Get Mystery Box with random crypto!

በዲላ ከተማ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰዎች ተጎዱ | ATC NEWS

በዲላ ከተማ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰዎች ተጎዱ

በዛሬዉ እለት በዲላ ከተማ ከባድ የተባለ ዝናብ መጣሉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ ንፋስ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያትም ሆኗል።

አደጋው የተከሰተው ዝናብ ተጠልለው ባሉት ልጆች ላይ በግንባታ ላይ ያለ አጥር ተደርምሶ ሲሆን በዚህም የ 2 ሰዉ ህይወት ስያልፍ በ 2 ሰዉ ደግሞ ከባድ ጉዳት ማድረሱን ነዉ የዲላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ምክትል እንስፔክተር እድገት ህርባዬ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል የሰማዉ።

ከዚህም በተጨማሪ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ኢንስፔክተር እድገት ህርባዬ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል የደረሰዉ መረጃ ያመላክታል።

#ዳጉ_ጆርናል
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news