Get Mystery Box with random crypto!

የእናቴ ልጅ ክፍል አንድ እኔና ወንድሜ ከፊት ከዋላ የሌለን ብቸኛ የእናታች | አትሮኖስ

የእናቴ ልጅ
ክፍል አንድ

እኔና ወንድሜ ከፊት ከዋላ የሌለን ብቸኛ የእናታችን ልጆች ነን እኔም እሱም ከልጅነታችን ጀምሮ ከእናታችን በስተቀር ማንንም እንደቤተሰብ ሳናውቅ በትልቁ ቤታችን ውስጥ ከግቢ ሳንወጣ አድገናል ፣ እናታችን ብዙም ሰው ስታቀርብ አላየንም ፣ እኛን ወደትምህርት ቤት ለማድረስ ይዛን ስትወጣ እንኳ ከጎረቤቶቿጋር ስትገናኝ በጣም የሳሳ ሰላምታ ነበረ ያላት ፣  ካደግን በዋላ እንኳን እኔ ነበርኩ ከሰው የማገናኛት  በሰላም ግን አይደለም ይህን ማለት ተገቢ ባይሆንም እንኳ በፀብ ነበር ከሰው ጋር ያገናኘዋት  በቃ እኔ ከማን እንደወረስኩት አላውቅም ነገሮችን በቀላሉ ማለፍ የምችል ሰው አልነበርኩም ቀድሜ ፀብ አልጀምርም ከነኩኝ ግን በፍፁም ፀብ ማብረድ የምችል ሰው አይደለውም ፣በዚ የተነሳ ከእናቴ ጋር ሆድና ጀርባ ሆንን ፣እናቴ  ተከባብሬ በኖርኩበት ሰፈር አዋረደኝ አሰደበኝ  ለአመታት ዘግቼ ከኖርኩበት ቤቴ በሱ የተነሳ አደባባይ ወጣው ብላ ለኔ ያላት ፍቅር ተቀዛቀዘ  ከጎኗ ሆኖ የሚያፅናናት ብቸኛ ልጇ ታናሽ ወንድሜ ሆነ  ወንድሜን የምበልጠው በሁለት አመት ነው  ነገርግን ለሚያየን ሰው እሱ ነው ታላቅ የሚመስለው  እኔ የሃያ አንድ እሱ አስራ ዘጠነኛውን ይዟል  ቢሆንም እንደኔ ቅብጥብጥ አይደለም በጣም የተረጋጋ እና ነገሮችን አስቦበት አቅዶ የሚያደርግ አይነት ሰው ነው ፣  በኔ ሁሌም እንደተናደደ እንደተበሳጨ ነው  ወደ እናቴ እንዳልቀርብ የተቻለውን ጥረት ሲያደርግ ሳየው አንዳንዴ በውስጤ እታዘበዋለው እውነት እናቴን የምጎዳትእየመሰለው ነው ወይስ የሷን ፍቅር እንዳልጋራው ለራሱ ሰስቷት ፣አይገባኝም ብቻ  ፣
አስታውሳለው አንድ ቀን የሰፈር ልጅ ነው  አመሻሽቼ ስመጣ አንድ ጥግ ላይ ከጓደኛው ጋር ተቀምጦ ልክ እኔ እልፍ ስል 'ሹፈው የሰፈራችንን በሬ ከፊቱ ብትቆም ወግቶ ከመግደል ወደዋላ አይልም 'ሲል ሰማውት በሱቤት ድምፁን ቀንሶ ማውራቱ ነው እኔግን ሰማውት በቃ ያለምንም ቃል ነበር ሁለቱንም በተቀመጡበት የረገጥኳቸው እስኪለምኑኝ ፈጣሪ ሲረዳቸው  አንዲት የጎረቤት ልጅ ቆማ ታይ ነበርና በጩኽት ሰው ሰበሰበች  እየተሯሯጡ የመጡ ጎረቤቶች ልጆቹን አስጣሏቸው ፣በጉልበቴ ሳይገረሙ አይቀርም 'ምን አልቻልነውም እኮ ፀብ ውስጥ ሲገባ ሴጣኖች ዘጠኝ ሆነው ሳያብሩለት አይቀርም 'ሲባባሉ ሰማው  እናቴ እንደፈረደባት መጥታ ያዘችኝ ወደቤት እንድገባ ለመነች ወንድሜ እንደታላቅ አበደብኝ ሰደበኝ  "አንተ ዘላለምህን አትማርም ተው ስትባል አትሰማም ለምንድነው እናቴን የምታሳቅቃት   ብሎ ወቀሰኝ ። እናቴ እንደዛ ሲናገረኝ አሳቢነቱ እና የኔ እንቢተኝነት ሆድ አስባሳት መሰለኝ አለቀሰች እሷ ስታለቅስ ሳይ ወደራሴ ተመለስኩ ሁሉንም ነገር ትቼ ወደቤት ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛው  ተኝቼ አስብ የነበረው ስለ እናቴ ነበር በቃ የዕንባዋ ምክንያት መሆኔን አልወደድኩትም ፣የዛኔ ነበር ለራሴ ቃል የገባውት ከዚ በዋላ ለሷ ስል ለመታገስ ፣ ግን ደስ የሚለው እኔ ፀብ አቁሜ እንኳ በቀድሞ ጭካኔዬ በሰፈሩ ሰው የተከበርኩ ሆኜ ቀጠልኩ ፣ አሁን ላይ ፀብ የለም ግን የቸገረኝ እንደቀልድ የጀመርኩት ሱስ መላቂያው ነው ፣ እናቴ ስለኔ ትታለች  ከወንድሜ ጋር ነው ነገሯ ሁሉ   ታምሜ እንኳ ዞር ብላ አታየኝም ፣  የምትጨነቀው ለታናሽ ወንድሜ አቤል ነው ፣ 

ደራሲ unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj