Get Mystery Box with random crypto!

የ እናቴ ልጅ ክፍል ሁለት እናቴ ለረጅም ጊዜ ቤቷን ዘግታ ታስተዳድረን ነበ | አትሮኖስ

የ እናቴ ልጅ
ክፍል ሁለት

እናቴ ለረጅም ጊዜ ቤቷን ዘግታ ታስተዳድረን ነበርና ነገሩ እየገረመኝ የመጣው ማስተዋል በጀመርኩ ጊዜ ነበር እንዴት ሁለት ልጆቿን ያለምንም ስራ የሚፈልጉትን እያሟላች ማኖር ቻለች በእርግጥ ያትልቁ ቤታችን ከሰፊ ግቢው ጋር ከአባቷ በውርስ እንዳገኘችው አውቄአለው እሱንም ከታናሽ ወንድሜ አቤል ነው እሱ እንዴት እንዳወቀ እንኳ ጊዜ ሰጥቼ አልጠየኩትመ በወቅቱ ነገርግን ስራ ሳይኖራት ያን ያለፈችውን አመታት እኛን ዘግታ እራሷንም ዘግታ ባኖረችን ግዜ ገንዘቡን ማለትም ወጪዎቿን የሚሸፍንላት ማን ነበር ይሄን ለማወቅ ስል አንድ ሁለቴ ጠይቄያት ነበር ነገርግን እናቴ ለኔ መልስ ከመስጠት ይልቅ አፌን ማዘጋት ይቀላታል !
"እናቴ ?"ስላት ገና ፊቷን እንኳ ወደኔ ሳታዞር
"አቤት" አለችኝ ደረቅ ባለ ድምፅ፣ አቤል ግን ወደኔ ዞረ ምን ሊል ነው በሚል አስተያየት ተመለከተኝ
"እኔ የምልሽ ግን ያንን ሁሉ አመታት እኔ ማስተዋል ከጀመርኩበት ጊዜጀምሮ አስታውሳለው ከቤት ወጥተሽ አታውቂም ነበረ እና እንድትመልሺልኝ የመፈልገው ነገር ቢኖር ፣ እንዴት ነው የሁለታችንንም ወጪ ሸፍነሽ ልታኖሪን የቻልሽው እስከማስታውሰው አንድም ነገር አላጎደልሽብንም ይሄን እንዴት ማድረግ ቻልሽ ? ሌላው ለምን ብለሽ ነው ከቤት የማትወጪው የነበር ?"ብዬ ለመልሷ ተዘጋጅቼ አይኖቿን ፈልጌ ለማየት ሞከርኩ ፣ ለመልሱ ዘገየች አቤል ሲነጫነጭ ወደሱ ዞርኩ ገላመጠኝ የእናቴ አሳቢ ልጅ ምን ብዬ ጭንቅላቴን በምልክት ነቀነቅኩ ፣እናቴ ድንገት ብድግ ብላ " አይመለከትህም ትኩረትህን እራስህ ላይ አድርግ ሌላውን ለኔ ተውልኝ እሺ ሲጀመር የልፋቴን ውጤት እንኳ አንተ ላይ አላየውም ! ትልቅ ቦታ ጠብቄህ ነበር ተመልከት በአጉል ባህሪክ የተነሳ ከኮሌጅ ተማሪነት የዘለለ ውጤት አላመጣህም ፣ይባስ ብለህ እኔ በምሰጥህ የኪስ ገንዘብ አጉል ልምዶች አመጣህበት አንተ ስለምንም የመጠየቅ መብት የለህም ያባቱ ልጅ ..."አለች ከላይ እስከታች ስትወርድብኝ ምንም አልመሰለኝም ፣ነገርግን ሞቷል ያለችንን አባታችንን ስትወቅስ ግን ለዛውም ከኔጋር አገናኝታ አልተመቸኝም ግን የዛን ለት ምነው አፌን በዘጋው ነበር ያልኩት በላዬላይ የናቴን ጥላቻ ይብስ ጨመርኩ ፣ምግብ እንኳ ስትሰጠኝ ፊቴን አታየውም ፣
አቤል ደሞ እሳት ላይ ቤንዚን ማርከፍከፍ ይችልበታል እሷ ፊት የሚያሳየኝ ባህሪና እደጅ አንድ አይደለም ፣ በዚ ትንሽ ብናደድበትም መቼም ታናሽ ወንድም ነውና እታገሳለው የሚገርማቹ እኔ እንዲ አትንኩኝ ባይ የሰፈሩ አንበሳ ተብዬ እንኳ አቤል እንደፈለገ ቢሆን እጄን አንስቼበት አላውቅም በጣም ነው የምወደው ከእናቴስ ቀጥሎ ያለሱ ማን አለኝ ፣,,,,,,,,
ዛሬ ሃያ አንድ አመቴ ነው እና ሁሉም ነገር ጥያቄ የሚፈጥርብኝ ወቅት ላይ ደርሻለው የእናቴ ብቸኝነት ከሷውጪ ሌላ ዘመድ አለማወቅ የወንድሜ ከኔጋር ያለው የሻከረ የመጣ ግንኙነት ,,,,,,,???
ሰኞ ቀን ጠዋት ነው ክፍሌ ውስጥ ጋደም እንዳልኩ ነው ከሳሎን ቤት የሰአን እና የበርጭቆ ድምፅ ይሰማኛል እናቴ ለቁርስ እያዘጋጀችው መሆን አለበት ፣መሃዛው የሚያውድ የሻዪ ሽታም ይሰማኛል ፣ማታ ጠጥቼ ነው የገባውት እና በውስጤ ያለው ምግብ እልቅ ብሏል ስጠጣ እንኳ ብዙም አልበላሁም ፣እና ሆዴ በረሃብ ተላወሰብኝ ፣ወጥቼ ቁርስ ከነሱጋር እንዳልቀመጥ ይሄንን ልምድ በነሱ ግልምጫ የተነሳ ትቼዋለው ፣ ማድረግ ያለብኝ ወይ አፍንጫዬን መዝጋት ነው ወይም በቱን ጥሎ መውጣት ፣አፍንጫዬን ለመዝጋት ሞከርኩ አልሆነም ፣ስለዚ ተነስቼ ልብሴን ለባብሼ ፣ ወጣው ስወጣ እየበሉ ነበር ፣እናቴ "ወዴት ነው ችኮላው "አለችኝ አብሬያቸው እንድበላ የፈለገች ትመስላለች ምንም እንኳ ኮስተር ብትል ። አቤል ግን ቀበል አድርጎ "ያው በጠዋቱም ሊጋት ይሆናላ መቼም ትምህርቱም ተመርቆ ቢያልቅም ስራም አላስገኘለት እኔማ እየወሰደ የነበረው የመጠጥ ኮርስ ነበረ እንዴ ኪኪኪ"ብሎ ሳቀ ቅስሜን ሰባበረብኝ ግን ምንም አላልኩትም ከሱ ንግግር ለማምለጥ እየተጣደፍኩ ወጣው ,,,,,,,


,ደራሲ unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj