Get Mystery Box with random crypto!

#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ስምንት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ..ይገርማል እሱ በ | አትሮኖስ

#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

..ይገርማል እሱ በማንኛውም አእምሮዋ በሚያመርታቸው ሀሳቦች ውስጥ የሆነ ቦታ ፈልጎ ተሸንቅሮ ሲወጣ ነው የምታየው....ስለሰማይም ታስብ ስለምድር…ስለእግዚያብሄር ይሁን ስለሰይጣን እሱ አለበት….፡፡.ደግሞ በሀሳቧ ብቻ አይደለም በህልሟም ጭምር እንጂ…..ህልሟ እኮ ስለ ምንም ሊሆን ይችላል ብቻ እሱ አለበት…ለምሳሌ እሷ እናቷ  መኝታ ቤት አልጋዋ ላይ ወጥታ ፀጉሯን ስትዳብሳት በህልሟ ብታይ እሱም ወይ በመስኮት ተደብቆ ሲያያት..ወይ ደግሞ እራሱን ወደቢራቢሮ ቀይሮ ክንፉን እያማታ መጥቶ ግንባራ ላይ ሲያርፍ ታየዋለች፡፡ይሄ ሁሌ ለራሷም ሳታስበው ግርም ይላታል፡፡እንዴት የሆነ ቦታ ላይ አትረሳውም…እንዴት የሆነ ሀሳብ አሰናድታ አጣጥፋ ስትጨርስ ድንገት ከሆነ ቦታ ተስፈንጥሮ መጥቶ ከላይ በቀላሉ ይደረባል…?ይሄ እንግዲህ በዚህ ከተማ በዚህ ቤት ውስጥ ሲኖር ነበር..አሁንስ ሁሉን ነገር ጣጥሎ ከሄደ በኃላ…….ምንድነው የምትሆነው?የቀንም ሆነ የሌት ህልሟ እንደሆነ ይቀጥላል? ከቀጠለስ እንዴት ልትቋቋመው ትችላለች?
እጇን ዘረጋችና አጠገቧ የተኛችውን የጊፊቲ ሆድ ላይ በቀስታ አሳረፈች…ጊፍቲም ከትራሷ ገልበጥ አለችና ፊቷን ወደእሷ ዞራ በሀዘኔታ አየቻት፡፡
‹‹ምን አለ እኔም እንደአንቺ ለቃልዬ አርግዤ ቢሆን…ማለት ልጅ አስረግዞኝ  ጥሎልኝ ቢሄድ?››
‹‹እኔም አንድ ነገር ልንገርሽ…››
‹‹ምንድነው ንገሪኝ››
‹የቃልዬን እስከ ወዲያኛው ጥሎኝ መሄድን ስሰማ ወደውስጤ ከመጣው የፀፀት ሀሳብ አንዱ ምን አለ ይሄ የፀነስኩት ልጅ የቃልዬ በሆነ የሚል ነበር..እርግጥ መድህኔ በጣም ጥሩ ኃላፊነት የሚሰማው መልካም አባት እንደሚሆን አውቃለሁ…እሱን ስላገኘሁም እራሴን እንደእድለኛ ነው የምቆጥረው…የልጅነት ህልሜንና  የዘመናት ፍላጎቴን ሁሉ ሊያሞላልኝ የሚችል ሰው ነው…ግን መድህኔን የማፈቅርበት ጥልቀት የኩሬ ያህል ሲሆን የቃልዬ ግን ውቅያኖስ አይነት ነው..እና ለዛ ነው እንደዛ ልመኝ የቻልኩት››
ዝም ብዬ ፈዛ አየቻት..ይሄን የተናገረችው ከቀናቶች በፊት በሰላሙ ጊዜ ቢሆን ኖሮ በርግጠኝነት ልዩ አንገቷን ፈጥርቃት ልትገላት ሁሉ  ትችል ነበር..አሁን ግን ያንን ማድረጉም ብቻ ሳይሆን እንደዛ አይነት ስሜት ማስተናገዱም ጥቅም አልባ እንደሆነ ተረድታለች....በዛ ለይ በመንፈስም ሆነ በስጋዋ ደንዝዛለች…
‹‹ግን ከቃልዬ ይሄን ሁሉ አመት ሳታረግዤ እንዴት በዚህች በጥቂት ወራት ከመድህኔ ልታረግዢ ቻልሽ?፡፡››
‹‹ከቀል ጋር በትንፋሽ ነው ማረግዘው?…››
‹‹ማለት….?››
‹‹እኔና ቃል እኮ  ወሲብ ፈፅመን አናውቅም››
‹‹ማለት…ብዙ ቀን እኮ እሱ ጋር አድረሽ እንደወጣሽ… ሲያደክመኝ እንዳደረ ምናምን እያልሽ ስትጎሪርብኝ ነበር››
‹‹ፈርቼሽ ነዋ…..ቃልዬን እንዳትመኚውና እንዳትቀሚኝ ..ተስፋ ላስቆርጥሽ ብዬ ነው…ማለት ከአመታት በፊት  አብሬው ብዙ ጊዜ አድር ነበር..በኃላ ግን ዝም ብሎ ማደሩ ስቃይ ስለሆነብኝ ወስኜ አቆምኩ…..››
‹‹አረ የምን ጉድ ነው..ቆይ ለምን…..?››
‹‹ምነው ገረመሽ..አንቺስ ከመድህኔ ጋር ለምን;?››
‹‹እኔ እንጃ ብቻ የእናንተን በጣም ደጋግሜ ስላመነዠግኩት ነው መሰለኝ አልተዋጠልኝም…››
‹‹መድህኔን ስለወደድኩት..ወይም ቃልዬ ሀብታም ስላልሆነ ይመስልሻል ከቃልዬ ጋር አቋርጬ ከመድህኔ ጋር የሆንኩት ነው  ወይስ አንቺ ስላለስፈራራሺኝ…?››
‹‹እና ለምንድነው?››
‹‹ሳላውቅ ድንገት ከመድህኔ ጋር ተሳሳትኩና ወሲብ ፈፀምኩ..ድንግልናዬን አስረከብኩት ….ወደቃልዬ ጋር እንዴት ልመሰለስ .. ?ሌላ ሰው ቢሆን ችግር የለውም ቃልዬ ግን?
‹‹ቃል ምን ይልሻል..?ምንም አይልሽም እኮ ነበር አንደውም በግልፅ ነበር ይቅርታ የጠየቀሽ፡››
‹‹አውቃለሁ ..ችግሩም እሱ ነው….እኔ በአእምሮው ካለሁበት ቦታ ተንሸራትቼ ወርጄያለሁ.ቃልዬ...የወርቅ ካባ አድርጎ  በብር የተለበጠ  ጫማ ተጫምቶ ወደቤቴ ሲመጣ ውስጤ በሀሤት ትደንሳለች ...ድንግልናዬን በክብር ልሰጠው ለዘመናት ጎጉቼያለሁ ።.እሱ ፍጽም ድንግል እንደሆነ አውቃለሁ.....ማወራሽ ስለስጋዊ ድንግልና አይደለም….ለዛ ግድ የለኝም...ልብ ከቆሻሻ ሀሳብ ጋር ያልተዋሰበ ንፅህ ፤ከክደትና ከማጭበርበር ጋር ያልተጋደመ  ክብር  ነው ።ለዚህም ማረጋገጫው እስሬ ሆኖ ሲያወራኝ  ልቤ ውስጥ ብርሀን ሲፍለቀለቅ ይታወቅኛል….የሆነ አካሉ የሰውነቴን ጫፍ ሲነካው ነፍሴ ድረስ የሚዘልቅ ደስታ ይሰማኛል……ድንገት አግኝቼው  ሰላም ሊለኝ  ከንፈሩ ጉንጬን በስሱ ሲነካው እንኳን .....ከልቤ  የፍቅር ደም ሲንጠባጠብ ይሰማኛል ...
‹‹ከዚህ በፊት ስለእሱ ምን እንደሚሰማኝ ነግሬሽ ነበር …? የእኔን ስሜት እኮ ነው እየነገርሺኝ ያለሽው…››
‹‹አየሽልኝ..ቃልዬ ማለት እንዲህ ነው..ሁለት ሴቶችን ጫፋቸውን ሳይነካ በተመሳሳይ የእብደት በሚመስል ስሜት አንዲያፈቅሩት ማድረግ የሚችል የተለየ ሰው ነው፡፡እሱ ለእኔ መስታወቴ ነው.. ፊት ለፊቴ ተቀምጦ በተመስጦ  ሳየው በጥልቀት ርቄ ሄዳለሁ…. እያንዳንዷን የልጅነት ጊዜዬን በምልስት አስታውሳለሁ… ሀዘኔንና ደስታዬን መልሼ አጣጥማለሁ…. እንዴት እንደተሰራው…? የት ጋር  ማደግ እንደጀመርኩና? የት ጋር ደግሞ እንደተሰበርኩ? ሁሉ እንዳስታውስ ያደርገኛል…እናም በዛ ምክንያት ቃልዬን ሳገኝ  ነፍሴ ሀሴት ታርጋለች…ውስጤ ይፍነከነካል..፡፡ግን ይሄ ስሜት ሁሌ አይደለም የሚያስደስተኝ ..አንዳንዴ ትናንቴ ፈፅሞ የሚያስጠላኝ ጊዜ አለ..አንገቴን ወደኃላ አዙሬ አይኖቼን ትናንቴ ላይ ተክዬ ማሰላሰል የሚያስከትልብኝን ህመም መቋቋም አቅም በማጣበት ጊዜ እሱን ለማግኘት ከራሴ ጋር ትግል እገባለሁ  …ምክንያት ፈጥሬ እሸሸዋለሁ….
ግን የሰዓታ ክፍተት እንኳን መቆየት ተስኖኝ  ግራ ይሁን ቀኝ ልቤ ላይ ብቻ በማለውቀው ቦታ በሆነ የልቤ ክፍል ብቸኝነት  ይለበልበኛል…መለብለብ ብቻም ሳይሆን እብጠትና ጥዝጣዜም አለው…ግን ደግሞ መቻል እስከምችል ደረስ እችለዋለሁ…ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን..ከዛ መተንፈስ ሲያቅተኝና ከአቅሜ በላይ ሲሆን ያለምን ማቅማማት ወደ አለበት በርሬ እሄዳለሁ ፡፡ፊቱ እገተራለሁ…የተጨማደደ ፊቱ በደስታ ፀደል ሲፈካ…ተከርችሞ የነበረ ጥርሶቹ ተፈልቅቀው  መሳቅ ሲጀምሩ አይና እደሰታለሁ....ተንደርድሬ ሄጄ እንጠለጠልበታለሁ….ያለምንም ቅሬታና ወቀሳ ወደላይ አንጠልጥሎ ልክ እንደእርግብ በአየር ላይ ያንሳፍፈኛል…..እና አሁን ያ የልጅነተ መስታወቴ ነው የተሰነጣጠቀዉ… የትዝታ ድልድዬ ነው ተንዶ የተሰበረው…..ወደትናንቴ ለመሻገር በጣም ይከብደኛል….ግማሽ  ሆኜያለሁ
‹እውነትሽን  ነው…..አሁን ሳስበው ቢነካንስ ኖሮ…ማለቴ ያው ነካክቶን ጥሎን ሂዶ ቢሆንስ..?››
‹‹እሰከ መጨረሻ ያበቃልን ነበራ…››ብላ መለሰችላት፡፡
‹‹እኔ እኮ አሁንም እስከመጨረሻው ነው ያበቃልኝ…›
‹‹ቆይ ግን ወደ ወሬሽ ልመልስሽና..ቃልዬንም እኮ ከዚህ በፊት ማለቴ አንቺ ከመድሀኔ ጋር ተገናኝተሸ ከመጀመርሽ በፊት ስለሁለታችሁ ግንኙነት ጠይቄው ነበር…››