Get Mystery Box with random crypto!

የኛ ARSENAL

የቴሌግራም ቻናል አርማ arsenalarmyofficial — የኛ ARSENAL
የቴሌግራም ቻናል አርማ arsenalarmyofficial — የኛ ARSENAL
የሰርጥ አድራሻ: @arsenalarmyofficial
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 209
የሰርጥ መግለጫ

ስለ አርሰናል የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም።
➥ በቻናሉ ውስጥ ያሉ ኘሮግራሞች 👇
♦️ የጨዋታ ኘሮግራም እና ውጤቶች📊
♦️ የቅድመ ጨዋታ ትንታኔ🗣
♦️ የተጫዋቾች ግለ ታሪክ👤
♦️ የተጫዋቾች የዝውውር መረጃ🔄
♦️ ጨዋታዎችን በቀጥታ
አስተያየት ካሎት በዚህ ያድርሱን ?
ለማስታወቂያ 👉 @konjoww

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-30 11:16:56 The Evening Standard ባወጣው መረጃ መሰረት አርሰናል ከጃክ ዊልሼር ጋር በወጣቶች የአርሰናል ቡድን የአሰልጣኝነት ቅጥር ዙርያ ተወያይቷል።
98 viewsMÏ Ķϥç, 08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 11:15:46
RUMOUR

አርሰናል የ3 ጊዜ የቻምፕዮንስ ሊግ አሸናፊ የሆነውን የሪያል ማድሪድ ንብረት ማርኮ አሴንሲዮን ለማስፈረም ንግግር ሊጀምሩ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ።
93 viewsMÏ Ķϥç, 08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 13:48:40
የአርሰናል የቅድመ የውድድር አመት መርሐ ግብር !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የቅድመ የውድድር አመት ዝግጅታቸውን በጀርመን ፣ አሜሪካ እና እንግሊዝ የሚያከናወኑ ሲሆን አምስት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን እንደሚያደርጉ ተዘግቧል ።

ሐምሌ 1 ኑረንበርግ
ሐምሌ 9 ኤቨርተን
ሐምሌ 13 ኦርላንዶ ሲቲ
ሐምሌ 16 ቼልሲ
ሐምሌ 23 ሲቪያ ( ኤምሬትስ ካፕ )

አርሰናል ከ ኑረንበርግ ጋር በጀርመን የመጀመሪያ የአቋም መፈተሻ ጨዋታቸውን ካከናወኑ በኋላ ወደ አሜሪካ በማቅናት ሶስት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን በማድረግ በኤምሬትስ ካፕ ሲቪያን በመግጠም የቅድመ የውድድር አመት ዝግጅታቸውን የሚያጠናቅቁ ይሆናል ።
110 viewsMÏ Ķϥç, 10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 13:47:07 #ጥልቅ_እይታ (ናብሪ >ራፊንሀ)

~የክለባችን አመራሮች ይሄንን የ 25 አመት ብራዚላዊ የቀኝ ክንፍ ተጨዋች (ራፊንሀ) ለማዘዋወር የፈለጉት በቀኝ ክንፍ አጥቂ ቦታ ላይ ከ ኒኮላስ ፔፔ በተሻለ ጥበበኛውን እንግሊዛዊ ቡካዮ ሳካን የመፎካከር አቅም አለው ፣ ወይም ደሞ ለታዳጊው ሳካ የበለጠ ተነሳሽነት በመፍጠር እራሱን ለበለጠ ድል እና ስኬት ያዘጋጃል አንዳንዴም ሳካ ጉዳት ካጋጠመው ወይም እረፍት ሊሰጠው ካስፈለገ ራፊንሀ [ Squad Player] ይሆናል ብለው ስላሰቡ ነበረ።

~እኔ በግሌ ራፊንሀ ቡካዮ ሳካን ተቀያሪ ወንበር ላይ የማስቀመጥ ችሎታ አለው ብየ አላስብም ፣ ሲጀመር እነ ኤዱም ያዩት የልጁን እምቅ ችሎት [ potential ] ነው እንጂ ተጨዋቹ በ ሊጉ ላይ እራሱን prove ያደረገ ተጨዋች ሆኖ አይደለም ፣ በሌላ አነጋገር ራፊንሀ ወደ አርሰናል ቤት መጥቶ በአንድ የውድድር አመት 15 እና ከዚያ በላይ ጎል እንደማያገባ ግልፅ ነው። በእኔ እይታ እራሱን prove ላላደረገ [ Squad Player ] ከ 50 ሚልየን ፓውንድ በላይ ማውጣት ተገቢ አይደለም።

~ባርሴሎናም እንደ አርሰናል ሁላ የዚህን ተጨዋች potential እና bright future በማየቱ ሊያዘዋውረው ፈልጎ ነበር ነገርግን የካታሎኒያው ሀያል ክለብ ባለበት የገንዘብ ችግር ምክንያት ከዚህ ዝውውር እራሱን ካገለለ ሰነባብቷል። ሊድስ ይሄንን ብራዚላዊ ተጨዋች እንዲህ ዋጋው እንደጦፈለት ሳይሸጠው ይሄ የዝውውር መስኮት እንደማይዘጋ ቀድሞ የተገነዘበው ክለባችን ያለፉትን ጥቂት ሳምንታት ያለማንም ተፎካካሪ ከ ዌስት ዮርክሻየሩ ክለብ ጋር ሲደራደር ቆይቷል። ሌላ ፈላጊ ክለብ እስካልመጣ ድረስም ይሄንን ብራዚላዊ በ 50 ሚልዮን የግሌ አደርገዋለውም ብሎ አስቦ እንደነበረ እሙን ነው።

~ነገርግን ባለቤት አልባ እንሆናለን ፣ ክለባችን ሊፈርስ ነው በቃ አለቀልን ብለው በተጨነቁበት ሰአት በነፍሳቸው የደረሰላቸው አሜሪካዊው ቢልዮኔይር ቶድ ቦሊ ከወዲሁ በቼልሲ ደጋፊዎች ልብ ውስጥ በጥልቀት ለመግባት እና የምእራብ ለንደኑን ክለብ በሚቀጥለው የውድድር አመትም ተፎካካሪነቱን ጠብቆ ማቆየት ያስችለው ዘንድ ቆርጦ እንደተነሳ ግልፅ ነው። ለዚህም ይመስላል በአንገብጋቢ ሁኔታ የክንፍ አጥቂ የሚፈልገው ቼልሲ ከየት መጣ ሳይባል በድንገት በ ራፊንሀ ዝውውር ውስጥ በመግባት 65 ሚልዮን + የተጫዋቹን ጥቅማጥሞች እና ሌሎችም በርካታ ክፍያዎችን በመክፈል የ ሊድስን ቀቢፀ ተስፋ እውን ለማድረግ ወስኗል።

~አሁንም ግን ክለባችን ለ ቡካዮ ሳካ ተቀያሪ የሚሆን የክንፍ አጥቂ መፈለጉን አላቆመም ፣ እንደ ራፊንሀ ከችሎታው በላይ ገንዘብ የተቆለለበት ሳይሆን Fair የሆነ ዋጋ የተቆረጠለትን ተጨዋች እስከ 50 ሚልዮን ፓውንድ በማውጣት የመግዛት ፍላጎት አለው። አሁንም ቢሆን እንደ ሰርጅ ናብሪ አይነት እራሳቸውን በትልቅ ደረጃ ላይ prove ያደረጉ የክንፍ አጥቂዎች በዝውውር ገበያው ላይ አሉ። ናብሪ ከ ቡንደስሊጋው ሀያል ክለብ ባየርን ሚውኒክ ጋር የሚያቆየውን አዲስ ውል አልፈርምም በማለቱ እሰጣ ገባ ውስጥ መግባቱ ይታወቃል። ክለባችን አርሰናልም ይቺን ምርጥ አጋጣሚ በመጠቀም ከ 50 ሚልዮን ባነሰ ዋጋ ይሄንን የ 26 አመት የቀድሞው የክለባችን ተጨዋች ወደ ቤቱ ሰሜን ለንደን ቢመልሰው መልካም ነው እላለሁ።

| @Dav_Gooner

VIA #ETHIO_ARSENAL
98 viewsMÏ Ķϥç, 10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 13:46:49
83 viewsMÏ Ķϥç, 10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 13:37:34
መሀመድ
ጄሱስ

አርሰናል አሁን ላይ በሀይማኖትም መቻቻል እንዳለ በተጫዋቾቹ አሳይቶናል ሲል 1 የ አርሰናል ደጋፊ ተናግሩዋል
85 viewsMÏ Ķϥç, 10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 13:36:25
የ ራፊንሃ ወኪል ዴኮ

ቻምፒዬንስ ሊግ መጫወት ይፈልጋል ለ አለም ዋንጫም ለመመረጥ ቋሚ ሆኖ ሚጫወትበትን ክለብ ይፈልግ ነበር ለዛም ነው ምርጫው ቼልሲ የሆነው።
81 viewsMÏ Ķϥç, 10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 13:35:08
|| የቼልሲ ተፅዕኖ !

ብዙዎቻችን ራፊናህ ወደ አርሰናል ባለመምጣቱ ወይም አርሰናል ተጫዋቹን ባለመግዛቱ ጥያቄ ፈጥሮብናል ። ነገር ግን ቼልሲ ተጫዋቹን እንዴት ሊወስደው ቻለ የሚለውን ማየትም ይጠበቅብናል ።

✓ ለ ሊድስ 70 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል ፍቃደኛ ነው ።

✓ ለ ወኪሉ የ 12 ሚሊዮን ፓውንድ ክፍያ ለመክፈል ፍቃደኛ ነው ።

✓ ለተጫዋቹ ዓመታዊ 12 ሚሊዮን ፓውንድ ድረስ ለመክፈል ፍቃደኛ ነው ።

* ዝውውሩ ይፋ ባይሆንም ባጠቃላይ 94 ሚሊዮን ፓውንድ ድረስ ተጫዋቹ ላይ ያወጣል ። ታዲያ አርሰናል የዚህን ያህል ሊደራድር ይችላል ወይስ ሌላ ክፍተቱን ይሞላል ?
81 viewsMÏ Ķϥç, 10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 13:34:31
ከሰባት አመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን አርሰናል አንጋፋውን የቼልሲ ግብ ጠባቂ ፒተር ቼክን አስፈረመ።

ቼክ በፕሪሚየር ሊጉ በአርሰናል ቤት፦

- 110 ጨዋታዎችን አደረገ
- 125 ግቦች ተቆጠሩበት
- 40 ክሊንሺት አስመዘገበ
- 336 ኳሶችን አዳነ
77 viewsMÏ Ķϥç, 10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 08:41:50
ኢዱ እና ሚኬል አርቴታ ሁሉም ስራዎች እስከ ጁላይ 6 እንዲጠናቀቁ በጣም ይፈልጋሉ።
87 viewsMÏ Ķϥç, 05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ