Get Mystery Box with random crypto!

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች ኦሬንቴሽን ተሰጠ ********** በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ገ | ATC NEWS

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች ኦሬንቴሽን ተሰጠ
**********

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ገቢ ፍሬሽ ማን እና ሪሚዲያል ተማሪዎች ሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲዉ አራቱም ግቢዎች ኦሬንቴሽን ተሰጥቷል፡፡
የዚህ መርሀ ግብር ዋና አላማ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የሚሰጡ አገልግሎቶችን አዉቀዉ እና ተረድተዉ እንዲንቀሳቀሱ እና ችግር በሚያጋጥም ጊዜ ተማሪዎች እንዴት በሥነልቡና መረጋጋት እንዳለባቸዉ ለማስገንዘብ አላማ ያደረገ ነዉ፡፡
በመርሃ ግብሩ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ም/ፕረዚዳንት አቶ ልጃአለም ጋሻዉ ቁልፍ ንግግሮችን ያደረጉ ሲሆን ተማሪዎች መብትና ግዴታቸዉን አዉቀዉ፤ተረጋግተዉ እና ተከባብረዉ የመጡበትን አላማ አሳክተዉ መሄድ እንደሚገባ በንግግራቸዉ ገልጸዋል፡፡
በፕሮግራሙ በአራቱም ግቢወች 5000(አምስት ሺህ) ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን የስነልቡና እና የአገልግሎት አሰጣጥ ሥልጠናዎችን ከወሰዱ በኋላ የተለያዪ ግንዛቤ ጥያቂዎችን አንስተዋል በመድረክ በኩልም ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶ የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር መርሃ ግብሩ ተጠናቃል፡፡


ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news