Get Mystery Box with random crypto!

#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_አምስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ በቀጠሯችን መሰረ | አትሮኖስ

#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

በቀጠሯችን መሰረት ወደቃል ቤት እየሄደች ነው።ይህ ቀጠሮ ለእሷ ልክ እንደከዚ ቀደሞቹ ቀጠሮዎች አይነት አይደለም።ቀጠሮውን ሳታሲዘው እንኳን "ለብቻህ ለረጂም ሰዓት ነው የምፈልግህ..በምንም አይነት የማይሰረዝ የሞት ቀጠሮ ነው"ነበር ያለችው።ልክ ስድስት ሰዓት እሱ ቤት ለመገናኘት ነው የተቀጣጠሩት። ሁለት ሰዓት ከቤት ወጣች፤ የውበት ሳሎን ደንበኞቾ ጋር ሄደች ...ከጥፍሯ አንስቶ ቅንድቧን ፀጉሯን እስክታስተካክልላት አራት ተኩል ሆነ...እቤት ሄዳ በሀገሪቱ አለ በተባለች ዲዛይነር በልዩ ሁኔታ ያሰፋችውን የሀገር በሀል ቀሚስ ለብሳ እሱን ደስ ያሰኘዋል ብላ ባሰችው አለባበስ ዘንጣ መኪናዋን እሱ የሚኖርበት ግቢ አስገብታ ስታቆም ሰዓቱ 6.03 ይል ነበር።የመኪናዋን ሞተር ከጠፋችና ለእለቱ ልዪ ዝግጅት ማድመቂያ ይሆን ዘንድ ይዛ የመጣችውን ቶርታ ኬክ፤ውስኪ፤ሻማዎች እና ቸኮሌቶችን ከእነ ዘንቢሉ እየተንገዳገደችም ቢሆን ይዛ ወረደችና ወደ ቃል ቤት ልትታጠፍ ስትል አሮጊቷ የቤት አከራይ ከእቤታቸው ሲወጡ ተገጣጠሙ ።
"ውይ በጌታ መጣሽ?"አሉ ከሞት የተነሳ ዘመዳቸውን ድንገት እንዳዩ አይነት ደንግጠው። የአሮጊቷ መደንገጥ ብቻ ሳይሆን እንባቸውም እየረገፈ ነው ።
" ማዘር ምን ሆኑ?"
‹‹አረ ምንም አልሆንኩ..ምነው ጠየቅሺኝ?"
"አይ እያለቀሱ ነው ብዬ ነዋ"
"እ አይ ልጄ ጭስ ነገር ነበር ..እቤት ያው ያሮጊት ነገር ታውቂ የለ"
"በሉ እሺ"ብላ መንገዷን ስትቀጥል
"ቆይ ልጄ ቁልፍ ልስጥሸ"አሏትና አስቆሟት፡፡
ውስጧን ክፍት አለው"ምነው ቃል የለም እንዴ?››ለስለስ ባለ ድምፀት ጠየቀቻቸው ።
"ቃል ነው ያልሽው ?"አሉና ወደውስጥ መግባቱን እረስተው ፍዝዝ ብለው ቆሙ፡
"እንዴ እማማ ..ችግር አለ እንዴ?"
"አረ የለም..ማለቴ ቃል ወጣ ብሎ ነው አልቆይም ብሎል"ብለዋት ወደ ውስጥ ገቡ ።
"ቃል ደግሞ በዚህ ቀን?ለዛውም እንዲህ አስጠንቅቄህ"ቃል ስሯ ሆኖ ባይሰማትም ተነጫነጨችበት ።
አሮጊቷ አምጥተው ቁልፍን ሰጧት... ነገረ ስራቸው አላማራትም‹..አይናቸውን ከዓይኔ ለምንድነው የሚያሸሹት?›ቁልፉን ተቀብላ እያልጎመጎመች ወደጓሮ ዞረችና የቃልን ቤት ከፍታ ገባች።እንደወትሮ ፅድት እንዳለ ነው።እሷ ግን ከወትሮ የተለየ የደመቀና የፈካ እንዲሆን ነበር የፈለገችው።ልቧ ላይ እንደሚንቦገቦገው አይነት የደስታ ብርሀን እቤቱም እንደዛው ይሆናል ብላ ጠብቃ ነበር.. በሚገርም ሁኔታ ግን ምን እንኳን እቤቱ በውስጧ በፈለገችው ሆኔታ ባይሸበርቅም ጠረጰዛው ግን በምትወዳቸው የምግብ አይነቶች ተሞልቶል። ሞባይሏን አወጣችና ከተለያየ አቅጣጫ አንድ ሶስት ፎቶዎች አነሳችና።‹‹እንደውም ጥሩ አጋጣሚ ነው ።እስኪመለስ አንዳንድ ነገሮችን አስተካክላለሁ› ብላ አሰበችና ወደውስጥ ዘለቀች።የቤቱን መብራት አበራችው...ሌላ አነስ ያለች ጠረጰዛ የክፍሉን አንድ ግድግዳ ተጠግታ ትታያለች።የጠረጰዛውን አቅጣጫ አስተካከለችና ያመጣችውን ኬክ መሀከል ላይ አስቀመጠችው.. የውሰኪ ጠርሙሱን አወጣችና ከጎኑ አደረገችው...ዝርግ ሰሀኖችን ፈለገችና ቸኮሌቶቾን በመዘርገፍ ቦታ ሰጠዋቸው ።
‹‹አዎ አሁን የጎደለው ሙዚቃና ቃልዬ ብቻ ነው።››አለችና ሙዚቃ ለመክፈት ወደመኝታ ቤት ገባች።ወደጂፓሱ ሄደችና ሶኬቱን ሰካችው.. እላዩ ላይ ፍላሽ ስለነበረ ከፈተችውና ድምፅን መጥና ወደሳሎን ልትመልስ ስትል አይኗ የቃልን አልጋ ላይ አረፈ..ከተነጠፈው ሰማያዊ የአልጋ ልብስ ላይ ሁለት ነጫጭ ፓስታዎች ተደራርበው ተቀምጠዎል።ለምን እንደሆነ ባይገባትም አልፋቸው መሄድ አልፈለገችም።ወደኃላ ተመለሰችና የአልጋው ጠርዝ ላይ በመቀመጥ አነሳቻቸው፡፡ ሁለቱንም በሁለት እጆቾ ይዛ ከላይ የተፃፈባቸውን አድራሻ አነበበች፡፡
አንደኛው‹‹ከቃል ለጊፋቲ የተፃፈ የስንብት ደብዳቤ ››ይላል።
‹‹የስንብት› ማለት ምን ማለት ነው?።አዎ ገባኝ መድህኔን ልታገባ ስለሆነ እየተሰናታት ነው…።በዚህ መጠን ተበሳጭቶብሻል ማለት ነው..ደግ አደረገ›› አለችና በውስጧ በስኬቶ በመኩራራት ፈነጠዘች፡፡
"እሱን ወደነበረበት አልጋ ላይ ወርወር በማድረግ ሁለተኛውን ገልብጣ፡፡ አድራሻውን ማየት ጀመረች፡፡ በተመሳሳይ ቀለም በአንዳ አይነት የፊደል አጣጣል የተፃፈ ነው፡፡ከቃል ለልዩ የተፃፈ የስንብት ደብዳቤ ይላል፡፡በዚህ ወቅት የቤቱ አየር ተበከለ ፤መተንፈስ ብቻ ሳይሆን አይኖቾን ከፍታ አካባቢዋን ሁሉ ማየት ነው ያቃታት.. ፖስታውን በሚንቀጠቀጡ እጇቾ ቀዳዳ ከፈተችው፡፡
‹ልዩ እንዲህ ያደረኩት አንቺን በአካል አግኝቶ መሰናበት ቀላል ሆኖ ስላላገኘሁት ነው።አንቺና ጊፍቲ ከአባቴ ቀጥሎ በዚህች ምድር ያላችሁኝ የቅርቤም የልቤም ሰዎች ናችሁ።ልዩ እኔ ከአሁን ወዲህ የለውም...እንደምታውቂው ነፍሴ በዚህ አለም ኳኳታና ትርምስ ደስተኛ አይደለችም።ከዚህ በላይ በውስጧ መኳተን ለእኔም ሆነ በዙሪያዬ ላሉ ሰዎች መልካም መስሎ አልታየኝም።ወደእዚህች ምድር የመጣሁበትን ምክንያት ለመመርመር ፀጥታ ወደአረበበትና በፅሞና ማሰላሰል ወደምችልበት ቦታ ማለቴ ወደገዳም አምርቼያለሁ።ነግሬሽ ባላውቅም ወደእዛ መሄድ የረጅም ጊዜ ውጥኔ ነበር...ግን ያው ይህቺ አለም የራሷ የሆነ ወጥመድ አላትና እስከአሁን ሊሳካልኝ አልቻለም ነበር።
ለማንኛውም እግዚያብሄር ነገሮች እንዲከወኑ የሚፈቅድበት የራሱ የሆነ ጊዜ አለው ...እናም ዛሬ ቀኗ ሆነችና ህልሜ ተሳካ።ካዛሬ ጀምሮ እኔ የመንፈሳዊው አለም ምልምል ወታደር ሆኜ ተመርጬለሁ።ጮርቃ የሆነውን መንፈሳዊ ህይወቴንም ጥልቀት ያለው የበሰለና ለሌላው የሚተርፍ እስኪሆን ድረስ በልምምድ ተጋለሁ ሁለት አመትም ፈጀብኝ ሀያ አመት ካልሆነም እድሜ ልክ አያስጨንቀኝም...በመንፈሳዊ ልምምድ ውስጥ ወደ ሰማያዊ ንቃት ለማደግ ምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ።እግዚያብሄርም እንደሚያግዘኝ እተማመናለሁ። አንቺም እንደምትፀልይልኝ ጥርጥር የለኝም።እንግዲህ ልዩ የህይወት አላማዬ አስገድዶኝ በመንፈሳዊ ተልዕኮ ተገድጄ ካልሆነ በስተቀር ከምሄድበት የፅሞናና የፀጥታ ቦታ ወጥቼ ወደእናንተ የምመጣ ስለማይመስለኝ ይህ ስንብት የመጨረሻችን ነው።ግን ደግሞ በሚቀጥለው አለም በተለየ ሁኔታ እንገናኛለን የሚል የፀና እምነት አለኝ።
በስተመጨረሻ ሁለት ነገሮችን እንድታደርጊልኝ እጠይቅሻለሁ ..የመጀመሪያው ለጊፍቲ ጥሩ ጓደኛ እንድትሆኚያትና ሁለተኛው ደግሞ በተቻለሽ መጠን አባቴን እንድትጠይቂው ነው።ያው አንቺም አባት የለሽም አይደል... አባቴን ሸልሜሻለሁ።የቤቱን ዕቃ ከጊፍቲ ጋር ተማክራችሁ እንደሚሆን አድርጉት ወይ ለተቸገረ ስጡት...ብቻ እንደመሠላችሁ። በስተመጨረሻ በእጆቼ ጣቶች በጥልቅ ምስጋናና በፍፅም ፍቅር የመጨረሻ ምሳ አዘጋጅቼልሻለሁ...ጣፍጦሽ እንደምትበይው እርግጠኛ ነኝ።በይ ቻው..እስከአሁን አብረን በቆየንባቸው ጊዜያቶች ስላሳየሽኝ ደግነት፤ስለ ሰጠሸኝ ፍቅር፡ስለአጎናፀፍሽኝ ደስታ ከልቤ አመሰግናለሁ!! አመስገናለሁ!!! አመሰግናለሁ... የእግዜያብሄር መንፈስ በልብሽ ይንገስ.. .አሜን
...እራሷን ተቆጣጥራ ፌንት በልታ ወደኃላዋ ተዘርራ ሳትወድቅ ደብዳቤውን አንብባ ጨረስችው.የዛ አይነት ፅናትና ብርታት ከየት እንዳመጣቸ ለራሷም ደነቃት...ምን እየተሠማት እንደሆነ ማወቅ አልቻለችም።

ይቀጥላል