Get Mystery Box with random crypto!

'እንዴት እንደዛ ታስቢያለሽ  የእኔ የሆነው ብርም ሆነ ወርቅ እኮ የአባትሽም ጭምር ነበር የራሱን | አትሮኖስ

"እንዴት እንደዛ ታስቢያለሽ  የእኔ የሆነው ብርም ሆነ ወርቅ እኮ የአባትሽም ጭምር ነበር የራሱን ንብረት ለምን ብሎ ይሰርቃል?"
"እኔ ምን አውቃለሁ ?እማዬ እኔ እኮ አይደለሁም ያንን የተናገርኩት አባትሽ ነው ..ያንቺ አባት?"
"ቆይ ይሄን ጉድ አሁን በምን ተአምር ልታስታውሺ ቻልሽ?"
"እማዬ አሁን  ዋናው አስፈላጊው ነገር እሱ ነው? ወይስ አንቺም የነገሩ ተባባሪ ስለነበስሽ  ከጥያቄዬ  እየሸሸሽ ነው?"
"አይደለም ልጄ"
"ካልሆነ ንገሪኛ...አባቴ ምንድነው የሠረቃችሁ"
"ነገሩ የስርቆት ጉዳይ አይደለም"
"እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው?"
"አያትሽን ታውቂው የለ ንግግሩ ቀጥታ አይደለም...በወቅቱ እንደዛ የሆነው ከሌላ ሴት ጋር  መማገጡን ሰምቶ ነው..?"
"ሴት ሴት ጋር?እና ሴትና ሌብነትን ምን አገናኘው"
"እሱማ ይገናኛል ያው ከትዳሩ ተደብቆ ሌላ ሰው ጋር ሲሄድ ሰረቀ ነው የሚባለው ...ይሄ የተለመደ አገላለፅ ነው..."
‹‹እና አባቴ በአንቺ ላይ ቺት ስላደረገብሽ ብቻ ከቤትም ከሀገርም ያባረራችሁት...ይሄ ጭካኔ አይመስላችሁም።"
"እኔ በዛ ጉዳይ ያላዘንኩ ይመስልሻል...ጉዳዩን በወቅቱ አውቄ ቢሆን   እንደዛ እንዲሆን እጄን አጣጥፌ የምቀመጥ ይመስልሻል።እንደው የማደርገው ቢጠፍኝ እና እሱን ማስቀረት ቢያቅተኝ ተከትዬው እጠፋ ነበር።"
"እሺ በወቅቱ አላወቅሺም ነበር ..ከዛ በኃላስ አባቴን ለምን ሳትፈልጊው?"
"አምስት አመት ሙሉ  ከሶስት በላይ ሰዎችን ቀጥሬ በድፍን ኢትዬጰያ አስፈልጌዋለሁ....ግን እምጥ ይግባ ስምጥ ሊገኝ አልቻለም።ከዛ ምን አልባት ከሀገር ወጥቶ ሊሆን ይችላል ብዬ አሰብኩና ተስፋ ቆረጥኩ።››እናቷ ስያወሩ እንባቸው እያረገፈ ነበር።
"ቆይ እማ ...በመካከላችሁ ችግር ነበረ እንዴ? ማለት አለመጣጣም ካሌለ ባንቺ ላይ  እንዴት?››
"የሚያንገበግበኝ እሱ ነው...አባትሽ  ምንም ጥፋት አልነበረበትምም.. ያቺ ይሄድባት የነበረችው በጣም የሚወዳት የልጅነት ፍቅረኛው ነበረች.በመሀከላቸው ጣልቃ የገባሁት እኔ ነበርኩ፡፡አባትሽን በጣም አፍቅሬው ስለነበረ ከእሷ የነጠቅኩት እኔ ነኝ፡፡እና አባትሽ ጨርሶ ሊረሳት ስላልቻለ አልፎ አልፎ ጎራ ይላል…ያንን ደግሞ እኔ በድንብ አውቃለሁ…ግን ሙሉ በሙሉ እንዳላጣው በሚልና የእራሴንም ጥፋት ስለማውቅ ነበር አይቼ እንዳላየሁ በመሆን ጉዳዩን በፀጋ የተቀበልኩት፡፡አባቴ ግን ይሄን ሁሉ ታሪክ ስለማያውቅ ሴትየዋ ቤት ሲገባ ብቻ ስለያዘው ያንን አደረገ››
‹‹እንዴ ታዲያ አባቴ እንደዛ ብሎ አያስረዳውም ነበር..ለምን እውነቱን አልነገረውም››
‹‹ያው ለእኔ ብሎ ነዋ….አባቴ እንዳያፍርብኝና እንዳይረግመኝ በማሰብ እራሱን ሰዋ››
‹‹እና አባቴ ሌባ አልነበረም ማለት ነው፡፡››
‹‹በፍፅም..››
ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነው የተሰማት‹‹…የእኔ አባት የመስዋዕት በግ ነው የሆነው››አለች…ሁለቱም ለቅሶቸውን መቋቋም አልቻሉም፡፡
‹‹ግን አንድ ነገር እኔ አሁነ እየሰራው ያለሁት እናቴ በወጣትነቷ የሰራችውን ስህት አይነት  እኮ ነው፡፡እኔ ቃልና ከጊፍቲ ለመንጠቅ ጥረት ላይ እንዳለሁ .አባቴም በእናቴ ከሌላ ሴት ጉያ የተሰረቀ ነበር…የታሪኩ ፍፃሜ ግን ይሄው የተወናባበደ ሆኗል….የእኔና የቃልዬስ…?.›ስትል የስጋት ሀሳብ አሰበች.‹‹እግዚያብሄር ያውቀል፡፡›ስትል ደመደመች..እራሷን አመማት…..እየተጎተች ተነሳችና በዝምታ ወደ መኝታ ቤቷ ሄደች፡፡


ይቀጥላል