Get Mystery Box with random crypto!

ባለ ዘርፈ ብዙ ባለሙያ የJimma University ተመራቂ ተማሪ። የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሚያዝያ 0 | ATC NEWS

ባለ ዘርፈ ብዙ ባለሙያ የJimma University ተመራቂ ተማሪ።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሚያዝያ 05/2016 ዓ.ም ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል ባለ ዘርፈ ብዙ ባለሙያው ተመራቂ
ዶ/ር በዛብህ ብርሃኑ ይገኝበታል ።

ከመደበኛ ትምህርቱ ጎን ለጎንም ስነ-ፅሁፍ የሚወደው ተማሪው መፅሐፍትን ማሳተምና የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በመፃፍ በሃገር አቀፍ ደረጃ ትልቅ እውቅና አግኝቷል።

ምንም እንኳን የሜዲካል ትምህርት በባህሪው ጊዜ የሚፈልግ ቢሆንም በቅርቡ የሚያሳትመውን ጨምሮ አራት መፅሐፍትን ሲፅፍና ከ6 በላይ ሲትኮም ድርሰቶችን ሲከትብ በትምህርቱ ላይ ተፅዕኖ እንዳልፈጠረበት ተመራቂው ይናገራል።

በጥርስ ህክምና የዶክተሬት ተመራቂው በዛብህ ብርሃኑ በሀገራችን በተለያዩ ቴሌቪዥን የሚተላለፉ ተከታታይ ድራማዎች ላይ በደራሲነት ተሳትፏል ፣ በርካታ ሲትኮሞችንም በመፃፍ Mr. sitcom የሚል ስም አግኝቷል።

በደራሲነት ከተሳተፈባቸው ስራዎች መካከል ዘጠነኛው ሺ ከ35 ክፍል በላይ ፤ መስሪያ ቤት ፣ ሳሎኑ ፣ ዶክተሮቹ ፣ ፊሽካዎቹና አንድ ላይ የተሰኙ ድራማዎች ላይ በደራሲነትና በዳይሬክተርነት ተሳትፏል። በርካታ የቴሌቪዥን እና የራዲዮ ማስታወቂያ አዘጋጅቷል።

ደራሲ ዶ/ር በዛብህ ብርሃኑ የአፍ ጤና አጠባበቅ ለልጆች እና ለወላጆች የሚል መማሪያ መፅሐፍ አዘጋጅቶ ያጠናቀቀ ሲሆን መፅሃፉ በቅርቡ ለህትመት እንደሚበቃ ተናግሯል።

ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ ሲወጡ ከትምህርታቸው ጎን በማወቅ ጊዜያቸውን በአግባቡ ተጠቅመው ተሰጧቸውን በመፈለግ ማውጣትና ማሳየት አለባቸው ብሏል።

(መረጃው የጅማ ዩኒቨርስቲ ነው )

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news