .....እኔም መለስኩ ..ከዛ ሲመክረኝ ዋለ ..በማግስቱ  ይቅርታም ልጠይቀው እንደማፈቅረውም ልነግረው ቀጥሬው በሰዓቱ  ብገኝ  እንዳልኩሽ ሆነ...ዳሩ ሌባን ማን ማፍቀር ይፈልጋል?"
"ልጄ አሁን እኮ ባለፈ ነገር ዝም ብለሽ ነው የምትጨናነቂው... እንዳልኩሽ ተነሽና ወደቤታችን እንሂድ፤ከዛ  በእርጋታ እንደ እናትና ልጅ አናውራ። የሚስተካከለውን እናስተካክላለን"

"የምለውን አልሰማሽም እንዴ እማዬ?"

"ምን አልሽ?"

"እሱ ሸሽቶ ቢሄድም እኔ እኳ አግብቼዋለሁ ....ከተቀመችበት ተንጠራራችና ቀለበቶቹን አነሳች የራሷን ቀለበት አጠለቀች
"...እማዬ ደግሰሽ ባትድሪኝም እኔ አግብቼያለሁ...እና እዚሁ ሆኜ መጥቶ ይሄን ቀለበት እስኪያጠልቅ እጠብቀዋለሁ።"

"ምን ነካሽ...?በግልፅ እኳ መቼም ላይመለስ አንደኛውን ወደ ገዳም እንደገባ ነግሮሻል?..እና ምንድነው የምትጠብቂው ?እስከመቼስ ነው የምትጠብቂው?"

"እማዬ ልቤ ተመልሶ እንደሚመጣ እየነገረኝ ነው...ከሁለት አመትም ሆነ ከሀያ አመት በኃላ አንድ ቀን ተመልሷ ይመጣል...እና እዚሁ ቤት ሆኜ እጠብቀዋለሁ።››